Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው››

‹‹ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው››

ቀን:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበራቸው ቆይታ፣ በኢትዮጵያ አንድነትና ጥቅሞች ላይ እንደማይደራደሩ አስታወቁ፡፡ ኢትዮጵያን ማፍረስም አይሞከርም ብለው፣ ‹‹ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2013 ዓ.ም. በጀትን ለማፅደቅ በተጠራው ስብሰባ በምክር ቤቱ በተገኙበት ወቅት ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ አንድነትና ጥቅም ላይ ያላቸው አቋም የፀና መሆኑን እንዲናገሩ ያስገደዳቸው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ፖለቲካ ጋር ተያይዞ የቀረበላቸው ጥያቄ ነው፡፡

የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ መንግሥት የሚከተላቸው አካሄዶች ሦስት መሆናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አንደኛው የግድቡን ግንባታ በጥራት ማከናወን፣ ሁለተኛው ከተፋሰሱ አገሮች ጋር በመወያየት መግባባትን መፍጠር፣ ሦስተኛው ደግሞ ትንኮሳዎችን መከላከል መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በቅርቡ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ሰበር ዜናዎች ምክንያት ዓይኑን ከህዳሴ ግድብ ላይ እንዲያነሳ ለማድረግ ከሚደረጉ መከራዎች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሃጫሉ በተገደለበት ሰዓት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታ ምክር ቤት ውይይት እየተካሄደ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ድምፃዊውን በመግደል የኢትዮጵያን ትኩረት ለማዛባት ሙከራ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ‹‹የሚሞቱ ይሞታሉ እንጂ ኢትዮጵያ የጀመረችውን አታቆምም፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከሌሎች የውጭ ኃይሎች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚጥሩ ኃይሎችንም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡ ‹‹ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው፤›› ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያንን እያጣሉና እያጋጩ መንግሥት መሆን አይቻልም ከአገር ውጭ ሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ አመፅ የሚቀሰቅሱትንም፣ ‹‹ከርቀት ሆናችሁ አመፅ የምታነሳሱና አመፁ መቆም የለበትም መቀጠል አለበት የምትሉ፣ ቢያንስ የሃጫሉን መንገድ ተከተሉና አገር ውስጥ ገብታችሁ ታገሉ፤›› ሲሉ ጥሪ አቅርበውላቸዋል፡፡

አገሩን ለማፍረስ እየሞከረ ለኢትዮጵያ እንደሚታገል የሚያስብ ኃይል ፈፅሞ ሊያሸነፍ እንደማይችልም ገልጸዋል፡፡ ‹‹እኛ በሕይወት እያለን የኢትዮጵያን መፍረስ አንፈቅድም፤›› ሲሉም አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡ የሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በእሳቸው ላይ ሐሜት መሰራጨት መጀመሩንም ጠቁመዋል፡፡

‹‹ዓብይ አህመድ ኦሮሞ አይደለም›› የሚል ዘመቻ እንደተከፈተባቸው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹ማንነቱን የካደ ዓብይ አህመድ ለሌላውም አይጠቅምም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ነፃ ወጥቷል፣ አሁን ልማት ነው የሚያስፈልገው፤›› ካሉ በኋላ፣ ኦሮሞን የሚከፋፍል ፖለቲካ እንደማይጠቅም ገልጸዋል፡፡

‹‹ለ30 ዓመታት የታገልኩት ለኦሮሞ ነፃነት እንጂ ኦሮሞ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር እንዳይኖር አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

የህዳሴ ግድቡን ድርድርና የውኃ ሙሌት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ ድርድሩ ወደ አፍሪካ ኅብረት መምጣቱ ትልቅ ድል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ድርድሩ ወደ አፍሪካ ኅብረት እንዲመጣ ጥረት ላደረጉት ለማሊ፣ ለደቡብ አፍሪካና ለዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ መሪዎች ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ድርድሩን በተመለከተ ኢትዮጵያ የተከተለችውን መንገድ በተመለከተ ወደፊት በዝርዝር እንደሚያቀርቡ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሁሉም የድርድር መንገዶች ኢትዮጵያ ማትረፏን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ዓመት የግድቡ ሙላት አይጀመርም ማለት ግድቡን ማፍረስ እንደ ማለት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ፓርላማው ለ2013 ዓ.ም. የቀረበለትን በጀት በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን፣ በቅርቡ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን አሥረኛ ብሔራዊ ክልል ሆና የተመሠረተው ሲዳማ ክልል የድጎማ በጀት 6.9 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...