Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየኢዜማ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ

  የኢዜማ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ

  ቀን:

  ነዋሪነቱ ድሬዳዋ ነው የተባለ ‹‹አክቲቪስት›› በዋስ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ተሰጠ

  ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ አምስት ኪሎ አካባቢ ከ70 እስከ 100 የሚደርሱ ወጣቶችን በማደራጀት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት የኢዜማ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሒሩት ክፍሌ፣ በስድስት ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

  የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ማክሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ አባል በተሰጠው ስምንት የምርመራ ቀናት የሠራውን ገልጿል፡፡ በዚህም የምስክሮችን ቃል መቀበሉን፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች የምርመራ ውጤት የሰነድ ማስረጃ መቀበሉን፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ድርጅቶች ደብዳቤ መጻፉን፣ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየሠራ መሆኑን አስረድቷል፡፡

  ቀሪ ምስክሮችን መስማት፣ የደረሰውን ጉዳት እንዲገልጹለት ደብዳቤ የጻፈውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍላተ ከተሞች ምላሽ መሰብሰብ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ምስክርነት ቃል መቀበል እንደሚቀረው በማስረዳት ተጨማሪ 14 የምርመራ  ቀናት እንዲፈቀዱለት ጠይቋል፡፡

  የሒሩት ጠበቆች የመርማሪ ፖሊሱን ሪፖርት በመቃወም ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ መርማሪው ቀደም ብሎ በነበረው የጊዜ ቀጠሮ በተሰጠው ትዕዛዝ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የመጨረሻ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ምርመራው አንድ ወር እንዳለፈው፣ ደንበኛቸው ሳይታሰሩ 14 ቀናት ምርመራ ማድረጉንና ለሦስት ተከታታይ ቀጠሮ ተጨማሪ ጊዜ እንደተሰጠው በማስታወስ፣ ይህ የተጠርጣሪዋን ሰብዓዊ መብት የሚነካ፣ ከጤናቸውና ኮሮና እያሳደረው ካለው ተፅዕኖ አንፃር ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ ደብዳቤ ለመቀበል የደንበኛቸው መታሰር የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ጠቁመው፣ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዓይቶና መርምሮ በመዝጋት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን በማክበር እንዲዘጋላቸው ጠይቀዋል፡፡

  ፖሊስ በሰጠው ምላሽ ሒሩት የተጠረጠሩበት ወንጀል የሰው ሕይወት የጠፋበት፣ በርካታ ንብረት የወደመበትና ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን አስረድቶ፣ ዋስትናው ውድቅ ተደርጎ የጠየቀው ጊዜ እንዲፈቀድለት አመልክቷል፡፡

  ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ ተጠርጣሪዋ አድርሰውታል ከተባለው ጉዳት አንፃር የሰውም ሆነ የሰነድ በርካታ ማስረጃ ማሰባሰብ መቻሉን፣ የምርመራ መዝገቡ እንደሚያሳይ ገልጿል፡፡ ነገር ግን ተጠርጣሪዋ በዋስ ቢወጡ ምስክሮችን ሊያባብሉና ማስረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ የሚለው አሳማኝ አለመሆኑን ጠቁሞ፣ የተሰጠው ጊዜ በቂ በመሆኑ ተጠርጣሪዋ የስድስት ሺሕ ብር ዋስ አስይዘው ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡

  በተመሳሳይ ችሎቱ የቀረበው ተጠርጣሪ ደግሞ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ተጠርጣሪ ገዳዮች ጋር ግንኙነት አለው የተባለና የስልክ ልውውጥ ሲያደርግ እንደነበርና ሃጫሉ የሞተ ቀንም ሳይቀር ከራሱ ከሃጫሉ ጋር መደዋወሉ በመርማሪ ፖሊስ ሲገለጽ የነበረው፣ የድሬዳዋ ነዋሪና ‹‹አክቲቪስት›› መሆኑ የተገለጸው አቶ ዮናታን ሰቀታም በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

  ተጠርጣሪው በፖሊስ ታጅቦ ፍርድ ቤት የቀረበ ቢሆንም መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው የምርመራ ጊዜ ውስጥ በአግባቡ መርምሮ መቅረብ ባለመቻሉና አሳማኝ ምክንያት ባለማቅረቡ፣ ተጠርጣሪው በሰባት ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቅ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...