Friday, March 1, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

‹‹ለውጡን ተቀብለን …››

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ለማሻሻል ያላቸውን አቅም በማቀናጀት የተሻለ አስተዋጽኦ ማድረግ መቻላቸውን ታሳቢ በማድረግ የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ አክሲዮን ማኅበርና የግዥ አገልግሎት ድርጅት 2008 .. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 እና የልማት ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሠረት ተዋህደው ‹‹የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሚል ስያሜ የኢትዮጵያን የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት ችግር ለመፍታት መቋቋማቸው ይታወሳል፡፡ 

የኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው ይህ ጽሑፍ መነሻ የተቋማቱን ምሥረታ ሒደት ለማስታወስ ሳይሆን፣ ሪፖርተር ጋዜጣ ሰኔ 28 ቀን 2012 .. በአስተያየት ዓምዱ ‹‹አልለወጥም ወይስ ለውጡን አልቀበልም?›› በሚል ርዕስ በአቶ ሞቱማ ወልተጂ ለቀረበው ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡ በአንጋፋነቱ ይታወቅ በነበረው  በኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት ነባር ሠራተኛ ስለነበርንና አሁንም በኮርፖሬሽኑ ስለምንሠራ ጸሐፊው በሞቱማ ወልተጂ ስለኮርፖሬሽኑ ከአንድም ሁለቴ በጻፉት ሐሳቦች ላይ በአብዛኛው ቅሬታ ስላለን እንደሳቸው የቃል መረጃና የሰዎችን አስተያየት አሰባስበን ሳይሆን፣ በኮርፖሬሽኑ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ሪፖርት ተደርገው  ለሚመለከታቸው አካላት በሕጋዊነት ከተላኩ የጽሑፍ መረጃዎች ካገኘነው እውነታዎች በመነሳት ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ተጠቅመው ለኮርፖሬሽኑ ዕድገት ተቆርቋሪ በመምሰል የመሰላቸውን የጻፉት ሞቱማ ወልተጂ ከሦስት ዓመት በፊት ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት በአማካሪ ድርጅት ስለተጠናው ጥናትና በአጠቃላይ ለአንድና ለጥቂት ሰዎች ተብሎ እንደገና ሊደራጅ ስለማይችለው የኮርፖሬሽኑ መዋቅር ጥናትና አመዳደብ እየደጋገሙ መናገር ለምን አስፈለገ? ይልቅስ  ትኩረታቸው የቅርብ ሰው ነኝ እንዳሉት ኮርፖሬሽኑ በኮቪድ-19 የደረሰበትን አገራዊና ተቋማዊ ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ በወጪ ንግዳችን የቡና፣ ቅባት እህልና ጥራጥሬ ተቀባይ አገሮች በወረርሽኙ ምክንያት መቀነሳቸው  በዋጋ ረገድም ወጪን ሸፍኖ ወደ ውጭ አገሮች ለመሸጥ በማያስችል ዝቅተኛ ደረጃ ስለመድረሱ፣ የእህል አቅርቦት መቀነስና የዋጋ መጨመር የመሠረታዊ ፍጆታ ሸቀጦችም የዋጋ ንረትና የምርት እጥረት በሸማቹ ኅብረተሰብ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ የማረጋጋት ሥራ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠሩ ኮርፖሬሽኑ ኃላፊነቱን  እንዴት ተወጣው?

በአዲስ አበባና በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ባሉ የግብይት ጣቢያዎች ለኅብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት  ሳይቋረጥ አገልግሎቱን ለመስጠት የሠራተኛውን ደኅንነት ለመጠበቅ የንፅህና መስጫ ግብዓቶችን በማቅረብ ሠራተኛውን ለማመላለስ ለተሸከርካሪ እጥፍ የነዳጅ ወጪ በማውጣቱ፣  ለተጨማሪ ሰርቪሶች ኪራይ ወጪ ችሎ እንዴት ትርፋማ ሆነ? ከእህል፣ የፍጆታ ዕቃዎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ በተጨማሪ  የሲሚንቶ መግዣ ዋጋ ንረትን ለማስተካከል ሲሚንቶ የማከፋፈል ኃላፊነት እስከ ክልሎች ድረስ ተሰጥቶታልና ገበያን የማረጋጋትና ሸማቹን ኅብረተሰብ የመደገፍ ሥራዎች ተሳክቶለታል? ገበያውን ይበልጥ ለማረጋጋት እንዲህ ቢያደርግ ይሻል ነበር? ወደ ፊትስ ምን አቀደ? ቢሉን ይሻል ነበር፡፡

 

በመሠረቱ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተልዕኮ ትርፍ ሳይሆን ለአምራቹ የገበያ ዕድል መፍጠርና አምራቹ ያመረተው ምርት ዋጋና ተቀባይ ሲያጣ ምርቱ ካለበት ቦታ ድረስ በመሄድ ለአምራቹ ተገቢውን ዋጋ ሰጥቶ የምርት እጥረትና ዋጋ ውድነት ለገጠመው ሸማች በተመጣጣኝ ዋጋ  ያቀርባል፡፡ ለዚህ ምሳሌ  በትራንስፖርት ርቀት ላይ ለሚገኙ የነቀምት አካባቢ ገበሬዎች የበቆሎ ምርታቸውን በተሻለ ዋጋ እየገዛ ወደ ማዕከል ማሰባሰቡ ከአዲስ አበባ 900 ኪሎ ሜትር ድረስ በመሄድ ምርታቸው ገበያ ላጣ የአርባ ምንጭ የሙዝ ተክል አምራቾች ያመረትነው ካሮት ሊበሰብስብን ነው ላሉ የደብረ ብርሃን አርሶ አደሮች ባመረቱት ምርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሠራ ያለው ችግር ፈቺነቱና ተደራሽነቱ ባለፉት ወራት ከተሠሩት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ 

 

2011 በጀት ዓመት መጨረሻ ኮርፖሬሽኑ ከነበረው የትርፍ ኪሳራ እንዴት አንሰራራ? ለሚለው እንደ ኮርፖሬሽን  ከተዋሃዱት ተቋማት የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት (አለ በጅምላ) 2006 .. በአዋጅ ሲቋቋም፣ ለካፒታልና ሥራን ለማስኬጃ በመንግሥት ከተፈቀደለት ብር 596 ሚሊዮን ብድር ለውጭ አማካሪ ድርጅት የተከፈለውን እስከ 256 ሚሊዮን ብር ዕዳ ድርጅቱ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ከተዋሃደ በኋላ የመነገጃ ካፒታል እጥረት ቢኖርም ተከፍሏል፡፡

2012 በጀት ዓመት  የፍጆታ ዕቃዎች ንግዳችንም ወደ አትራፊነት መሸጋገሩና  በአትክልትና ፍራፍሬ ንግዳችንም ላይ የምርቱ ባህሪ ቶሎ ለብልሽት የሚጋለጥ በመሆኑ ዘመናዊ የመሸጫ ሱቆች በመሥራትና  በሌሎች  የአሠራር ለውጦች በምርት ግብይቱ ላይ በተፈጠሩ መሻሻሎችና  የገበያ መዳረሻዎች በመስፋታቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ግብይት  የበለጠ ትርፋማ ሆኗል፡፡ በተለይ ሀብትንና አሠራርን አቀናጅቶ መጠቀም የመዋሃዳቸው ዋና ዓላማ በመሆኑ፣ የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ቀድሞ የነበረው  የመነገጃ ካፒታል የመገበያያ ማዕከላት፣ መጋዘኖች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ትላልቅ ተሽከርካሪዎች  ለኮርፖሬሽኑ መጠናከርና ማትረፍ ዋነኛ ምንጭ ናቸው፡፡ 

2011 በጀት ዓመት መጨረሻ ኮርፖሬሽኑ ከትርፍ ኪሳራ የመውጣቱ መነሻ ነጥቦችን ስንዘረዝር፣ ከላይ ከተጠቀሱት ሐሳቦች በተጨማሪነት በኮርፖሬሽኑ መቋቋሚያ አዋጅ ከተሰጠው ከቀዳሚ ተልዕኮዎቹ ባሻገር በአዋጁ ገቢ ለማስገኘት  የሚያስችሉት  ተጓዳኝ ሥራዎች የትርፍ ምንጭ  ናቸው፡፡  ጸሐፊው በትርፉ ላይ የሚያሳስባቸው ነገር ካለ ሐሳቡን ለኦዲተሮች እንተውላቸው፡፡  

ወደ ግዥና ማማከር አገልግሎት ስንመጣ፣ የኮርፖሬሽኑ ችግር  በለቀቁት ዘርፍ ኃላፊ ምትክ በሚመደበው አመራር ላይ ሳይሆን፣  በዋነኝነት  በግዥ ዙሪያ የሚሰጡ ሥልጠና የአገልግሎቶችን  ከኢትዮጵያ የንግድ ሥርዓት መዘመን ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ ሥልጠና የሚሰጡ ተቋማት በመበራከታቸው ነው፡፡ በውጭ የጥቅል ግዥ አገልግሎትን በውክልና ማስገዛት የሚፈልጉ ተቋማት በራሳቸው አቅም መሥራት መጀመራቸውም የግዥና ማማከር አገልግሎትን ትርፋማ ሊያደርገው አልቻለም፡፡ በመሆኑም  የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አመራሮች በአገልግሎቱ ላይ ጥናት እንዲደረግ በሰጡት አመራር መሠረት  በቅድሚያ የገበያ ችግሩን ለመፍታት  እየተሠራ በመሆኑ  የኃላፊ ምደባ ዘግይቷል፡፡ 

ከዚህ ጋር በተያያዘ  የግዥና ማማከር አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ከአራት ወራት በፊት ባቀረቡት የሥራ መልቀቂያ በመሰናበታቸው፣ በውክልና በሚሠሩት ኃላፊ ላይ የሰነዘሩት ነቀፋ ትክክል አይደለም፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት በተዋሃደው  የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት አብሮ የመሥራትና በቅርበት የማወቅ አጋጣሚው ስላለን ብቃታቸውን አስመልክቶ እርስዎ እንዳሉት ሳይሆን በኃላፊነት ደረጃ ብዙ ልምድ ያላቸው፣ ከሙያ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ያጣነውን የግዥና ማማከር አገልግሎት  ገበያ  ለመፍታት፣ በቀጣይ በኮቪድ-19 ምክንያት ልንሰጥ የማንችላቸውን የሥልጠና አገልግሎቶች  ከደንበኞች ጋር በመነጋገር  በአዳዲስ አሠራሮች ለመተካት ብዙ ጥረት እያደረጉ ያሉ ናቸው፡፡ 

አስተያየት አቅራቢው እየመላለሱ የሚያነሱት ሐሳብ በውጭ አካል ተጠንቶ ከሦስት ዓመት በፊት ተግባራዊ የተደረገውን የአመራርና ሠራተኞች ምደባ ነው፡፡ ከፍተኛና መካከለኛና የሥራ አመራሮችን ጨምሮ አብዛኛው የማኔጅመንት አባላት ለቦታው ብቁ አይደሉም ብለዋል፡፡ እኛ ግን አመራሩ ብቁ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ እየተንቀሳቀስና ትርፋማ እየሆነ መምጣቱን ታዝበናል፡፡ አላሠራ ያለና መስተካከል ያለበት አደረጃጀት ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ መስተካከል አለበት ያሉትን የምንስማማበት ሲሆን፣ በኮርፖሬሽኑም በኩልም ይህ እየተተገበረ መሆኑን ልንገልጽልዎት እንወዳለን፡፡  

በሌላ በኩል የኮርፖሬሽኑን አሠራር የማስተካከል፣ የበላይ አመራሮችን  የመሾምና  የማውረድ ሥልጣንና ኃላፊነት ስለተሰጣቸው የቦርድ አመራሮች ስለተደረጉ የአመራር ለውጦችና ሹመት በጻፉት አስተያየት ላይ የተገለጹት እውነታነት የላቸውም፡፡ እንደ እኛ ሐሳብ አመራሮች ከተሾሙ ሁለት ወራትን ሳያስቆጥሩ አመራርነታቸውን መተቸት መቸኮል ስለሚሆን  ለአመራር ጊዜ መስጠቱ የተሻለ ነው፡፡ የመንግሥት የሥራ ሰዓትን ሳይበድሉ ተጨማሪ ሥራዎችን መሥራት በኢትዮጵያ ሕግ የተከለከለ ባይሆንም፣ ከአሥር ዓመት በፊት ተመልሶ የነበረ የንግድ ፈቃድን አስታውሶ በኦፕሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተሾሙት ኃላፊ ስም የተቋቋመ የንግድ ድርጅት መኖሩን መግለጹ፣ የጸሐፊው አስተያየቶች ባልተጣሩ መረጃዎች የታጀበ መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ 

ጸሐፊው የሐሰትን ካባ አጥልቀው ባልጠራ መረጃ ለኮርፖሬሽኑ ተቆርቋሪ ለመምሰል ያደረጉት፣ በሠራተኛውና በአመራሩ መካከል ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነት ለማሻከር ካልሆነ በስተቀር ዕውን ለኮርፖሬሽኑ ተቆርቋሪ ከሆኑ ጉዳዩን ከሚመለከታቸውኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራሮች   ጋር ቀርበው ቢነጋግሩ በቂ ምላሽ  ያገኙ ነበር፡፡

ከአዘጋጁጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡ 

spot_imgspot_img
- Advertisment -

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

Related Articles