Tuesday, July 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጥብቅ እንዲተገበር ጥሪ የቀረበበት መድረክ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጥብቅ እንዲተገበር ጥሪ የቀረበበት መድረክ

ቀን:

‹‹የወረርሽኙ ዕለታዊ ሪፖርት በተሻለ በዝርዝርና በሚያስተምር መልኩ መቅረብ ይኖርበታል››

የጤና ማኅበራት

በሔለን ተስፋዬ

በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል በሚያዝያ ወር መተግበር የጀመረው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም፣ በመጀመሪያዎቹ ወራት ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ የአዋጁን አፈጻጸም የሚመረምረው ቦርድም በየጊዜው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለተቋቋመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ ያቀርባል፡፡

በቦርዱ ምልከታ በዝግጅት ምዕራፍ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ አደረጃጀቶችን በአጭር ጊዜ ማቋቋሙ ይገኝበታል፡፡ ይሁን እንጂ በማኅበረሰቡ ዘንድ መዘናጋቶች መኖራቸው በድንበሮች አካባቢ የቁጥጥር ሥርዓት አለመኖሩ ታይቷል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጥብቅ እንዲተገበር ጥሪ የቀረበበት መድረክ

 

በሌላ በኩል የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት እየጨመረ ቢመጣም በኅብረተሰቡ እየታየ ያለው የመከላከያ መንገዶች አተገባበር እየቀነሰና ተከታታይነት እያጣ መሆኑ ዋጋ ስለሚያስከፍል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጥብቅ ተግባራዊ መደረግ አለበት በማለት የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ማኅበራት ያሳስባሉ፡፡ ይህን ማሳሰቢያ በተለያየ ዘርፍ የተደራጁ አሥራ አንድ የጤና ሙያ ማኅበራት ሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በቅንጅት በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

ማኅበራቱ በቀጣይ የሚከናወነውገራዊ የኮቪድ-19 ምርመራ ዘመቻ በቫይረሱ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ሊያስገኝ ስለሚችል፣ መለስተኛ ወይም ምንም የበሽታውን ምልክት ያላሳዩ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ የሚደረግበት ሥርዓት በጥንቃቄ እንዲመራ ጠይቀዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስገዳጅ የነበረው ነገር ግን ከጊዜ በኋላ መቀዛቀዝ የታየበት የሕዝብ መሰባሰብ ዋጋ እንዳያስከፍል ትኩረት እንዲያገኝም በአፅንዖት አሳስበዋል።

ከማኅበራቱ መካከል የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር ዋና ዳይሬክተር ዓለማየሁ መኰንን (ዶ/ር)፣ ኅብረተሰቡ ያለበትን ወቅት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ጥንቃቄ የሚደረግበት መሆኑን ተገንዝቦ ከዚህ ቀደም ሲተገበሩ የነበሩት የመከላከያ መንገዶች አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በኅብረተሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ገልጸው መለስተኛ ወይም የበሽታው ምልክት የማያሳዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በቤታቸው ተወስነው ራሳቸውን እንዲያገሉ የሚደረገው አማራጭ በጥንቃቄና በሥርዓት እንዲተገበርም መክረዋል፡፡

በየቤታቸው በሚቆዩበት ወቅት ተገቢ መረጃና የጤና ክትትል የሚያገኙበት መንገድ መኖር እንዳለበትም ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡

ለተጀመረው አገራዊ ዘመቻ ስኬት የጤና ሙያ ማኅበራት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ያመለከቱት ዋና ዳይሬክተሩ በንቅናቄ ዘመቻው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን ቢችልም ኅብረተሰቡ ከመደናገጥ ይልቅ ጥንቃቄ በማድረግ ራሱንና ሌላውን መጠበቅ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በቫይረሱ የሚያዙ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ለጤና ባለሙያዎች የግል ደኅንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶች የአቅርቦት ችግር እንዲሻሻልና በደረጃው ተጋላጭ ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች ተደራሽ እንዲሆን ቀደም ሲል መጠየቃቸው ያስታወሱት ማኅበራቱ፣ በአሁኑ ወቅትም በየደረጃው ባለ የጤና ሥርዓት በኃላፊነት ላይ ያሉ አመራሮች ችግሩን ለመቅረፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ማኅበራቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለጤና ባለሙያዎች ሥልጠና መስጠታቸውን ያስታወሱት፣ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት አመዘነ ታደሰ (ዶ/ር)፣ የግል ደኅንነት መጠበቂያ ቁሳቁስ ዕጥረት በመላው ዓለም የተከሰተ ችግር መሆኑን አንስተው፣ በተለይ በጤና ተቋማት ላሉ ኢንተርንና ሬዚደንት ሐኪሞች በአግባቡ መዳረስ እንዳለበት አስረድተዋል።

በዓለም ላይ ለኮሮና ቫይረስ የሚመረት ክትባት ውጤታማነቱና ተገቢነቱ ቢረጋገጥ እንኳ ወደ አዳጊ አገሮች ለመድረስ ጊዜ ስለሚፈጅ ኅብረተሰቡ የጥንቃቄና የመከላከያ መንገዶችን መከተል አሁንም እንደ አማራጭ መውሰድ እንዳለበት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሳያስገነዝቡ አላለፉም።  

የጤና ማኅበራቱ በመግለጫው እንዳሳሰቡት የ24 ሰዓታት የወረርሽኙ ሪፖርት አሁን ካለበት በተሻለ በዝርዝርና በሚያስተምር መልኩ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚደርሰው ዕለታዊ የቫይረስ ሥርጭት መረጃ ይዘት ከሚቀርብበት መንገድ ይልቅ የኅብረተሰቡን መረጃ ፍላጎት መሠረት ያደረገ እንዲሆን ማኅበራቱ እገዛ ያደርጋሉ፡፡  

ባለፉት ጥቂት ወራት ሲተገበሩ የነበሩት የጥንቃቄ መንገዶች፣ ማለትም በጣም አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር በቤት መቆየት፣ አካላዊ መራራቅ፣ የእጅ ንፅህናን መጠበቅ፣ የአፍና አፍንጫን መሸፈኛ ጭንብል በአግባቡና በወጥነት መጠቀምና ያልበሰሉ የእንስሳትና የዓሳ ምግቦችን ከመመገብ መታቀብ መሠረታዊ የመከላከያ ዘዴዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...