አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 440 ደርሷል
ከግማሽ ሚሊዮን ምርመራ ውስጥ ከ24 ሺሕ በላይ በቫይረሱ ተይዘዋል
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አስመልክቶ የጤና ሚኒስቴር ነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም. በለቀቀው ዕለታዊ መረጃ፣ በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 11,881 የላቦራቶሪ ምርመራ 584 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 24,175 መድረሱንና 20 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈው ቁጥርም 440 ደርሷል።
እስከ ነሐሴ 5 ቀን ድረስ ለ520,891 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፣ በቫይረሱ የተያዙትም 24,175 ሆኗል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 10,696 ሲደርስ፣ 190 ሰዎች በፅኑ ሕሙማን ሕክምናቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውም ታውቋል።
ኮቪድ-19 በወረርሽነት ዓለምን ካካለለ ዘጠኝ ወር ሆኖታል፡፡ በእነዚህ ወራት ሕዝበ ዓለም ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቅ፣ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ እንዳይያዝ የጤና ባለሙያዎችና ዓለም አቀፋዊም ሆነ አገራዊ ተቋማት ማስገንዘቢያዎችን ከመስጠት ችላ ያሉበት ጊዜ አልነበረም፡፡
ኮቪድ-19 የሚተላለፍበት መንገድ አስመልክቶ እስካሁን ያለው አቋም፣ በሽታው ከሕመምተኛው አፍንጫ ወይም አፍ በሚወጣ ጥቂት ፈሳሽ አማካይነት የሚተላለፍ መሆኑ ነው፡፡ ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ሲያስነጥስም ሆነ ሲተነፍስ ወደ ሌሎች ከማስተላለፍ ባለፈ፣ ከሕሙማን የሚወጣ ፈሳሽ ያረፈበትን ቦታ የነኩ ሰዎችም በበሽታው በቀላሉ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ከሰዎች ጋር ያላቸው ቅርርብ ከአንድ ሜትር በላይ መሆን አለበት የተባለውም በሽታው በትንፋሽ ስለሚተላለፍ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩት ቫይረሱ በአየር ውስጥ ሳይሆን በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች የመተንፈሻ አካላት ከወጡ ፍሳሾች ጋር በሚኖር ንክኪ ብቻ የሚተላለፍ መሆኑን ነው፡፡
ይሁን የቅርብ መረጃዎች የኮሮና ቫይረስ በአየር ላይ የመተላለፍ ዕድሉ ሰፊ መሆኑ እየገለጹ ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት በቫይረሱ የመጋለጥ ወይም ያለመጋለጥ ዙርያ የቀረቡ ጥናቶች ላይ እየመከረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በአየር ላይ ቫይረሱ በመቆየት ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ስለሚችል ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
ተተኳሪ ጉዳዮች
የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት አገላለጽ፣ ኮሮና ቫይረስ የተለያዩ የቫይረስ ዓይነቶችን የያዘ የቫይረስ ቤተሰብ ነው፡፡ ይህ ቫይረስ በሰዎችና በእንስሳት ላይ በሽታን ያስከትላል፡፡ በሰዎች ላይ የሚከሰተው ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በመጉዳት ከተራ ጉንፋን እስከ ከፍተኛ የመተንፈሻ አካል ችግር የሚያደርስ ነው፡፡
በሽታው በጠናባቸው ታማሚዎች ላይ ደግሞ እንደ ሳንባ ምች (ኒሞኒያ)፣ ከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም የሚያሳይ ሲሆን የኩላሊት ሥራ ማቆምና ሞትን ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡
ኅብረተሰቡ ከዚህ በፊት ማንኛውንም በሽታ ለመከላከል ሲጠቀምባቸው የነበረውን የበሽታ መከላከያ መንገዶች ችላ ሳይልና ሳይደናገጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ያስተላለፈው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ቀጥለው የተዘረዘሩትን መልዕክቶች እንዲተገበሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
-
-
-
- ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ ዕርምጃ ርቀት ያህል መራቅ፣
- እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ ዓይንና አፍንጫዎን አይንኩ
- ከሰዎች ጋር አይጨባበጡ፣
- እጅን በንፁህ ውኃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
- ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የሕመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
- በሚያነጥሱበትና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣
- የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
- በሥራ ቦታ፣ በትራንስፖርትና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
- መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገርና ፍርኃት ይከላከሉ!
- በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ አገሮች የሚመጡ ሰዎች ወይም ንክኪ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ራሱን ለ14 ቀን በመለየት በበሽታው አለመያዛቸውን ሲያረጋግጡ ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እንመክራለን::
-
-
ከኮሮና ቫይረስ እንዴት እንጠበቅ?
- አንድ ሰው ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ አለው ሲባል በኮሮና ቫይረስ የታመመ ሰው ምልክቱን ማሳየት ከመጀመሩ ሁለት ቀናት በፊት በአንድ ሜትር ርቀት ውስጥ ሆኖ ከአሥራ አምስት ደቂቃ በላይ ቆይታ ሲኖራቸው ነው፡፡
- በተጨማሪም የግል የጤና መከላከያ መሣሪያዎችን ሳይጠቀሙ በበሽታው የተያዘን ሰው እንክብካቤ ሲያደርጉ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በበሽታው መታመማቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች በመለየት በጤና ባለሙያዎች ለ14 ቀናት ክትትል ይደረግላቸዋል፡፡
- በአገራችን ማኅበራዊ ግንኙነታችን፣ የአኗኗር ባህላችን የጠነከረ በመሆኑ በአብዛኛው የምንጠቀማቸው ቁሳዊ ነገሮች በጋራ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ አኳያ አንድ በቫይረሱ የታመመ ሰው ነገር ግን መታመሙ በሕክምና እስከሚረጋገጥ ድረስ ከሰዎች ጋር ከሚኖረው ንክኪ በተጨማሪ የሚጠቀምባቸው መገልገያዎች ሌሎችም ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ ቫይረሱ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው እንዲተላለፍ ያስችለዋል፡፡
- በሽታው በሳልና በማስነጠስ ወቅትና ከታማሚ ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ፣ ባልታጠበ እጅና በመሳሰሉት ይተላለፋል፡፡
በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ አገሮች የሚጓዙ መንገደኞች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች
- የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣
- እጅን በሳሙናና ውኃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ካደረጉ፣
- ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣
- ምክንያቱ ባልታወቀ በሽታ በታመሙም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ
በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች
- ወደ አገር በተመለሱ በ14 ቀናት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ሕመም፣ ትኩሳትና እንደ ሳል ያሉ የሕመም ምልክቶች ካሳዩ፣ በተጨማሪ የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አሥራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገሮች ሄደው ከነበረ፣ በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገሮች ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ እንዲሁም የበሽታውን ምልክት ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ በአስቸኳይ በ8335 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ሪፖርት ያድርጉ፡፡
- በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ ወይም በሶፍት መሽፈን፣
- አፍና አፍንጫን ለመሽፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድና እጅን ሁል ጊዜ በውኃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡
ኅብረተሰቡ በሽታው በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ሳይዘናጋ የሚተላለፉ መልዕክቶችንና መከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች በሚያገኝበትም ወቅት በተዘረጉ የነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል እንዲያሳውቅና የበሽታውን ሥርጭት በመቆጣጠር በኩል የድርሻውን እንዲወጣ አሳስቧል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፣ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜይል አድራሻ [email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡
በተጨማሪም ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ሥርጭት እንዲከላከል ኢንስቲትዩቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ኅብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር አሳስበዋል፡፡ ሁለቱም ተቋማት ዕለት ዕለት በሚደረገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በበሽታው መያዝን የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ፣ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ‹‹መ›› ሕጎች በመተግበር የበሽታውን ሥርጭት ሁሉም እንዲከላከል በጥብቅ አሳስበዋል፡፡
አራቱ የ‹‹መ›› ሕጎች
- መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
- መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
- መቆየት፡ አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
- መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ11 ሺህ 39 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 773 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባወጡት መረጃ ባለፉት 24 ሰአታት የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት 205 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይም 10 ሺህ 411 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
እንዲሁም 164 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን ለ509 ሺህ 10 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 23 ሺህ 591 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 10 ሺህ 411ዱ ያገገሙ ሲሆን 12 ሺህ 758 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል፡፡
እንዲሁም 420 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 15 ሺህ 834 መድረሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በመዲናዋ እስከዛሬ ለ289 ሺህ 794 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 15 ሺህ 834 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 591 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 446 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ10 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 5 ከአስከሬን ምርመራ 5 ደግሞ ከጤና ተቋም መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል፡፡
- በ24 ሰአት ውስጥ በየካ ክፍለ ከተማ 50 ሰዎች በኮቪድ 19 ተይዘዋል።
++++++++++++
ባለፉት 24 ሰአታት በየካ ክፍለ ከተማ 50 ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን በድምሩ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሽህ 537 ደርሷል።
በቫይረሱ ስርጭት ክፍለ ከተማው ቦሌን ፥ ጉለሌንና አዲስ ከተማን ተከትሎ በ4ኛ ደረጃ ይገኛል።
በቦሌ 2332 ፥ በጉለሌ 1967 ፥ እንዲሁም በአዲስ ከተማ 1762 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
በመዲናዋ በዛሬው እለት ብቻ 446 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ እስካሁን ከተደረገ 289 ሽህ 794 የላቦራቶሪ ምርመራ 15 ሽህ 834 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
The first Physician died in Ethiopia while treating Corona Virus Victims.
D/r Fissehaye Alemeseged( Axum University Medicine and Health Department)
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ማኅበረሰብን እያገለገለ በኮሮና የሞተ ዶ/ር!!! የአክሱም ዩንቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ፋካሊቲ መምህር ዶ/ር ፍስሃየ አለምሰገድ