Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኮንሶ የተገኘው 1.4 ሚሊዮን ዓመታት ያስቆጠረው ከጉማሬ አጥንት የተሠራው ጥንታዊ መሣርያ

በኮንሶ የተገኘው 1.4 ሚሊዮን ዓመታት ያስቆጠረው ከጉማሬ አጥንት የተሠራው ጥንታዊ መሣርያ

ቀን:

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎችን ትኩረት ስቦ የነበረው የሥነ ጥንት ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ ደቡባዊ አካባቢ በኮንሶ መካነ ቅርስ ከጉማሬ አጥንት የተዘጋጀ የእጅ መሣርያ ማግኘታቸውን የሚገልጸው የጥናት ውጤት ነበር፡፡

አስደናቂው ግኝት ተብሎ የተሞካሸው ከጉማሬ አጥንት ተጠርቦ የተሠራው የድንጋይ መሣርያ 1.4 ሚሊዮን ዓመታትን ያስቆጠረ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያኑን የሥነ ጥንት ሊቃውንት ዮናስ በየነ (ዶ/ር)  እና ብርሃኔ አስፋው (ዶ/ር) የሚገኙበት የኮንሶ ፖሊዎአንትሮፖሎጂ የጥናት ቡድን የጃፓን ተመራማሪዎችንም አካትቷል፡፡

በአሜሪካ የሳይንስ አካዴሚ ጆርናል (PNAS) ታትሞ የወጣው የግኝቱ ሐተታ እንደሚያመለክተው፣ ከጉማሬ አጥንት ተጠርቦ የተሠራው ጥንታዊ መሣሪያ ‹‹አሹሊያን›› ተብሎ በሚጠራው የድንጋይ መሣሪያ ቴክኖሎጂ ዘመን ልክ በወቅቱ የተሠሩ የድንጋይ መሣሪያዎች የተሠሩበትን የላቀ የአጠራረብ ጥበብ ተከትሉ ተሠርቷል፡፡

በኮንሶ የተገኘው 1.4 ሚሊዮን ዓመታት ያስቆጠረው ከጉማሬ አጥንት የተሠራው ጥንታዊ መሣርያ

ከኮንሶ መካነ ቅርስ የተገኘውና በጉማሬ አጥንት የተሠራው መሣሪያ /Bone Handaxe/ 13 ሳንቲ ሜትር ርዝመትለው ሲሆን፣ መሣሪያው የአጥንቱ የውጭው አካል በዛ ያሉ የመጠረብ አሻራዎች ይታዩበታል፡፡ እነዚህ የመጠረብ ምልክቶች አንዱ ከሌላው ጋር በተከታታይ እንደተጠረቡና በመሣሪያው ጫፍ ፊት ላይ በጥንታቄ መጠረባቸው በግልፅ ይታያል፡፡ ማይክሮስኮፕ በመጠቀም የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው መሣርያው ለመቁረጥና ለመገዝገዝ አገልግሎት እንደዋለ ይጠቁማል፡፡ በዚህ የአጥንት መሣሪያ ስል ጠርዞች ላይ በድንጋይ መሣሪያዎች ላይ የሚታየውን የመሰለ የመፈግፈግና የመጫጫር ምልክቶች መገኘታቸውን ሆኖም መሣሪያውምን አገልግሎት እንደዋለ በእርግጥ አለመታወቁ ተጠቁሟል፡፡

እስካሁን ድረስ በተደረጉ የአርኪዎሎጂ ጥናቶች በጣም ጥቂት የአጥንት መሣሪያዎች ከአፍሪካና ከአውሮፓ ጥንታዊ መካነ ቅርሶች ቢገኙም፣ “KGA13” ተብሎ  በሚጠራው የኮንሶ መካነ ቅርስ ልዩ ቦታ የተገኘው አዲሱ የኮንሶ ግኝት በዕድሜ ልቀትና የቅርሱ ለዚህ ሁሉ ዓመታት በጥሩ ሁኔታ በመቆየቱ፣ የነባሩን አሻራን ይዞ መገኘቱና የላቀ የአሠራር ጥበብ የታየበት በመሆኑ ግኝቱን ልዩ ያደርገዋል፡፡

በኢትዮጵያዊው ዶ/ር ዮናስ በየነና በጃፓናዊው ዶ/ር ጌን ሱዋ የሚመራው የጥናት ቡድን ባወጣው መግለጫ እንደተገለጸው ጥንታዊው መሣርያ ከጉማሬ አጥንት መሠራቱ የታወቀው ባከናወነው ንፅፅራዊ ጥናት ነው፡፡

‹‹ቅርሱ ከየትኛው ትልቅ እንሰሳ፤ ከየትኛው የአካል ክፍል ተጠርቦ እንደተሠራ ለማወቅ የዝሆን፣ የጉማሬ፣ የአውራሪስና ሌሎች ትልልቅ እንስሳት አጥንቶች ላይ ምርምር ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም ከብዙ የንፅፅር ጥናቶች በኋላ ከጉማሬ የታፋ አጥንት የላይኛው ክፍል መሆኑ ተረጋግጧል፡፡››

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ2.6 ሚሊዮን ዓመታት ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ የቅድመ ሰው ዘር አውራሾች በየዘመኑ የተለያዩ ዓይነት የድንጋይ መሣሪዎችን ይጠቀሙ ነበር፡፡ በተለይም 1.75 ሚሊዮን ዓመታት ጀምሮ እስከ 200 ሺሕ ዓመታት ድረስ በነበረው 1.5 ሚሊዮን ዓመታት ጊዜ ውስጥ ‹‹አሹሊያን›› በመባል የሚታወቁ በሁለት ገጽ የተጠረቡ የድንጋይ መሣሪዎች ተሠርተው አገልግሎት ላይ የዋሉ ሲሆን፣ እነዚህን የእጅ መዳፍ ቅርፅ ያላቸው የድንጋይ መሣሪያዎች የሠራቸው ሆሞ ኢረክተስ (Homo erectus) በመባል የሚታወቀው ጥንታዊ የቅደመ ሰው ዘር ነው፡፡ ይህ ዝርያ በኮንሶ መካነ ቅርስ 1.75 ሚሊዮን እስከ 800 ሺሕ ዓመታት በነበሩት ዘመናት ውስጥ ይኖር እንደነበረ መረጋገጡን መግለጫው ያሳያል፡፡

በዚህም ጊዜ ውስጥ አሹሊያን ተብለው ከሚጠሩ የድንጋይ መሣሪዎች በተጨማሪም 1.4 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የጉማሬ የታፋ አጥንት (femur) በመጠቀም ተመሳሳይ የመቁረጫ መሣሪያርተው መጠቀማቸውን የኮንሶው መካነ ቅርስ ግኝት ያመለክታል፡፡

የኮንሶ ፓሌዎአንትሮፖሎጂ መካነ ቅርስ .. 1991 በዶ/ ብርሃኔ አስፋው ይመራ በነበረው የባህል ሚኒስቴር የፓሌዎ አንትሮፖሎጂ ኢንቨንቶሪ ፕሮግራምተገኘ ሲሆን፣ በተከታታይ ዓመታት ባደረጋቸው ጥናቶች መካነ ቅርሱ ከሁለት ሚሊዮን እስከ 800 ሺሕ ዓመታትድሜ እንዳለው ተረጋግጧል፡፡

በመካነ ቅርሱ 12 ሜትር ጥልቀት ያለው የአፈር ውስጥ ሆሞ ኢሬክተስና አውስትራሎፒቲከስ ቦይዚያይ በመባል የሚታወቁ ጥንታዊ የቅድመ ሰው ዝርያዎች ተገኝተው ለኅትመት በቅተዋል፡፡ መካነ ቅርሱን በዓለም ታዋቂ ያደረገው አሹሊያን በመባል የሚታወቁት የድንጋይ መሣሪዎችና በየዘመናቱ ከጥንታዊ ቴክኖሎጂው  ጀምሮ ያለውን የቴክኖሎጂ ለውጥ የተመዘገቡበት መሆኑ ነው፡፡

ጥናቱ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ላቦራቶሪና በጃፓን ቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም መከናወኑን በተለይ በጃፓን የተካሄደውን በማይክሮስኮፕ ቴክኖሎጂ የተደገፈውን ጥናት መሪ ጃፓናዊው / ካትሱሂሮ ሳኖ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የኮንሶ ፓሌዎአንትሮፖሎጂ መካነ ቅርስ፣ ከሰባት ዓመት በፊት 1.75 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠሩ የድንጋይ መሣርያዎች መገኘታቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...