Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትመልስ ያላገኘው የሰበታ ከተማ አሠልጣኝና ተጫዋቾች ጥያቄ

መልስ ያላገኘው የሰበታ ከተማ አሠልጣኝና ተጫዋቾች ጥያቄ

ቀን:

ክለቦች በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን እግር ኳስ እንደገና ለማስጀመር በአንዳንድ ክለቦችና ተጫዋቾች መካከል ከወርኃዊ ክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ከፍተኛ ችግር እንቅፋት እንደሆነ ይወሳል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከደመወዝ ክፍያ ጋር ተያይዞ በክለቦችና በተጫዋቾች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት፣ ክለቦች በገቡት የውል ስምምነት መሠረት የተጫዋቾቻቸውን ወርኃዊ ክፍያ እንዲከፍሉ ያስተላለፈው ተደጋጋሚ መመርያና ማስጠንቀቂያ መፍትሔ ሊሆን እንዳልቻለ የሚናገሩ አሉ፡፡

ወቅቱ ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በየደረጃው የሚወዳደሩ ክለቦች ምንም እንኳ የ2012 የውድድር ዓመት በኮሮና ቫይረስ መቋረጡን ተከትሎ ወራጅም ሆነ ወጪ ሳይኖር በነበሩበት ለ2013 የውድድር ዓመት ቅድመ ዝግጅት የሚጀምሩበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ከሕግና ሥርዓት ውጭ ሆኖ የቆየው የክለቦች የፋይናንስ አሠራር በተለይም ከተጫዋቾች ክፍያ ጋር ተያይዞ እየተነገረ ያለው ጉዳይ ለእግር ኳሱ ተጨማሪ ውድቀት እንዳይሆን የክለብ አሠልጣኞች ጭምር ሥጋታቸውን መግለጻቸው አልቀረም፡፡

ከእነዚህ አሠልጣኞች መካከል በአሁኑ ወቅት የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ከለብን በማሠልጠን ላይ የሚገኘው አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ይጠቀሳል፡፡ አሠልጣኙ የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ለማሠልጠን ሲስማሙ ለተጫዋቾች ሊከፈል የሚገባውን ወርኃዊ ክፍያ ጨምሮ በሚያቀርቡት ዕቅድ መሠረት እንዲፈጸም ከክለቡ ጋር ስምምነት እንደነበው፣ ሆኖም ሥራ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ እስካሁን በስምምነቱ መሠረት ሁኔታዎቹ ተፈጻሚ እየሆኑ እንዳልሆነ ያስረዳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በፕሪሚየር ሊጉ የተለያዩ ክለቦችን በማሠልጠን የሚታወቀው አሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ለማሠልጠን ሲስማማ፣ በዕቅድ ደረጃ የተያዙ በተለይም ክፍያን ጨምሮ የተጫዋቾች አያያዝ፣ ለቅድመ ዝግጅት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችና መሰል ጉዳዮች እንደሚሟሉ ቃል የተገባለት ስለመሆኑ ጭምር ያስረዳል፡፡

አሠልጣኙ፣ “ስምምነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በክለቡ ሥራ ሲጀምር ሁለት ዓይነት ማልያና ቁምጣ እንዲሁም ተጫዋቾች በልምምድ ጊዜ የሚለብሱትን መለያ፣ ኮኖዎችን፣ የልምምድ ኳሶችንና ሌሎችም ቁሳቁሶች (ቆይቶ ቢሟሉም) በወቅቱ ግን በግሌ ገዝቼ ነው፡፡ በዚያ ላይ ወደ ክለቡ እንደመጣሁ ያስፈረምኳቸውን ጨምሮ ለሌሎችም ተጫዋቾች የሐምሌ፣ የነሐሴና የመስከረም ወር ክፍያ የተከፈለው ከሦስት ወር በኋላ ነው፡፡ በቅርቡ ወደ ሆነው ስንመጣ ደግሞ የግንቦትና የሰኔ ወር ክፍያ እስካሁን አልተከፈለም፤” በማለት የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ያስረዳል፡፡

በአሁኑ ወቅት ምንም እንኳ የኮቪድ 19 ወርሽኝ ጉዳይ ገና መፍትሔ ባያገኝም፣  ለቅድመ ዝግጅት የሚያስፈልጉ አንዳንድ ጉዳዮች ቀደም ሲል እንደነበረው ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ለክለቡ አመራሮች ያለፈውን ዓመት ሪፖርት ጨምሮ በቀጣይ ሊሟሉ ስለሚገባቸው ጉዳዮዎች ጥያቄ ማቅረቡን ጭምር አሠልጣኙ አልሸሸገም፡፡

ምክንያቱን አስመልክቶ አሠልጣኝ ውበቱ፣ “ካለፈው አንድ ዓመት ተሞክሯችን መረዳት የምንችለው በዚህ ሁኔታ ውጤት ከማምጣት ጀምሮ በፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቀጠል ከባድ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄድና አሠራር አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ለማምጣት ይቸግረኛል፡፡ ምክንያቱም የክለቡ አሠልጣኝ እንደመሆኔ ተጫዋቾች እንዲሟላላቸው የሚጠይቁትን ጥያቄ የማላስፈጽም ከሆነ በእኔ ላይ እምነት ስለሚያጡ፣ በሁለታችን መካከል የሚኖረው ግንኙነት መልካም ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ ማለት በተጫዋቾች ዘንድ ሊኖረኝ የሚገባው ክብር በራሱ ዋጋ እንዳይኖረው የሚያደርግ ነው፤” በማለት ያስረዳል፡፡

ወቅቱ ክለቦች ለ2013 የውድድር ዓመት ዕድሜ ዝግጅት የሚያደርጉበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ክለቦች የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች የሚያዘዋውሩበት ነው፡፡ ከተጫዋቾች  ክፍያ ጋር ተያይዞ ችግር የሌለባቸው አንዳንድ ክለቦች ኮንትራት ያጠናቀቁ ተጫዋቾቻቸውን ጨምሮ ሌሎችን ተጫዋቾች እያስፈረሙ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ ውበቱ እንደሚናገረው ከሆነ፣ ክለቡ የተጫዋቾች ክፍያን ጨምሮ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ይገኛል፡፡

ሰበታ ከተማ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ቅድመ ሁኔታዎችን የማያሟላ ከሆነ ቀጣይ ውሳኔያቸው ምንድነው ለሚለው የሪፖርተር ጥያቄ አሠልጣኝ ውበቱ፣ “ቀደም ሲል እንደተናገርኩት ክለቡ ሊያሟላ የሚገባውን ነገሮች እንዲያሟላ ጥያቄ ከማቅረቤ በፊት ማቅረብ የሚጠበቅብኝን ሪፖርት አቅርቤያለሁ፡፡ ከጥያቄዎቹ መካከል የክለቡ ቦርድ ተጫዋቾችን ሰብስቦ እንዲያናግርና የመፍትሔ አቅጣጫም እንዲያስቀምጥ የሚጠይቅ ጭምር ነው፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየት የምፈልግ መሆኔን ጭምር በጥያቄዬ አካትቻለሁ፤” ብሏል፡፡

አሠልጣኙ፣ “ክለቡ የፊርማን ጨምሮ ወርኃዊ ክፍያን ያጓደለብኝ ምንም የለም፤” ይህ ለእኔ ምንም ዓይነት እርካታ አይሰጠኝም፣ ምክንያቱም በወርሃዊ ክፍያና በሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞች ያኮረፈ ተጫዋች ይዤ የትም መድረስ እንደማልችል ስለምረዳ ነው፤” ብሏል፡፡ ይህ የተጫዋቾቹም ጥያቄ ስለመሆኑም ሳይገልጽ አላለፈም፡፡ ሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በቅርቡ የራሱን ስታዲየም ገንብቶ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...