Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየፌዴራል ዋና ኦዲተርን ሪፖርት ፓርላማው በአስቸኳይ ስብሰባ ካላዳመጠ ለሚዲያዎች ይፋ ሊደረግ እንደሚችል...

የፌዴራል ዋና ኦዲተርን ሪፖርት ፓርላማው በአስቸኳይ ስብሰባ ካላዳመጠ ለሚዲያዎች ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ተጠቆመ

ቀን:

የሥራ ዘመኑን ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ያጠናቀቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ባቀረበለት የኦዲት ሪፖርት ላይ ካልተወያየ፣ ሪፖርቱ ለሚዲያዎች ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ አስታወቁ። 

አቶ ገመቹ ለሪፖርተር እንደገለጹት ተቋማቸው በፌዴራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ላይ ያከናወነውን ኦዲትና ግኝቶቹን የተመለከተ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ሪፖርቱ ለምክር ቤቱ ሳይቀርብ የሥራ ዘመኑ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ከምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ጋር ሪፖርቱ መቅረብ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሳይመካከሩ የምክር ቤቱ የዘንድሮ የሥራ ዘመን ቢያበቃም፣ ከእነ ጭራሹ ሳይደመጥ ሊቀር ይችላል የሚል ሥጋት እንደሌላቸው አቶ ገመቹ አስረድተዋል። ተቋማቸው በፌዴራል መንግሥት ተቋማት ላይ በየዓመቱ የሚያከናውነው የበጀት አጠቃቀምና የሥራ ክዋኔ ኦዲት የመንግሥትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ስለሆነ፣ ዘንድሮ የተከናወነውን ኦዲት ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ እንደሚወያይበት እምነታቸውን ገልጸዋል። ይህ ካልሆነ ግን የኦዲት ግኝቱን የተመለከተው ሪፖርት በሁሉም የመገናኛ ብዙኃን በኩል ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም የፌዴራል ዋና ኦዲተር በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ተልዕኮውን መወጣት የሚችልበት አሠራር እንዲኖር ከምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር ቀደም ብለው ተወያይተው መግባባታቸውን የገለጹት ዋና ኦዲተሩሪፖርቱ ለምክር ቤቱ መቅረብ የሚችልበት ዕድል ካልተፈጠረ የሚዲያ አማራጭ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

ነገር ግን ከዚህ አማራጭ ይልቅ ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባ ሪፖርቱን ያዳምጣል የሚለው እምነታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህ የሚሰጡት ምክንያትም የምክር ቤቱ አባላት በተለመደው አሠራር መሠረት ዘንድሮ የእረፍት ጊዜያቸውን ወደ ተመረጡበት አካባቢ ሄደው ከሕዝብ ጋር የመወያየት ዕድላቸው በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የተገደበመሆኑ ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ መሠረት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን የኦዲት ሪፖርት የሚያዳምጠው፣ የቀጣዩ ዓመት በጀት ለምክር ቤቱ ከሚቀርብበት የሰኔ ወር መጀመርያ አስቀድሞ ወይም በግንቦት ወር ነበር። ይህ የተደረገበት ምክንያትም ምክር ቤቱ የቀጣዩን ዓመት ረቂቅ በጀት ሲመረምር ቀድሞ የቀረበለትን የኦዲት ሪፖርት ግኝቶች በግብዓትነት በመጠቀም፣ አስፈጻሚውን አካል ተጠያቂ እንዲያደርግና በጀት አባካኝ በሆኑ ተቋማት ላይ ዕርምጃ ሳይወሰድ በጀት እንዳይያዝላቸው ለመወሰን እንዲችል ነው።

‹‹የምክር ቤቱ የአሠራር ደንብ በሚያዘው መሠረት የዋና ኦዲተር ሪፖርት ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚቀርብ አጀንዳ ተይዞ ነበር። ዋና ኦዲተርም ሪፖርቱን ግንቦት 25 ከመድረሱ አሥር ቀናት በፊት ሪፖርቱን አስገብቷል። ነገር ግን ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት፣ የፓርላማው እንቅስቃሴ በመገደቡና በሌሎች ምክንያቶች ሪፖርቱ በተያዘለት ጊዜ ሊቀርብ አልተቻለም፤›› ሲሉ አቶ ገመቹ አስረድተዋል

የኦዲት ሪፖርቱ መቅረብ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ከአፈ ጉባዔ ታገሰ ጋር መምከራቸውን ያስታወሱት ዋና ኦዲተሩባደረጉት ውይይትም የኦዲት ሪፖርቱ ላይ ውይይት መካሄድ እንዳለበት ተስማምተው ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. የምክር ቤቱ ስብሰባ ተጠርቶ እንደነበር አስታውሰዋል። 

ይሁን እንጂ ከዚህ ቀን አስቀድሞ በነበረው ምሽት ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳመገደሉና ይህንንም ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት፣ ተጠርቶ የነበረው ስብሰባ ሳይካሄድ መቅረቱን ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ በነበሩት ቀናትም ቢሆን ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ መምከር አልቻለም። ነገር ግን ባለፈው ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ምክር ቤቱ የመጪውን ዓመት በጀት አፅድቆ የዘንድሮ የሥራ ዘመኑ ተጠናቋል።

ዋና ኦዲተር በየዓመቱ የሚያቀርበው የኦዲት ሪፖርት ግንቦት ወር ላይ የሚቀርብበት ምክንያት ምክር ቤቱ የቀጣዩ በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን በሚመለከትበት ወቅት፣ ዕርምጃ ለመውሰድ ወይም መንግሥትን ተጠያቂ ለማድረግ እንደ ግብዓት እንዲጠቀምበት መሆኑን ያስረዱት አቶ ገመቹይህ ግን አንዱ የኦዲት ሪፖርት ጠቀሜታ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል። 

የኦዲት ሪፖርት ዋና ዓላማ መንግሥት በታክስ አማካይነት ከሕዝብ የሚሰበሰበውን ገቢና አጠቃላይ የአገር ሀብት በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም የሕዝብ ሀብትን ያባከኑ የመንግሥት ተቋማትና ኃላፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል።

በመሆኑም ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ የቀረበለትን የኦዲት ሪፖርት ይመለከታል ብለው እንደሚያምኑ፣ ነገር ግን ይህ ካልሆነ ተቋማቸው የኦዲት ግኝቱን በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የሕዝብ ተወካይች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር የምክር ቤቱ አባላት በቅርቡ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደሚጠሩ ለሪፖርተር የጠቆሙ ቢሆንምአስቸኳይ ስብሰባው የሚጠራው የኦዲት ሪፖርቱን ለማዳመጥ እንደሆነ  ማረጋገጥ አልተቻለም።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...