Thursday, November 30, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከጉዳት መልስ እንቅስቃሴ የጀመረው የከተማዋ ኢኮኖሚ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከጉዳት መልስ እንቅስቃሴ የጀመረው የከተማዋ ኢኮኖሚ

ሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት 3፡30 ሰዓት አካባቢ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በከተማዋ መሞቱን ተከትሎ ከፍተኛ ሁከት ተቀስቅሶ ነበር፡፡ ሆኖም የአዲስ አበባ ከተማ የወትሮው የንግድ እንቅስቃሴ ከዓርብ ሰኔ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እ ቀድሞው በመደበኛነት መካሄድ ጀምሯል። የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፣ ባንኮች፣ ልዩ ልዩ የንግድ መደብሮች ተከፍተዋል። ይን እንጂ በከተማው በርካታ የንግድ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በሁሉም አቅጣጫ በከተማዋ በሚገኙ በርካታ ሕንፃዎች ላይ መጠኑ የተለያየ የመሰባበር፣ የዝርፊያ አልፎ አልፎም የቃጠሎ አደጋዎች ታይተዋል፡፡ ከቦሌ እስከ መገናኛ፣ ከገላን እስከ ጀሞ ባሉ አካባቢዎች የደረሰው ውድመት ሥራቸውን ያስተጓጎለባቸው በርካቶች ናቸው። በቦሌ አካባቢ ሬስቶራንቶች፣ የመኪና መሸጫ መደብሮችና በውስጣቸው የነበሩ በርካታ ለሽያጭ የቆሙ ተሽከርካሪዎች የተሰባበሩባቸው ክስተቶች ተፈጥረዋል፡፡ በከተማዋ ሰሞኑን በተነሳው ሁከት በርካታ የግልና የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ተሰባብረዋል፡፡ ተቃጥለዋል፡፡

ባንኮች ላይ ከደረሰው ዝርፊያ ጥቃት መካከል በዓባይ ባንክ እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የደረሱት ጥቃቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በተለይ ዓባይ ባንክ ከስምንት ያላነሱ ቅርንጫፎቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ይፋ አድርጓል፡፡ ንግድ ባንክም በሁለት ቅርንጫፎቹ ላይ ዝርፊያን ጨምሮ፣ የመሰባበር ጥቃቶች የተፈጸሙባቸው ቅርንጫፎቹ ተጠጋግነው ሥራ የጀመሩ እንዳሉ እየታየ ነው፡፡

ከጀሞ እስከ ሚካኤል አደባባይ፣ ከጀሞ እስከ ፉሪ፣ አልፎም እስከ ዓለም ገና ባለው መንገድ የሚገኙ ተቋማት በርካታ ጉዳት ካስተናገዱ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በሁለቱም አቅጣጫ በሚገኙ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ባለፈው ጊዜ 97 ዜጎልፈት ምክንያት የሆነው የአቶ ጃዋር መሐመድ የተከብቤያለሁ ጥሪ ጋር በተያያዘ በተነሳው ሁከት በከተማው ክፍሎች የታየውን ዓይነት ተመሳሳይ ጥቃቶች ተሰንዝረዋል። ከሕንፃዎች መሰባበር ባሻገር፣ በርካታ ተሽከርካሪዎች ተሰባብረዋል፡፡

ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችና አምቡላንሶች ሲርመሰመሱባት የሰነበተችውና ከዳር ዳር ተዘግታ ሦስት ቀንና ሌሊት የሰነበትችው አዲስ አበባ፣ ስብርባሪዎቿን ጠራርጋ፣ የፈራረሱ ተቋሞቿን ጠጋግና ሥራ የጀመረች ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎችም ቀስ በቀስ ወደ ተለመደ ዕለታዊ ሥራቸው መግባት ጀምረዋል፡፡

በከተማዋ በተፈጸመው ጥቃት ብቻም ሳይሆን ለቀናት እንቅስቃሴዎች በመቋረጣቸው ሳቢያ ጭምር በከተማዋ የደረሰው ኢኮኖሚያዊ የጉዳት መጠን ምን ያህል እንደሆነ በዝርዝር የሚያመላክት መረጃ ማገኘት አዳጋች ቢሆንም፣ ይህንኑ የሚጠቁሙ አኃዞች ወደፊት ከመድን ተቋማትና ከሌሎችም ሊወጣ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች