Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበህዳሴ ግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር በአፍሪካዊ መንፈስ እንዲቀጥል ደቡብ አፍሪካ ጥሪ አቀረበች

  በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር በአፍሪካዊ መንፈስ እንዲቀጥል ደቡብ አፍሪካ ጥሪ አቀረበች

  ቀን:

  በአፍሪካ ኅብረት ሥር የህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌትና አስተዳደርን በተመለከተ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሚያደርጉትን ድርድር እየመራች የምትገኘው የኅብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ፣ አገሮቹ ድርድሩን በአፍሪካዊ መንፈስ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረበች።

  የኅብረቱ ሊቀመንገበር የሆኑትን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በመወከል የደቡብ አፍሪካ የውጭ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናልዲ ፓንደር ሰሞኑን ባወጡት መግለጫ አገሮቹ ወደ ድርድሩ እንዲመለሱ ያሳሰቡ ሲሆንድርደሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ጠቅሰው በአፍሪካዊ መንፈስናወንድማማችነት ተቀራርበው ድርድሩን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

  ደቡብ አፍሪካ ጥሪውን ያቀረበችው ሦስቱ አገሮች ባለፈው ሳምንት በተግባቡት መሠረት ድርድሩን በቴክኒክ ባለሙያዎች ማካሄድ በጀመሩበት መድረክ ላይ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን የውኃ ሙሌትና አስተዳደር አስመልክቶ ያዘጋጀችውን የቴክኒክ ሰነድ ለሁለቱ አገሮች የባለሙያዎች ቡድን ካቀረበች በኋላ፣ ግብፅና ሱዳን የኢትዮጵያን ሰነድ ለመመርመር ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ ድርድሩ ለተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥማድረጋቸው ነው።

  ከዚህ ባለፈም ግብፅና ሱዳን ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የቴክኒክ ሰነድ እንደማይቀበሉ የሚገልጹ መግለጫዎችን በተናጠል እያወጡ ስለሆነና ወደ ድርድሩ ላይመለሱ እንደሚችሉም ፍንጭ እየሰጡ መሆናቸው፣ ደቡብ አፍሪካ መግለጫውን ለማውጣት ምክንያት ሆኗታል።

  የሱዳን የውኃና መስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ አገራቸው ወደ ድርድሩ ለመመለስ እንደምትቸገር ሰሞኑን ለሚዲያዎች የገለጹ ሲሆን፣ በምክንያትነት የጠቀሱት ደግሞ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር ወደ ሁሉን አቀፍ የውኃ ክፍፍል እንዲያመራ እያደረገች ነው የሚል ነው።

  ግብፅና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ድርድር በውኃ ሙሌት በዋነኝነት በተራዘመ ድርቅ ወቅት የግድቡ አስተዳደርን መወሰን በማለት፣ ኢትዮጵያ ወደፊት በዓባይ ውኃ ላይ የሚኖራት የውኃ አጠቃቀም በዚህ ድርድር እንዲካተት ይጠይቃሉ።
  ኢትዮጵያ በበኩሏ የወደፊት የዓባይ ውኃ አጠቃቀም በማንም ፈቃድ ላይ የሚመሠረት እንደማይሆን ፅኑ አቋም የያዘች ስለሆነ፣ የወደፊት የውኃ አጠቃቀም ከተነሳ ሁሉንም የዓባይ ተፋሰስ አገሮች የሚመለከት የውኃ ክፍፍል ስምምነት መደረግ አለበት ብላለች፡፡ ወደዚህ የሚገባ ከሆነ ደግሞ ሌሎቹ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ... 2010 የፈረሙት፣ ነገር ግን ግብፅና ሱዳን ረግጠው የወጡት የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ዶሴ የሚከፍትባቸው ይሆናል።

  በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት የተጀመረው ድርድር ሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ዳግም ይጀመራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ግብፅና ሱዳን በተለያዩ ሚዲያዎች እየሰጡ ካለው መግለጫ አንፃር ወደ ድርድር የመመለሳቸው ጉዳይ ጥርጣሬ አጭሯል።
  ከዚሁ ጎን ለጎን የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለማድረግ እየሞከረ ሲሆን፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኢትዮጵያ በድርድር ወደ ስምምነት ለመምጣት የሚያስችላት ጊዜ እየረፈደ ነው የሚል መግለጫ ሰሞኑን ማውጣቱ ይታወሳል።

  ይህ መግለጫም ሦስቱ አገሮች በድርድሩ ስምምነት መድረስ ያልቻሉት በኢትዮጵያ አቋም ምክንያት እንደሆነ የሚያመላክት ገጽታ በመስጠት፣ ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ የመክተት አዝማሚያን ይዟል።

  ኢትዮጵያ በበኩሏ ማንኛውም ኃይል ህዳሴ ግድቡን ዕውን ከማድረግ እንደማያግዳት፣ ነገር ግን የትኞቹንምተፋሰስ አገሮች ፈፅሞ እንደማትጎዳና በድርድሩ አማካይነት ወደ መፍትሔ መምጣት እንደሚቻል አበክራ እየገለጸች ነው።

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...