Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርየደረቅ ቼክ ክሶች ምሕረት መቼ ነው የሚደረግላቸው?

የደረቅ ቼክ ክሶች ምሕረት መቼ ነው የሚደረግላቸው?

ቀን:

መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት የለውጥ ሽግግሩን የበለጠ ለማሳለጥ ከፖለቲካና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ታስረውና ክሳቸው በሒደት ላይ ያሉ ሰዎችን በመንግሥት ዓይን እይታ በመመልከት ምሕረትና ይቅርታ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በተለይ ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ በማረሚያ ቤት ያሉ ዜጎችን ለመታደግ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ታራሚዎችና ጉዳያቸው በክስ ሒደት ላይ ያሉ ዜጎችን ምሕረት በማድረግና ክስ በማቋረጥ ምን ያህል የአሁኑ መንግሥት የዜጎችን ጉዳት በጥልቀት መመልከት እንደሚችል አሳይቷል፡፡

በቅርቡ አገሪቱ ካጋጠማት የኢኮኖሚ ችግሮችና ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ የኢኮኖሚ ችግሮችንና ተግዳሮቶች በንግድ ማኅበረሰቡ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ከኢኮኖሚ ወንጀሎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው የታክስ ጉዳዮችን ማለትም ከንግድ ማጭበርበር፣ ከኮንትሮባንድና ከሐሰተኛ ሰነዶች ጋር በተያያዘ በድርጅቶችና በግለሰቦች ላይ የተመሠረቱት ክሶችን ያነሳ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህ የመንግሥት ተግባር በብዙ መልኩ የሚደገፍ ቢሆንም፣ ከደረቅ ቼክ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ክሶችንና ታራሚዎችን ጉዳያቸው በዚህ ሒደት ውስጥ አለመታየቱ ጉዳዩ በሚመለከታቸው በርካታ ዜጎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡

በተጨማሪም መንግሥት አሁን የወሰደውን ዕርምጃ የፍትሐዊነት ሚዛን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በጥቅሉ በአገራችን በተፈጠረው የኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያት የንግድ ሥርዓቱ በመቀዛቀዙና የእኛ አገር የንግድ ባህል በመበዳደርና ደረቅ ቼኮችን በመያዣነት በመስጠትና ዋስ በማድረግ የሚከናወን በመሆኑ፣ ከዚሁ የኢኮኖሚ ችግር ጋር በተያያዘ ተበዳሪዎች ለተበደሩት ወይም በቼካቸው ዋስትና የሰጧቸው ግለሰቦች በቼኩ ባለቤት ላይ ክህደት በመፈጸማቸው ወዘተ ምክንያት ከፍትሐ ብሔር ክስ በተጨማሪ ከደቀረቅ ቼክ ሰነድ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ብዙ ዜጎች የወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸውና በማረሚያ ቤት በስቃይ ይገኛሉ፡፡ የደረቅ ቼክ ክስ የመንግሥት ክስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ ምክንያት ብዙ ንፁህን ዜጎች ማለትም

  • በዕድሜ የገፉና በቼክ ዋስ በመሆናቸው ብቻ ክስ የተመሠረተባቸው፣
  • ሴቶችና የልጆች እናቶች ከዚህ ደረቅ ቼክ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ክስ የተመሠረተባቸውና በማረሚያ ቤት ያሉ፣
  • በአራጣ አበዳሪዎች ድርጊት በደረቅ ቼክ ምክንያት ሰለባ የሆኑና
  • በሌሎች ሰዎች ለተበዳደሩ እንደ ዋስትና ቼካቸውን በመስጠት የተካዱ አሉ፡፡

በእነዚህ ምክንያቶች ክስ ተመሥርቶባቸውና በሒደቱ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚሰቃዩ በርካታ ዜጎች ናቸው፡፡ ከዓለም አገሮች ውስጥ ቼክን በፍትሐ ብሔርና በወንጀል በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚከሱ ውስን አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት፡፡ ለምሳሌ አንድ የንግድ ግለሰብ ቼክን እንደ መያዣ በመስጠት የተበደረውን ወይም ዋስ የሆነበትን በኪሳራ ምክንያት ገንዘቡን ካልከፈለ በፍትሐ ብሔር ንብረቱን ከመውረስ በተጨማሪ በመንግሥት በኩል በወንጀል መጠየቁ የቼክ የወንጀል ክስ ምን ያህል ኢፍትሐዊ እንደሆነ ያሳያል፡፡

ስለዚህም መንግሥት ይህንን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባትና እስካሁን ካነሳቸው ክሶች አኳያ፣ ቼክ በጣም ትንሽ ተራ የወንጀል ክስ መሆኑን በጥልቀት በማየት የተለያዩ ንፁህን ዜጎች ባለማወቅ የፈጸሙትም ስህተት ግምት ውስጥ በማስገባትና በመንግሥታዊ እይታ በመመልከት ክሳቸው እንዲያቋርጥና ምሕረት እንዲያደረግ የተጎጂ ቤተሰቦች ይጠይቃሉ፡፡

ከዚሁ ጉዳይ በተያያዘ ዓቃቤ ሕግ በተለያዩ ጊዜያት በተጎጂ ቤተሰቦች ክሳቸው እንዲነሳ ሲጠየቅ፣ የግለሰብ ጉዳይ ነው በሚል ተጨባጭ ያልሆነ የሕግ ምክንያት ወደ ጎን ሲተው ይታያል፡፡ ነገር ግን ዓቃቤ ሕግ እስካሁን የግለሰቦችን ብሎም የአገርን ጥቅም የሚነኩ የተለያዩ ከኢኮኖሚ ወንጀሎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያዙ የተለያዩ ክሶችን በመንግሥታዊ እይታ በማየት ሲያነሱ፣ የቼክ ክሶችን ወደ ጎን መተው ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በቀጣይ ከሚያነሳቸው ክሶች ጋርና መንግሥት ምሕረት ከሚያደርግላቸው ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምን የታሰበ ነገር አለ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...