Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኢትዮጵያ አስጊነቱ የጎላው ኮቪድ 19

በኢትዮጵያ አስጊነቱ የጎላው ኮቪድ 19

ቀን:

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን በተለያዩ ጊዜያት በየመገናኛ ብዙኃን ሐሳብ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡ ሆኖም በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለው ግዴለሽነት እንደቀጠለ ነው፡፡ በትራንስፖርትና በገበያ ቦታ፣ በምግብና መጠጥ ቤቶች በጫት መሸጫ አካባቢዎች የሚታየው ጥንቃቄ የጎደለው አካሄድ፣ ኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመላከል የምትሠራውን ሥራ ወደኋላ የሚጎትትም ነው፡፡ የኅብረተሰቡ መዘናጋትም ለጤና ባለሙያዎችና ለመንግሥት ሥጋት ሆኗል፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አዝማሚያ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተወያየበት ወቅት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት ከመጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ  ያለውን ሥርጭት አስመልክተው የጤና ሚኒስትር አማካሪ ስንታየሁ ፀጋዬ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በቫይረሱ ከተያዙት 61 በመቶ ወንዶች፤ 39 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡ 92 በመቶ ሰዎች ደግሞ ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳዩ ናቸው፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) በወረርሽኙ ምክንያት የሚመዘገበው የሞት ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው 4.4 በመቶ የሞት ምጣኔ አንፃር ሲታይ ከፍተኛ የሚባል ባይሆንም፣ የሞት መጠንና የታማሚዎች ቁጥር መናር ወረርሽኙ እየጨመረ መምጣቱን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡

ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመጀመርያዎቹ 1,000 ሰዎች የተገኙት በመጀመሪያዎቹ 79 ቀናት ሲሆን፣ ቀጣይ 1,000 ሰዎች የተገኙት ደግሞ በዘጠኝ ቀናት ብቻ መሆኑ ወረርሽኙ እየጨመረ ስለመምጣቱ አመላካች መሆኑን ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር ስንታየሁ ሪፖርት ደግሞ፣ የሞት ምጣኔው 1.8 ሲሆን፣ 75 በመቶ የሚሆነው ሞት የተመዘገበው በአዲስ አበባ ነው፡፡

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ 75 በመቶ የጨመረ ቢሆንም፣ መታጠብና መራራቅ  ከ25 እስከ 30 በመቶ ውስጥ ይገኛል፡፡  የመመርመር አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመሆኑ ሪፖርቱ እስከቀረበበት ሐምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ፣ ከ302,000 በላይ ሰዎች የተመረመሩ ሲሆን፣ የዕለቱን ሳይጨምር በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 8,475 ደርሷል፡፡ ቁጥሩ እያደገ መምጣቱም አሳሳቢ ሆኗል፡፡

የሥርጭቱ መጠን እያደገ በመምጣቱም የበሽታውን ሥርጭት ለመግታትና ወረርሽኙን ለመከላከል ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከወረርሽኙ ስፋት፣ ሥርጭትና በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚታየው መዘናጋት የከፋ ችግር እንዳያስከትል በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ በበኩሉ፣ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ይረዳሉ በሚል የተቀመጡ መመርያዎች በተገቢው መንገድ እየተተገበሩት አለመሆኑንና ይህም የማይቀለበስ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል አስታቋል፡፡

የተለያዩ አገሮች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል ጥለዋቸው የነበሩ ገደቦችን እያነሱ በመሆኑ የቫይረሱ ሥርጭት እያገረሸ መምጣቱንም የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስን ለመከላል የተቀመጡ መመርያዎች ካልተተገበሩ የቫይረሱን ሥርጭት በአጭር ጊዜ መግታት አይቻልምም ብለዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ 14,043,778 ሰዎች በኮሮና የተያዙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 594,781 ሰዎች ሞተዋል፡፡ አሜሪካና ብራዚል ከፍተኛውን ሞት በማስመዝገብ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

8,333,787 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ቢሆንም፣ ቫይረሱ ጥሎት ከሚያልፈው ችግር ለማገገም ተጨማሪ ወራት እንደሚያስፈልግ የጤና ባለሙያዎች ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችን በመጥቀስ በጣሊያን፣ ስፔን፣ አሜሪካና ሌሎችም አገሮች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ቫይረሱ መላ አካላትን ጎድቶ የሚሄድ ነው፡፡ በመሆኑም ሰዎች ከቫይረሱ ቢድኑም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸው ላይ ጉዳት ይደርሳል፡፡

ቫይረሱ የመተንፈሻ አካልን የሚጎዳ ነው ተብሎ በስፋት ቢታመንም፣ ከሳምባ ባለፈ ኩላሊት፣ ጉበት፣ የሆድ ዕቃ፣ ልብ፣ አዕምሮና የጀርባ አጥንት ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

በወጣትነት ዕድሜ ላይ ያሉትን ጭምር ምት (ስትሮክ) እንደሚጥማቸው፣ ሕፃናት ከትኩሳት በተጨማሪ ሽፍታ፣ የዓይን መቅላት፣ የእጅ፣ የእግርና የዕጢ ማበጥ አንዳንዴም የልብ ችግር እንደሚያጋጥማቸው የጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ሰዎች በኮሮና ምክንያት ለተለያየ የጤና ቀውስ ከሚዳረጉ፣ ለጊዜው ሕክምና የሆነውን፣ እጅን መታጠብ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ አለመጨባበጥ፣ ርቀትን መጠበቅ፣ የበሰሉ ምግቦችን በንጽሕና መመገብ የግልና የአካባቢ ንጽሕናን መጠበቅ እንደሚገባቸው የጤና ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...