Thursday, June 8, 2023

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ድጋፍ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከእድሮችና ከወጣት ማኅበራት ጋር በመተባበር በኮቪድ-19 ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን እየረዳ ይገኛል፡፡ ማኅበሩ ነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት በመገኘት የዓይነት ዕርዳታ የለገሰ ሲሆን፣ 492 ሰዎችም የዕርዳታው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ማኅበሩ 24ሺሕ በጎ ፈቃደኞችን በማሰማራት ኅብረተሰቡ ራሱን ከቫይረሱ እንዲከላከል የሚያስችለው የጤና ሕጎችን እንዲተገብር፣ ራሱን እንዲጠብቅ እየሠራ ሲሆን፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችን በመመገብ፣ ለችግረኞች ደግሞ የገንዘብና የምግብ ድግፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ ከኔዘርላንድ መንግሥት በተገኘ 1.6 ሚሊዮን ብር ከአዲስ ከተማ፣ ከቂርቆስ እንዲሁም ከልደታ ክፍላተ ከተሞች ለተውጣጡ ከ7,000 በላይ ቤተሰቦች የምግብ ዕርዳታ እንደሚደረግም ማኅበሩ ገልጿል፡፡ 

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ድጋፍ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ድጋፍ

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -