Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዑጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ የትራክ ንግሥናና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሥጋት

የዑጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ የትራክ ንግሥናና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሥጋት

ቀን:

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የዓለም አትሌቲክስ (ወርልድ አትሌቲክስ)  አቋርጦት የነበረውን የአትሌቲክስ ውድድር ባለፈው ዓርብ ነሐሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በሞናኮ ከተማ በዳይመንድ ሊግ በመጀመር አብስሯል፡፡ የውድድሩ መጀመር በመልካም ጎኑ የሚጠቀስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለወትሮው በእነዚህ የውድድር መድረኮች በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ያስመዘገቡት ውጤት ግን ምናልባትም “ኢትዮጵያና አትሌቲክስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ” ሲባል የቆየውን ማዘናጊያ በጉልህ ያመላከተ ክስተት ሆኖ ማለፉ አልቀረም፡፡

የሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያን በመሰሉ በአትሌቲክሱ ቀደምት ታሪክ ለነበራቸው አገሮችና አትሌቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ቆም ብለው ራሳቸውን እንዲፈትሹ ያስቻለ መድረክ እንደሆነ የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡ ሙያተኞቹ ለዚህ ሥጋታቸው ዑጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ በ5,000 ሜትር ያስመዘገበው አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ ጭምር ያስረዳሉ፡፡

በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያ በሴቶች 5,000 ሜትር ሁለተኛ ሆና ካጠናቀቀችው ለተሰንበት ግደይ በስተቀር፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያን የአሯሯጭነት መልክ ይዘው ውድድሮቻቸውን አጠናቀዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያውያን በአትሌቲክሱ ዘርፍ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት አትሌቶች ከፊት የማይጠፉበትን ጊዜ መለስ ተብሎ እንዲታወስ ያስገደደበትን አጋጣሚ ፈጥሯል፡፡

የዑጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ የትራክ ንግሥናና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሥጋት

 

በሁለቱም ጾታ የተደረገው 5,000 ሜትር፣ በ3,000 ሜትር መሰናክልና በሌሎችም ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በተሳተፉበት የሞናኮ ዳይመንድ ሊግ፣ ከቀደምቱ ጀግኖች አይበገሬው ቀነኒሳ በቀለ ለ16 ዓመታት ያህል ተይዞ የቆየው የ5,000 ሜትር 12፡ 37. 35 የዓለም ክብረ ወሰን፣ በዑጋንዳዊ ጆሽዋ ቼፕቴጌ 12፡ 35. 37 ተሻሽሏል፡፡

በትራክ ውድድር በጥንካሬው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠቀሰ የሚገኘው ዑጋንዳዊው ጆሽዋ ዳይመንድ ሊግን ጨምሮ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚያስመዘግባቸው ውጤቶች በተለይም ለኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ፈታኝ እንደሚሆን ከወዲሁ እየተነገረለት ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...