Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ ልደቱ አያሌው በተጠረጠሩበት ወንጀል ሐምሌ 20 ቀን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

አቶ ልደቱ አያሌው በተጠረጠሩበት ወንጀል ሐምሌ 20 ቀን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

ቀን:

‹‹ለደኅንነታቸው ብሎ አዲስ አበባ ያመጣቸው የኦሮሚያ ፖሊስ ነው››

ኢዴፓ

በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) ከተማ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረውን ሁከት በማደራጀትና በገንዘብ በመርዳት ወንጀል ተጠርጥረው ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተነገራቸው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራር አቶ ልደቱ አያሌው፣ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ታወቀ፡፡

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተለይ በቢሾፍቱ ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ፣ አቶ ልደቱም ሁከቱን በገንዘብ በመደገፍ መጠርጠራቸውን እንደ ነገሯቸው የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተናግረዋል፡፡

አቶ ልደቱ በቢሾፍቱ የነበረውን ሁከት በገንዘብ ከመርዳታቸው ባለፈ፣ በሁከቱ ስለተፈጸመው የወንጀል ድርጊትና ስለደረሰው የጉዳት ዓይነት እንዳልተገለጸላቸው የተናገሩት አቶ አዳነ፣ አቶ ልደቱ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉበት ሒደትም ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ደውሎላቸው እንደሚፈለጉ ነግሯቸው ወደ ፌዴራል ፖሊስ መሄዳቸውን እንደ ነገሯቸው አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡ በቢሮአቸው የጠበቋቸው የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተጻፈ የመያዥያ ደብዳቤ እንዳሳዩዋቸው፣ ምክንያቱ ደግሞ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ሁከት በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል መጠርጠራቸው መሆኑን ነግረዋቸው ወደ ቢሾፍቱ እየወሰዷቸው እንደሆነ፣ በስልክ እንደገለጹላቸው አስታውቀዋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምርያ ከከተማው ወረዳ ፍርድ ቤት የመያዥያ ትዕዛዝ የወሰደው፣ ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. መሆኑንም አቶ አዳነ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ልደቱ ለበርካታ ዓመታት መኖሪያቸው ከነበረው አዲስ አበባ ከተማ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ቢሾፍቱ በመቀየር፣ አዲስ በገነቡበት ቤት እየኖሩ እንደነበርም አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡ የድምፃዊ ሃጫሉ ሞትን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሁከት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ቤታቸውን ፖሊስ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቦ ሲጠብቅ ካደረ በኋላ፣ በማግሥቱ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ‹‹ለደኅንነትህ›› በማለት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዳመጣቸውም አስረድተዋል፡፡

አቶ ልደቱ ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አበባና በሰሜን ወሎ ላሊበላ ከተማ ልዩ መጠሪያው ‹‹መካነ ልዕልት›› በሚባለው ሥፍራ፣ ከ12 ጓደኞቻቸው ጋር እየገነቡት ያለውን የሪዞርት ፕሮጀክት ለማየት ሄደው እዚያው ቆይተው ሐምሌ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. መመለሳቸውን አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...