Tuesday, April 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 21.6 በመቶ ማሻቀቡ ተገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

አገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት ቀደም ባሉት ወራት ከነበረበት በመጨመር፣ በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ወደ 21.6 በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የፌዴራል መንግሥት በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. በጀመረው አዲሱ የበጀት ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ አሁን የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋወደ ነጠላ አኃዝ ወይም ወደ ዘጠኝ በመቶ ለማውረድ እንደሚጥር፣ ከሳምንት በፊት አዲሱን የአገሪቱ በጀት በፓርላማ ባስታወቀበት ወቅት መግለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የበጀት ዓመቱ በተጀመረበት በዚህ ወር ያለውን የዋጋ ግሽበት የሚጠቁመው መረጃ ፈጣን የዋጋ ግሽበት አዝማሚያ ከወዲሁ መታየቱን ነው።

የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ለሪፖርተር የላከው ወርኃዊ የሸቀጦች ዋጋ መረጃ እንደሚገልጸው፣ በሰኔ ወር መጨረሻ የተመዘገበው አገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 21.6 በመቶ መጨመሩን ገልጿል።

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በማነፃፀር የሚገኘው ውጤት ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት ሁኔታን እንደሚገልጽ የሚያስረዳው መረጃው በሰኔ ወር የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት፣ ከግንቦት ወር ከነበረው አጠቃላይ የዋጋ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር 2.9 በመቶ እንደጨመረም አመልክቷል።

በተከታታይ ወራት መካከል ያለውን የዋጋ ንፅፅር የአጭር ጊዜ የዋጋ ግሽበት ሁኔታን የሚያመለክት እንደሆነ ይገልጻል።

የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 21.6 ከመቶ ለመጨመሩ ቀዳሚ ምክንያት የሆነው በምግብ ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ወደ 23.1 በመቶ ከፍ በማለቱ ሲሆንበዚህም አብዛኞቹ የእህል ዓይነቶችናአትክልት ጭማሪ ማሳየታቸውን ገልጿል።

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ 19.7 በመቶ ዕድገት ማስመዝገባቸው ሌላው ምክንያት እንደሆነ አመልክቷል፡፡
በዚህ ዘርፍ ለታየው የዋጋ ግሽበት ጉልህ ድርሻ ከያዙት መካከል የቤት ኪራይ፣ የቤት እንክብካቤና የማብሰያ ዋጋ (ማገዶና ከሰል) የቤት መሥሪያ ዕቃዎች፣ ትራንስፖርትና ሕክምና ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ተጠቃሽ ናቸው።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች