Sunday, April 14, 2024

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አሠራርን የሚያሻሽለው አዋጅ ምን አዲስ ነገር ይዟል?

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓመቱን የሥራ ዘመን ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. አጠናቆ እረፍት በወጣ በሳምንቱ አባላቱን ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓም ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ካፀደቃቸው አዋጆች መካከል፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ማቋቋሚያ የሚያሻሽለው አዋጅ አንዱ ነው።

ደቀው አዋጅ በመግቢያ ምዕራፉ ማቋቋሚያ አዋጁን ለማሻሻል የተፈለገበትን ምክንያት እንደሚከተለው ያስረዳል።

‹‹የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተቋቋመበትን የሰብዓዊ መብቶችን ግንዛቤ የማስፋፋት፣ የማስጠበቅና የማስከበር ሥራ በተገቢው መንገድ እንዲያከናውን ማስቻልና የማስፈጸም አቅሙን ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፤›› ይላል።

በማከልም የኮሚሽነሮች አመራረጥና አሿሿም አሳታፊና ግልጽ ማድረግና የኮሚሽኑን የመዋቅር፣ የሠራተኛ ቅጥርና አስተዳደር፣ እንዲሁም የበጀት ነፃነት ማረጋገጥን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ማሻሻልና የተቋሙን ተዓማኒነት፣ ተቀባይነትና ውጤታማነት ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑንም መግቢያው ያስገነዝባል።

በማሻሻያ አዋጁ መግቢያ ከተገለጹት የማሻሻያውን አስፈላጊነት ከሚያስረዱት ጥቅል አገላለጾች በዘለለ፣ የማሻሻያ አዋጁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን አሠራርና ተልዕኮ ውጤታማ ከማድረግ አኳያ የሚኖረውን ፋይዳ የሚያሳዩትማሻሻያ ድንጋጌዎች የሚከተሉት ናቸው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 210/1992 አንቀጽ ስምንት ሥ ስለኮሚሽኑ አወቃቀር የተቀመጡት ድንጋጌዎች ዋና ኮሚሽነር፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነርና የሕፃናትና ሴቶች ኮሚሽነር፣ እንዲሁም ሌሎች ኮሚሽነሮች እንደሚኖሩት ተደንግጓል።

የፀደቀው ማሻሻያ ከላይ የተገለጹትን ድንጋጌዎች የተመለከተ መጠነኛ ማስተካከያዎችን ያካተተ ሲሆን፣ በዚህም ኮሚሽን ከዋና ኮሚሽነርናምክትል ዋና ኮሚሽነር ቀጥሎ ያሉትን በማሻሻል፣ ‹‹ሌሎች ከአራት ያላነሱ የልዩ ልዩ ሰብዓዊ መብቶች ዘርፍ ጉዳዮችን የሚመሩ ኮሚሽነሮች›› እንደሚኖሩት ደንግጓል።

በሥራ ላይ የሚገኘው አዋጅ አንቀጽ ዘጠኝ ሥር ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ከሚኖረው ዋና መሥሪያ ቤት በተጨማሪ፣ እንደ አስፈላጊነቱ በተለያዩ አካባቢዎች ቅርንጫፍ ቢሮዎች እንደሚኖረው የተቀመጠው ድንጋጌ ተሰርዞ፣ ‹‹የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ሆኖ በኮሚሽነሮች ጉባዔ ውሳኔ መሠረት፣ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሕፈት ቤቶች ወይም እንደ ሁኔታው አቤቱታ መቀበያ ማዕከሎች ሊኖሩት ይችላል፤›› በሚል እንዲሻሻል ተደርጓል።

ከላይ የተገለጹት ማሻሻያ ድንጋጌዎች ፋይዳን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ አሁን ባለው አሠራር የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ሕፈት ቤቶች ላይ ተመድበው የሚሠሩ አመራሮች፣ ሙያው ከሚጠይቀው ነፃነትና ገለልተኝነት በተቃራኒ ቅርንጫፎቹ የሚገኙባቸውን ክልሎች ፖለቲካ የመከላከልና ተጠሪነታቸው ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሆኖ ሳለ ለክልል አመራሮች እንደሆነ የመቁጠር፣ ወይም የመሳብ አዝማሚያ የሚታይባቸው በመሆኑ ማሻሻያው ሙያውንና ኃላፊነቱን እንዲያጎላ ተደርጎ መቀረፁን አስረድተዋል።

የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የመምራት ኃላፊነት ከአካባቢ ፖለቲካ ጋር የመቆራኘት አዝማሚያውን ለመቅረፍ የኮሚሽኑ አመራሮች በሰብዓዊ መብቶች ዘርፍ እንዲመደቡ በማሻሻያው መደንገጉን ያስረዱት አማካሪው፣ ይህም የሰብዓዊ መብት ጉዳይን የሚከታተሉ አመራሮች በቅርንጫፍ አካባቢዎች ፖለቲካ እንዳይሳቡ ለመከላከል፣ የልዩ ልዩ ሰብዓዊ መብቶች ዘርፎች ኮሚሽነር ሆነው እንዲመደቡና በዚህም ግንኙነታቸው ከሚከታተሉት ልዩሰብዓዊ መብት ጋር እንዲዛመድ የሚያስችል እንደሆነ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በአንድ ክልል አንድ የቅርንጫፍ ሕፈት ቤት ማቋቋምን የሚያስቀርና እንደ ነባራዊ ሁኔታዎች በአንድ ክልል በርካታ ቅርንጫፎችን ለመክፈት እንደሚያስችልም ገልጸዋል።

ማሻሻያው ከአራት ያላነሱ የልዩ ልዩ ሰብዓዊ መብቶች ዘርፍ ጉዳዮችን የሚመሩ ኮሚሽነሮች እንደሚኖሩ የሚደነግግ ሲሆን ነዚህን የዘርፍ ኮሚሽነሮች ሥልጣንና ተግባርም በሚከተለው መሠረት ደንግጓል።

በዚህም መሠረት የዘርፍ ጉዳይ ኮሚሽነሮች በዋናው ኮሚሽነር አማካይነት የሚመደቡበትን የሥራ ዘርፍ በኃላፊነት ከመምራት በተጨማሪ፣ ከዋናው ኮሚሽነር ጋር በመመካከር የሥራ ዘርፉን ማደራጀት፣ ማስተዳደር፣ የሥራ ዘርፉን ሠራተኞች መከታተልና መምራት ሚመሩትን ዘርፍ ወቅታዊና ዓመታዊ ክንዋኔ ሪፖርት ለዋና ኮሚሽነሩ ማቅረብ በዋና ኮሚሽነሩ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል።

ከላይ ከተጠቀሱት ማሻሻያ ድንጋጌዎች በተጨማሪ በሥራ ላይ በሚገኘው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ ስድስት ተጨማሪ ንዑስ አንቀጾች እንዲካተቱ ተደርጓል። በዚህም መሠረት በሥራ ላይ በሚገኘው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ ስድስት ሥ ኮሚሽኑ፣ ‹‹በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ስለሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታ ክትትል ማድረግ›› የሚል ድንጋጌ አንቀጽ 6(12) ሆኖ ዋጁ ካቷል።

ሌላው አዲስ ድንጋጌ ሆኖ የቀረበው ደግሞ፣ ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ማናቸውንም ማረሚያ ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች ወይም በቁጥጥር ወይም በዕገታ ሥር የሚገኙ ሰዎች ያሉበትን ሥፍራ፣ እንዲሁም እንደ ትምህርት ቤትና መጠለያ ጣቢያዎችና ሌሎች ሥፍራዎች ያለ ቅድመ ማስታወቂያ መጎብኘት፤›› የሚል አዲስ ድንጋጌ አንቀጽ 6(13) ሆኖ ተደንግጓል።

የኮሚሽኑን ነፃነት በተለይም ከሥራ አስፈጻሚው መንግ የበጀት ዕኖ ለመጠበቅ የኮሚሽኑ በጀት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚድቅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ ለኮሚሽኑ ደቀውን ዓመታዊ በጀት በየሦስት ወሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ወደ ኮሚሽኑ የባንክ ሒሳብ የማስገባት ግዴታ ተጥሎበታል።

ስለኮሚሽነሮች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞች፣ እንዲሁም  በተጨማሪ የሙያ ሥራ መሳተፍ እንዲችሉ የሚቻልበትን ኔታ የሚፈቅድ ድንጋጌ በማሻሻያው እንዲካተት ተደርጓል። በዚህም መሠረት የዋና ኮሚሽነሩምክትል ዋና ኮሚሽነሩናሌሎች ኮሚሽነሮች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞች እንደ ቅደም ተከተላቸው በሚኒስትር፣ በምክትል ሚኒስትርና በዋና ዳይሬክተር ማዕረግ ላሉ የመንግሥት ተሿሚዎች የተፈቀዱ መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች እንዲያገኙ ተደንግጓል።

ተሿሚ ኮሚሽነሮች ልዩ አስተዋጽኦ ማድረግ በሚፈልጉበት የጥቅም ግጭት የማይፈጥር ሌላ የሥራ ወይም የሙያ መስክ ቢኖር፣ ከኮሚሽነሮች ጉባዔ በሚቀርብ ሐሳብ መሠረት ከምክር ቤቱ ሕፈት ቤት ጋር በመመካከር ሊፈቀድ ንደሚችልም በማሻሻያው ተደንግጓል

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -