Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

​​​​​​​ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

ቀን:

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማከናወኛ በቦንድ ግዥና በስጦታ 13.5 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኅበራት ፌዴሬሽን ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሄደው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዥ፣ ችግኝ ተከላና ደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ የጽሕፈት ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ሮማን ገብረሥላሴ እንደተናገሩት፣ ገንዘቡም ሊገኝ የቻለው ኅብረተሰቡ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የጀመረውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል ዳግም የሕዝብ ማነሳሳትና የቅስቀሳ ሥራ ከተከናወነበት ዕለት አንስቶ ነው፡፡

የማነሳሳቱና የቅስቀሳ ሥራ የተጀመረውም ከቦንድ ግዥና ከስጦታ ቢያንስ ከ15 በመቶ እስከ 20 በመቶ ለመሰብሰብ በማቀድ ሲሆን ኅብረተሰቡ ግን የዕቅዱን 14 በመቶ ለመሸፈን በቅቷል፡፡ 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በችግኝ ተከላው ዕለት የአካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኅበራት ፌዴሬሽን የ30 ሺሕ ብር ቦንድ ግዢ መፈጸሙን የፌዴሬሽኑ ዳይሬክተር አቶ በላይነት ጉጂ ገልጸዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ከዓመታት በፊት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ‹‹እኛም ድርሻ አለን›› በሚል ባዘጋጀው የድጋፍ ሥነ ሥርዓት ላይ ለግድቡ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የ10 ሺሕ ብር ስጦታና የ10 ሺሕ ብር ቦንድ ግዢ ማከናወኑን፣ የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞችም በዓመት ክፍያ የተጠናቀቀ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ማበርከታቸውን ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡ አሁንም ከተረፈው ሳይሆን ካለው በማካፈል ፌዴሬሽኑ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የቦንድ ግዥ በመፈጸም በግድቡ ግንባታ ላይ የአካል ጉዳተኞችን አሻራ በድጋሚ እንዳሳረፈም አስታውቀዋል፡፡ 

‹‹የምናልማት የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን  ለማድረግ የአገር ሰላም መሆን የማይተካ ዋስትና ይሰጣል፡፡ በአገር ሰላም መደፍረስ ውስጥ እኛ አካል ጉዳተኞች የመጀመርያው ተጠቂዎች ነን፡፡ በመሆኑም መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የምንማፀነው ለአገር ሰላም ዘብ በመቆም አካል ጉዳተኞችን በሕይወት የመቆየት ዋስትና በመስጠት የአገራችን ብልፅግና በማረጋገጥ የትሩፋቱ የጋራ ተጠቃሚ እንሁን፤›› ብለዋል፡፡

የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ እየተደረገ ስላለው ወቅታዊ ድርድር ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሮ ሮማን፣ ግብፅ የምታካሂደው ኢፍትሐዊ ትርክት በስግብግብነት የተሞላና ዓለም አቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት ያለመ እኩይ ተግባር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለዚህም በማሳያነት ያነሱት የግብፅ ሕዝብ የኑሮ ደረጃ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተሻለና መቶ በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆኑን ነው፡፡ በአንጻሩ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ 19 በመቶ ያህሉ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር፣ 54 በመቶ የሚሆነው ወይም 55 ሚሊዮን ሕዝብ ደግሞ ያለ ኤሌክትሪክ ብርሃን እስካሁን በጨለማ ውስጥ የሚኖር መሆኑን ነው፡፡

‹‹ከዚህም ማስገንዘቢያ በመነሳት ተደራዳሪዎቻችን የግብፅን ትርክት በማስረጃና በሳይንሳዊ መንገድ በማክሸፍ ሽንጣቸውን ገትረው እየተሟገቱና በዚህም አንዳንድ መልካም ውጤቶችን አስመዝገበዋል፤›› ያሉት ኃላፊዋ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ 16 ዩኒቨርሲቲዎችም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያተኩር መድረክ በመፍጠር፣ በውጭ ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያን ምሁራን ጋር በመቀናጀት የግብፅን የሐሰት ትርክት ለዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ የማጋለጥና ሃቁን የማስጨበጥ ሥራ በማከናወን ላይ መሆናቸውንንም አስረድተዋል፡፡

የህዳሴው ግንባታ ሲጠናቀቅ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብፅና ሱዳን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ፣ በተለይም ሁለቱ የተፋሰሱ አገሮች ግድቦቻቸው በደለል ከመሞላት እንዲሁም ደለሉንም ለመጥረግ በየጊዜው የሚያወጡት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘባቸው እንደሚያድንላቸው ከወ/ሮ ሮማን ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የቱሪስት መስህብ እንደሚሆን፣ ይህም ከድህነት አረንቋ ለመላቀቅ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ፣ ፋብሪካዎች ያለ ኤሌክትሪክ መቆራረጥ ማምረት እንደሚችሉ፣ እናቶች ከማዕድ ቤት ጭስ እንደሚገላገሉና በማጀት ተወስኖ የቀረው የእናቶች ጉልበት አደባባይ ወጥቶ ለልማትና ለሰላም እንደሚውል እምነታቸው መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...