Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአገሪቱ የተከሰተው ድርጊት አሳፋሪና ሊደገም እንደማይገባ ኢዜማ አሳሰበ

በአገሪቱ የተከሰተው ድርጊት አሳፋሪና ሊደገም እንደማይገባ ኢዜማ አሳሰበ

ቀን:

የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ሳቢያ በበርካታ ዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ የደረሰው ጥፋት እጅግ አሳሳቢ፣ አሳፋሪ፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተወገዘና በምንም ዓይነት ሊደገም የማይገባው ድርጊት ነው ሲል፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አስታወቀ፡፡

ኢዜማ ይህን አቋሙን ይፋ ያደረገው ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2012 ዓ.ም. የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እና ሊቀመንበሩ አቶ የሺዋስ አሰፋ አማካይነት፣ ‹‹የአገር ህልውናና የዜጎች ደኅንነት መጠበቅ የሁሉም ነገር መሠረት ነው›› በሚል መሪ ቃል በራስ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

በሰሞነኛው አለመረጋጋትና ብጥብጥ የደረሰው የበርካታ ዜጎች ሕይወት መቀጠፍና ከፍተኛ የንብረት ውድመት እጅግ አስከፊና የትውልዱ ማፈሪያ እንደሆነ ያስታወቀው ኢዜማ፣ ‹‹በዘውግ ማንነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ አካሄድ ወደ መቀመቅ እየወሰደን እንደሆነ፣ ሕዝብና መንግሥት ከበቂ በላይ ትምህርት አግኝተዋል፤›› በማለት፣ የሰሞኑ ድርጊት የዘውግ ፖለቲካው ያስከተለው ምስቅልቅል ነው የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በእውነተኛ ፌዴራሊዝም ሁሉም ራሱን በራሱ የማስተዳደርና በመረጠው የመተዳደር መብት እንደሆነ ኢዜማ ገልጾ፣ ፖለቲካው ከዘውግና ከሃይማኖት ካልተላቀቀ በስተቀር መጨረሻው እጅግ አደገኛ እንደሚሆን በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱን አስረድቶ፣ ይህ የፓርቲው አቋም ግን እንደ መለሳለስ መቆጠሩን አስታውሷል፡፡

ከዚህ በመነሳትም ከሰሞኑ በተከሰተው አለመረጋጋትና ብጥብጥ፣ ‹‹በድንገት የሚፈጠር ነውጥ አገራችንን ከማትወጣው የከፋ አዘቅት ውስጥ ሊያስገባት እንደሚችል፣ በዘውግና በሃይማኖት ላይ የሚሰበክ የፖለቲካ ትርክት፣ ከዚህ ትርክት ተነስቶ የሚቆሰቁሰው ፍፁም ስሜታዊ ጥላቻ፣ እንዲሁም ጥላቻው የሚቀሰቅሰው የደቦ እንቅስቃሴ የሰውን ልጅ ከሰብዓዊነት ማማ አውርዶ ወደ አውሬነት ሊቀይረው እንደሚችል›› መገንዘቡን ኢዜማ በመግለጽ፣ አሁንም ከዘውግ ፖለቲካ እንዴት መውጣት እንደሚቻል ሁሉም ቆም ብሎ ሊያስብ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

በቅርቡ የተከሰተውና በአገሪቱ ላይ ከፍተኛ የአለመረጋጋት አደጋ ደቅኖ የነበረው ክስተት  ለጊዜውም ቢሆን መክሸፉን  ያስታወቀው ኢዜማ፣ ‹‹ነገር ግን ችግሩ ዘላቂ የሆነ መፍትሔ አግኝቷል ማለት አይደለም፤›› በማለት፣ አሁንም ቢሆን ለዘላቂ መፍትሔ መሠራት እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል፡፡

‹‹ያለ አገር ፖለቲካም ሆነ ዴሞክራሲ ትርጉም የላቸውም፤›› ያለው ኢዜማ፣ ‹‹ከዚህ አንፃር ሁሉም የአገራችን ዜጎች ይህን ፈታኝ ጊዜ በትዕግሥት፣ በማስተዋልና በጥንቃቄ እንዲሻገሩትና የአገሪቱን አንድነትና ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነትና ድርሻ የመወጣት ግዴታ አለበት፤›› ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

የእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረት ለዘላቂ አገራዊ መረጋጋት መሠረት መሆኑን እንደሚያምን የገለጸው ኢዜማ፣ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚመሠረተው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ማለትም በእውነተኛ ውይይትና ድርድር ብቻ ነው፤›› ሲልም አቋሙን አስታውቋል፡፡

‹‹ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ሽግግር ዕውን ለማድረግ የሚያስችልና ለሁሉም ተስፋ የሚሰጥ የባለድርሻዎች ውይይት ሳይውል ሳያድር እንዲጀመር እንጠይቃለን፤›› በማለት ማሳሰቢያ አቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...