Friday, December 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ንግድ ባንክ ሰፊ የመዋቅርና የአደረጃጀት ለውጥ ሊካሄድበት ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በአዲስ አደረጃጀትና አወቃቀር ለማሻሻል የሚያስችል ሰፊ ዝግጅት መጀመሩንና ለዚህ ሥራ በጥናትና የምክር ሥራ ለሚያካሂዱ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጨረታ እንደሚወጣ ታወቀ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት አሁን ያለውን አጠቃላይ አሠራር ለመቀየርና ተወዳዳሪ ባንክ ሆኖ እንዲወጣ የሚያስችውን ሪፎርም ለመተግበር በዓለም አቀፍ ደረጃ  ልምድ ያላቸውን ተቋማት ለመምረጥ በመስከረም ወር ጨረታ ይወጣል፡፡

ቅድመ ጥናቱን የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት አካሂደዋል፡፡ ተቋማቱ የባንኩን ሪፎርም ለማካሄድ ሐሳባቸውን ያቀረቡና በባንኩ አመራር ደረጃም ታስቦበት አጠቃላይ የባንኩን ቅርፅና ይዘት የሚለውጥ አደረጃጀት ይፈጠርለታል፡፡ የዚህን ሒደት የሚቀይሱ አማካሪዎች ተጠንቶ ከቀረበና ከታየ በኋላ በመንግሥት ውሳኔ መሠረት ይተገበራል ተብሏል፡፡

በባንኩ ዕቅድ መሠረት ሥር ነቀል ለውጥ እንዲያመጣ ተብሎ የታመነበትንና የባንኩን የወደፊት ጉዞ የሚያመለክተው የጥናት ውጤት ተፈትሾ በመጪው ዓመት ሊተገበር እንደሚችል ከባንኩ ምንጮች የተገኘው መረጃ ይገልጻል፡፡

ይህ ሪፎርም አጠቃላይ የእስካሁኑ አሠራር በመለወጥና አቅሙን በማጎልበት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ፣ የባንኩ ሪፎርም ማድረግ በአገር ኢኮኖሚ ውስጥ የሚጫተውን ሚና እንዲጎላ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ መጠነኛ ለውጦች በማድረግ ያጋጠሙትን ችግሮች ለመቅረፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ማስታወቁ ተዘግቧል፡፡

ባንኩ በነበሩበት የአሠራር ችግሮች ሳቢያ እንቅስቃሴዎቹ ተዳክመው፣ ያስመዘገበው ዓመታዊ ገቢና ትርፍ ያለወትሮው ማሽቆልቆሉን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች