የሲቪክ ሰርቪስ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ስብስብ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለከፋ ችግር የተዳረጉ ወገኖችን ለመርዳት “ከራሳችን እንጀምር” በሚል ሐሳብ በመነሳሳት፣ ለአካል ጉዳተኞች በነፍስ ወከፍ 50 ኪሎ ፉርኖ ዱቄት፣ አምስት ሊትር ዘይት፣ የሚታጠቡ ሦስት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛን ሐምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም. አስረክበዋል፡፡ በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኅበራት ፌዴሬሽን ቅጥር ግቢ የነበረውን ሥነ ሥርዓት ከፊል ገጽታ ፎቶዎቹ ያሳያሉ፡፡