Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዳግም የተከሰቱት የኮሌራና ወባ ወረርሽኞች

ዳግም የተከሰቱት የኮሌራና ወባ ወረርሽኞች

ቀን:

በአገር አቀፍ ደረጃ እስከ ሐምሌ 2012 ዓ.ም. የመጨረሻው ሳምንት ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊዮ፣ የኮሌራና የወባ ወረርሽኞች ተከስተዋል፡፡ በዚህም 145 ሰዎች ሲጠቁ፣ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የኅብረተሰብ ጤና ሥጋቶችና ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ ሳምንታዊ መግለጫ አመልክቷል፡፡

ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. የወጣው መግለጫ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በስድስት ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል አንድ ወረዳ የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በምዕራብ ኦሞ ዞን በጋጨትና በጎርጎርሻ ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ በአዲስ መከሰቱን መግለጫው አመላክቶ፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የሕክምና አቅርቦትን የማስፋፋት፣ የውኃ ንፅህና መጠበቂያ ኬሚካሎችን የማሠራጨት፣ የቤት ለቤት ርጭት፣ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር  ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች የማፈላለግና የክትትል ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለወባ በሽታ ከተመረመሩት ውስጥ 27‚898 ሰዎች ምልክት የታየባቸው ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል፡፡

የወባ ወረርሽኝ የተከሰተባቸውም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ፣ በትግራይ፣ በደቡብ ክልሎች በሚገኙ 42 ወረዳዎችና 19 ዞኖች ውስጥ ነው፡፡ ለዚህም የምላሽ ሥራ እየተሠራባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 እንደ መግለጫው እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ በመላ ኢትዮጵያ 32 ሰዎች ፖሊዮ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ብቻ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሐረርጌ በቦኬ ወረዳና በአዳማ ከተማ ሁለት ሰዎች በፖሊዮ መያዛቸው ታውቋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 መከሰቱን ተከትሎ ግብዓቶችን በወቅቱ ወደ አገር ውስጥ የማድረስ፣ የንፁህ ውኃ አቅርቦት፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚሠራጩ ግብዓቶች መዘግየት፣ የተሻሻለ የመፀዳጃ ቤት አቅርቦት አለመኖር፣ ክልሎች በኮቪድ-19 በሽታ ሥራ መጠመድ፣ የማኅበረሰብ ንቅናቄ ዘመቻ  አጀማመር ወጥ አለመሆን፣ በክልሎች ያለው የቅድመ ዝግጅትና የንቅናቄ ሥራ ውስን መሆን ችግሮች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...