Saturday, June 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ልማት ባንክ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ አተረፈ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የተበላሸ ብድር መጠኑ ወደ 25 በመቶ ዝቅ ብሏል

የተበላሸ የብድር መጠኑ አሻቅቦ የቀየቀውማ ባለፈው ዓመት ኪሳራ ያስመዘበው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ዘንድሮ የተበላሸ የብድር መጠኑን ወደ 34 በመቶ ዝቅ ማድረግ እንደቻለና ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ አዲስ ታሪክ እንዳስመዘገበ አስታወቀ፡፡

አፈጻጸሙን በማሻሻል በባንኩ ታሪክ ከፍተኛ የተባለ የ1.13 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገብ የቻለው ይህ የመንግሥት የፖሊሲ ባንክ፣ በ2013 ዓ.ም. የተበላሸ የብድር መጠኑን አሁን ከደረሰበት በማውረድ ወደ 25 በመቶ ዝቅ ለማድረግ አቅዷል፡፡

የልማት ባንክ የ2012 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም እንደሚያሳየው፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ 40 በመቶ ያሻቀበውን የተበላሸ ብድር መጠን ዘንድሮ ወደ 34 በመቶ ለማውረድ ችሏል፡፡ ይህም የ4.6 በመቶ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን የሚጠቁም ነው፡፡ በዓመቱ ያስመዘገበው ውጤት ዓምና ካጋጠመው ኪሳራ አውጥቶት ወደ አትራፊነት እንዳሸጋገረው የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የበጀት ዓመቱ ትርፍም ከዕቅዱ በላይ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ በዓመቱ የ7.37 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዝግቧል፡፡ ከዕቅዱ አኳያም የ111 በመቶ አፈጻጸም የታየበት ሆኗል፡፡ ይህ የዘንድሮ ገቢ ከዓምናው አንፃር ሲታይ የ31 በመቶ ዕድገት እንዳሳየ ባንኩ አስታውቋል፡፡  

በዓመቱ 10.4 ቢሊዮን ብር በብድር እንዲሰጥ ያፀደቀ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 8.58 ቢሊዮን ብር ለተበዳሪዎች መልቀቁን ባንኩ አመላክቷል፡፡ ከብድር አሰባሰብ አንፃር በዕቅድ ከያዘው አፈጻጸም አኳያ 98 በመቶውን እንዲሳካ በመጥቀስ፣ 7.7 ቢሊዮን ብር እንዳሰባሰበ ይፋ አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ የባንኩ የብድር ክምችት 55.67 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ፣ የዘጠኝ በመቶ ዕድገት እንደታየበት ባንኩ አስፍሯል፡፡

በ2013 ዓ.ም. የ10.09 በ2011 ዓ.ም. የ768.7 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ማስመዝገቡ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች