Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​ፆታዊ ጥቃትን ‹‹ዝም አልልም››

​​​​​​​ፆታዊ ጥቃትን ‹‹ዝም አልልም››

ቀን:

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ መንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ያደረገው ከመጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ሕፃናትና ታዳጊዎች ከቫይረሱ እንዲጠበቁ ቢያስችልም፣ ልጆች ለሌላ ጥቃት እንዲጋለጡ ማድረጉ አልቀረም፡፡ ጠለፋ፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ አስገድዶ መድፈር በሕፃናትና ታዳጊዎች ላይ እየተጸመ ስለመሆኑ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ‹‹ዝም አልልም›› ፕሮግራም በወንድና በሴት ሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ወሲባዊ ጥቃት በመቃወም ችግሩ እንዲፈታ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ሲሆን፣ የሕፃናት ደኅንነት ጉዳይ የሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማንቃትና በማገዝ ላይ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ወሲባዊ ጥቃት አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑን በማስገንዘብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል የወንጀል ሕግ አንቀጾች እንዲሻሻሉ ለማድረግ ጥረት እያደረገም ይገኛል፡፡ የመቅዲ ፕሮዳክሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ መቅደስ ፀጋዬ (ተዋናይ) ‹‹ዝም አልልም›› ፕሮግራም ዕውን እንዲሆን ከሚሠሩ አንዷ ናቸው፡፡ ተመስገን ተጋፋው አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ‹‹ዝም አልልም›› ምን ዓይነት ፕሮግራም ነው?

ወ/ሮ መቅደስ፡- በሕፃናት ላይ የሚደርስ ፆታዊ ጥቃትን በመቃወም ችግሩ እንዲፈታ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ያለውን የሕፃናትና ታዳጊዎች የመደፈር ችግር ለመፍታት፣ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ማኅበረሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ እየሠራ የሚገኝ ፕሮግራም ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ፕሮግራሙ መቼ ተጀመረ?

ወ/ሮ መቅደስ፡- በዋልታ ቴሌቪዥን 51 በመቶ በሚል ሳምንታዊ ፕሮግራም ላይ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ በኩል የተገለጸውን አስደንጋጭ መረጃ በመስማት የተጀመረ ነው፡፡ ከተመሠረተም አንድ ወር ያህል ሆኖታል፡፡

ሪፖርተር፡- ፕሮግራሙን የሚሠሩት ከማን ጋር ነው?

ወ/ሮ መቅደስ፡- ከ42 በላይ የሚሆኑ ሲቪክ ማኅበራት፣ ዶክተሮች መንግሥታዊ የሆኑና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር አብረን እየሠራን እንገኛለን፡፡ የአዲስ አበባ ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ በቀጥታ የሕፃናት ጉዳይ የሚመለከተው ተቋም በመሆኑ፣ የ‹‹ዝም አልልም›› እንቅስቃሴን ለማድረግ የመጀመሪያውን ግንኙነት የፈጠርነው ከዚሁ ቢሮ ጋር ነበር፡፡ ከቢሮው ጋር በርካታ ውይይቶችንና ተከታታይነት ያለው የመረጃ ልውውጦችን አድርገናል፡፡ 16 የሚሆኑ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የሃይማኖት መምህራንን ያካተተ የሁለት ደቂቃ ከ39 ሰከንድ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ከመቅዲ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲተላለፍ በማድረግ ኅብረተሰቡ የሕፃናት መደፈርን እንዲቃወም እያደረግን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የችግሩ አሳሳቢነት የሚጎላው በአዲስ አበባ ነው ወይስ በክልል?

ወ/ሮ መቅደስ፡- ችግሩ በአገሪቷ ላይ በሁሉም ቦታዎች ቢኖርም፣ በይበልጥ እየተፈጠረ ያለው በክልሎች ነው፡፡ ይሁን እንጂ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ ብዙ ሕፃናት ልጆች በአባቶቻቸውና ቅርብ በሚሏቸው ሰዎች እየተደፈሩ ይገኛሉ፡፡ ክልሎች ላይ የጎላ እንዲሆን ያደረገው ምክንያት የግንዛቤ እጥረት፣ ከለላና ሕፃናትም በጨቅላ ዕድሜያቸው ለትዳር በመታጨታቸው ጭምር ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ችግሩ ከዚህ ቀደምም የነበረ ነው? የአሁኑን ምን ለየው?

ወ/ሮ መቅደስ፡- ወንድና ሴት ሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለው ወሲባዊ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በተለይም ደግሞ የግብረ ሰዶም ጥቃት መብዛቱ ችግሩን ይበልጥ ለየት እንዲል አድርጎታል፡፡ መረጃው እንደሚያሳየው በክልሎችም ሆነ በአዲስ አበባ ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ አብዛኛው ሕፃናት ወሲባዊ ጥቃት እየረደሰባቸው ይገኛል፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ችግሩ መባባሱ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል፡፡

ሪፖርተር፡- ከክልሎች ጋር በምን መልኩ እየሠራችሁ ነው?

ወ/ሮ መቅደስ፡- ‹‹ዝም አልልም›› የሕፃናት መደፈር አገር አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን በአግባቡ በመወጣት ችግሩ አፋጣኝ እልባት እንዲያገኝ የማንቃትና የመቀስቀስ ሥራ እየሠራ ነው፡፡ ከክልሎች ጋር በመሆን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችንና መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም ማኅበረሰቡ ጋር ጠልቆ በመግባት የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ፆታዊ ጥቃት ሲፈጸም በቤተሰብ በኩል የመደበቅ ሁኔታ አለ፡፡ ጉዳዩን ወደ ውጭ ለማውጣት ምን ታስቧል? ከዓቃቢ ሕግ ጋር ምን እሠራችሁ ነው?

ወ/ሮ መቅደስ፡- በየቤቱ በመግባትና በር በማንኳኳት የሕፃናት ልጆች ፆታዊ ጥቃት አስከፊነትን ለማኅበረሰቡ በማስተማር እንዲሁም ከጉዳቱ በኋላም ደፍረው ወደ ሕግ አካል እንዲወጡ ለማድረግ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆንና የተለያዩ አቅጣጫዎችን በመዘርጋት እየተሠራ ነው፡፡ ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር አጋርነት በመፍጠር የተለያዩ አንቂና አስተማሪ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ለሕዝቡ ለማድረስ ዕቅዶችን ይዘናል፡፡ ቀደም ብሎም በአዲስ አበባ ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ በኩል በተሰጠው መረጃ መሠረት፣ የ‹‹ዝም አልልም›› እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን ደብቀው ይኖሩ የነበሩ ተጎጂዎች በስልክና በአካል ወደ እኛ እየመጡ ይገኛሉ፡፡ ተጎጂዎቹን በመቀበልና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ከሚያገኙበት አካላት ጋር ለማገናኘት ኃላፊነታችንን እየተወጣን ነው፡፡ የፍትህ አካላት፣ ምሁራን፣ የሕፃናት ጉዳይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ሌሎችም ተሳታፊ የሚሆኑበት ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ ሊያስጨብጥ የሚችል፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚፈቅደው መልኩ ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ ከዓቃቢ ሕግና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀትም ጥቃቱ የደረሰባቸውን ሕፃናት ፍትህ እንዲያገኙ እያደረግን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ጥቃት ለደሰባቸው ምን ዓይነት ድጋፍ ታደርጋላችሁ?

ወ/ሮ መቅደስ፡- ለጊዜው የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ልጆች በሥነ ልቦና እንዳይጎዱ ከዝም አልልም አባላት መካከል ዶክተሮች ስላሉ በእነሱ በኩል የተለያዩ ምክሮች እንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡ በጤና ዙሪያ ያሉት ችግሮች እንዲፈቱም እያገዝን እንገኛለን፡፡ ወደፊት ግን ሰፋ ባለ መልኩ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን በገንዘብም ሆነ በሌሎች ድጋፍ ለማድረግ የምንሠራ ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡- ዝም አልልም የአንድ ጊዜ ፕሮግራም ነው ወይስ ቀጣይነት አለው?

ወ/ሮ መቅደስ፡- ዝም አልልም ቀጣይነት ያለው ፕሮግራም ነው፡፡ ከዚህ በኋላም በአገሪቷ ላይ በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የሚሠራ ይሆናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...