ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙርያ በፋና ቴሌቪዥን በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የተናገሩት፡፡ አገሪቱ ከለውጥ ጋር በተያያዘ ፈተና ውስጥ መሆኗን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አንዱ ችግር ነው ብለው ያነሱት በብልፅግናና በሕወሓት መካከል ያለው ግንኙነት መለያየት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል የተፈጠረው ክፍተት በትዕግሥት በመነጋገር ችግሮቹ እንደሚፈቱ እምነታቸው መሆኑን ሳያወሱ አላለፉም፡፡