Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ መሥራች በፀረ ትምባሆ ሥራቸው በዓለም ጤና ድርጅት ተሸለሙ

የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ መሥራች በፀረ ትምባሆ ሥራቸው በዓለም ጤና ድርጅት ተሸለሙ

ቀን:

በሔለን ተስፋዬ

የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም የማጨስበትን ቀን አስመልክቶ በየዓመቱ በሚሰጠው የዕውቅና ሽልማት፣ የማቲዮስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ መሥራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ በቀለ፣ ‹‹በዓለም የማይጨስበት ቀን 2020›› ተሸላሚ ሆኑ፡፡

የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር)፣ የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ቡሬማን ሐማሳንቦ (ዶ/ር) እና ሌሎችም በተገኙበት በዓለም የማይጨስበት ቀን 2020ን ሽልማት ለማበርከት ሐምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በተዘጋጀ መድረክ የዕውቅና ሽልማት የተሰጣቸው አቶ ወንዱ፣ ለሽልማት የበቁት በኢትዮጵያ በተደረገው ፀረ ትምባሆ እንቅስቃሴ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦና ላስመዘገቡት ለውጥ ነው ተብሏል፡፡

አቶ ወንዱ የሚመሩት የማቲዮስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲና ሌሎችም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በኢትዮጵያ የትምባሆ ሕግ እንዲሻሻልና እንዲወጣ፣ በዚህም የትምባሆ ታክስ እንዲጨምር፣ በነጠላ እንዳይሸጥ፣ የማሸጊያዎች አብዛኛው ክፍል ማስጠንቀቂያ እንዲሆንና ሌሎችም ትምባሆን የማያበረታቱ ጉዳዮች ወደተግባር እንዲለወጡ መሥራታቸው ይታወቃል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ከአፍሪካ ከሸለማቸው ስድስት ግለሰቦችና የሚመሩዋቸው ድርጅቶች ከኢትዮጵያ አቶ ወንዱን መምረጡን በሥነ ሥርዓቱ ላይ ሽልማቱን ያበረከቱት ዶ/ር ቡሬማን ገልጸዋል፡፡

አቶ ወንዱ በፀረ ትምባሆ ሥራ ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠራቸውን በማስታወስም፣ በኢትዮጵያ የትምባሆ ቁጥጥር ላይ የጋራ ትብብርና ጥረት ባይደረግ በኢትዮጵያ አሁን የተመዘገበው ስኬት አይገኝም ነበር ብለዋል፡፡

በዕውቅና ሽልማት አሰጣጡ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር (ዶ/ር) ሊያ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ላለፉት ስድስት ዓመታት በዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን ሽልማት መሳተፏን አስረድተው፣ ኢትዮጵያውያን ለሦስተኛ ጊዜ የዕውቅና ሽልማት የበቁት በትብብርና በጋራ በመሥራታቸው እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡

እ.ኤ.ኤ. በ2019 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2014 የትግራይ ክልል  የሽልማቱ ተቋዳሽ መሆናቸው፣ በኢትዮጵያ ትምባሆን ለማስቀረት ያለውን ጥረት ያሳያል ሲሉም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ትምባሆ ማጨስ ልቅ እንዳይሆን ጠንካራ ሕግ በማውጣት ከአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ አገሮች ተርታ የምትሠለፍ መሆኗን አቶ ወንዱ ተናግረው፣ የተጀመረው የፀረ ትምባሆ ጥረት እንዲቀጥል፣ ሶሳይቲው ከብሪስቶል ሜየርስ ስኪዩብ ፋውንዴሽን ባገኘው የ57 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአፋር ክልሎችና በአዲስ አበባ የሚተገበር የሳምባ ካንሰር ፕሮጀክት እ.ኤ.አ. በ2020 መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በፀረ ትምባሆ ላይ የተጀመረው ሥራ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ፣ ምናልባትም በ2021ም ተሸላሚ የሚኮንበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነትም ተናግረዋል፡፡

ከጤና ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የኮሮና ወረርሽኝ በተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሕሙማን ላይ የሚያሳድረውን ተጨማሪ ችግር ለመቋቋም አዲስ ፕሮጀክት በመሥራት ላይ እንደሚገኙም አቶ ወንዱ ጠቁመዋል፡፡

ትምባሆ የሚያጨሱ ግለሰቦች በኮሮና የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን፣ ከተያዙም ሕመሙ ከፍተኛ ከመሆኑ በበለጠ ሕመማቸውን ውስብስብና አስቸጋሪ ሊያደርገው እንደሚችልና ትምባሆ የሚያጨሱ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ቢያዙ ከማያጨሱ ሰዎች በበለጠ ችግሩ ሊወሳሰብባቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው (ዶ/ር) ሊያ መክረዋል፡፡

በየዓመቱ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በትምባሆ ምርቶች ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ይህ እንዳይሆን ግንዛቤ ለማስጨበጭ በየዓመቱ ትምባሆ የማይጨስበት ቀን የሚከበር ሲሆን፣ ዘንድሮ በዓለም ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ ታስቦ ውሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...