Monday, June 24, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ ሌላ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው

[ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ጸሐፊያቸው ገባች]

 • ፈለግሽኝ?
 • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ቀጠሮ ነበረብኝ፡፡
 • አይሆንም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምኑ ነው የማይሆነው?
 • ማውራት አለብን፡፡
 • አስቸኳይ ነው?
 • በጣም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እሺ ቁጭ በይ፡፡
 • ምን አጠፋሁ ክቡር ሚኒስትር?
 • ኧረ ምንም፡፡
 • ያስቀየምኩዎትን ነገር ንገሩኝ?
 • አላስቀየምሽኝም አልኩሽ እኮ፡፡
 • በሥራዬ ደስተኛ አይደሉም?
 • ምን ሆነሻል ዛሬ?
 • የእውነቱን ንገሩኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • አልገባኝም?
 • እኮ ጥፋቴን ንገሩኛ?
 • ምንም አላጠፋሽም አልኩሽ እኮ፡፡
 • እኔ እኮ የምሠራውን ሥራ የወደዱት መስሎኝ ነበር?
 • የትኛውን ሥራ?
 • እርስዎ የሰጡኝን ሥራ ነዋ፡፡
 • እኮ የትኛውን?
 • ይኼ ሠራተኞችን የማባላት ሥራውን ነዋ፡፡
 • በእሱማ ሁሌም ታስደስቺኛለሽ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ እኮ ወንበርዎት እንዲፀና ነው የምፈልገው፡፡
 • እንዴት ማለት?
 • ያው ሠራተኞቹ እርስ በርስ እየተባሉ የእርስዎን ሌብነት የሚጠይቅ አይኖርማ፡፡
 • እየሰደብሽን ነው?
 • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር፣ የምሠራው ሥራ ወሳኝ ነው ለማለት ነው፡፡
 • እሱማ ነው፡፡
 • ይኼ አካሄድ ሠራተኛውን ከፋፍሎ ለመግዛት ያመቻል ብዬ ነው፡፡
 • በጣም የሚሠራ ስትራቴጂ ነው ስልሽ፡፡
 • ታዲያ ምነው ዘነጉኝ?
 • እንዴት?
 • ሰሞኑን ባለው ሹም ሽር ቦታ አገኛለሁ ብዬ ነበር፡፡
 • የአንቺ ሥራ እኮ አይተኬ ነው፡፡
 • ምን እያሉኝ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ማለቴ አንቺ የምትሠሪውን ሥራ ማን ይሠራልኛል ብለሽ ነው?
 • እሱስ ልክ ነዎት፡፡
 • ለዚያ ነው እኮ ሌላ ሹመት የማልሰጥሽ፡፡
 • ግን ምን አለ ደርቤ ብሠራ?
 • ምን?
 • ማለት አንድ ሥልጣን ቢሰጡኝ ከአሁኑ ሥራዬ ጋር ደርብ እሠራዋለሁ፡፡
 • የሚገርምሽ እኔም እያሰብኩበት ነው፡፡
 • ምኑን?
 • ከአንቺ ጋር የሚሄድ አንድ ኮሚሽን ሊቋቋም ነው፡፡
 • እውነት?
 • ስለዚህ አንቺ ከአሁኑ ሥራሽ ጋር ደርበሽ ትሠሪዋለሽ፡፡
 • ደስ ይለኛል፡፡
 • ከሰሞኑ የአዲሱ ኮሚሽን ኃላፊ ተደርገሽ ትሾሚያለሽ፡፡
 • ምንድነው አዲሱ ኮሚሽን?
 • የሴራ ፈጠራ ኮሚሽን!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር ቢሮ እያወሩ ነው]

 • ምን ሆነሃል?
 • ምን ሆንኩ?
 • ያኮረፍክ ትመስላለህ፡፡
 • ለምን አላኮርፍ ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ተገኘ?
 • የሚሠራው ነገር ሁሉ ያሳዝናል፡፡
 • ምን ተሠራ?
 • እኛ እኮ ብዙ ሚስጥር እናውቃለን፡፡
 • የምን ሚስጥር?
 • አማካሪዎት አይደለሁ እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን እያልክ ነው?
 • ማለቴ ስለእርስዎም ቢሆን ብዙ ነገር አውቃለሁ፡፡
 • ምንድነው የምታውቀው?
 • ከቤት ጀምሮ ውጭ አገር እስካስቀመጡት ሀብት ነዋ፡፡
 • እ…
 • ክቡር ሚኒስትር ቤት ስንት ካዝና እንዳልዎት አውቃለሁ፡፡
 • የምን ካዝና?
 • ገንዘብ ያስቀመጡበት ነዋ፡፡
 • እ…
 • አሁን ደግሞ የወጣውን መመርያ ሰምተዋል አይደል?
 • የምን መመርያ?
 • ቤት ማስቀመጥ የሚችሉት ገንዘብ ገደብ ተደርጎበታላ፡፡
 • ምን ያህል?
 • ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ አይቻልም ተብሏል፡፡
 • እኔ እኮ ያን ያህል ገንዘብ የለኝም፡፡
 • ለነገሩ በብር ላይኖርዎት ይችላል፡፡
 • ማለት?
 • ያው በዶላር ቀይረው ነዋ የሚያስቀምጡት፡፡
 • ኧረ እኔ እንደዚህ ዓይነት ገንዘብ የለኝም፡፡
 • ምን?
 • ስነግርህ ቤት የሚላስ የሚቀመስ የለንም፡፡
 • እያጃጃሉኝ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እውነቴን ነው ምንም ነገር የለንም፡፡
 • ዝም ብለን ስንሰማዎት የምናምንዎት ይመስልዎታል?
 • ምን እያልከኝ ነው?
 • እያንዳንዷን ነገር እናውቃለን፡፡
 • እያስፈራራኸኝ ነው?
 • እሱ ብቻ አይደለም፡፡
 • ማለት?
 • የሰነዶች ማስረጃዎችም በእጃችን አለ፡፡
 • የምን ማስረጃ?
 • ስለሚሠሯቸው ወንጀሎች ነዋ፡፡
 • ሁሉም ነገር ገብቶኛል፡፡
 • ምኑ ነው የገባዎት?
 • አሁን ለምን አልተሾምኩም ነው አይደል?
 • ክቡር ሚኒስትር እንደዚህ ዓይነት የተጨመላለቀ አስተሳሰብና ሥራ እንደማልወድ ያውቃሉ አይደል?
 • በቃ ጥሩ ሹመት እሰጥሃለሁ፡፡
 • ነገርኩዎት እኮ ከእርስዎ ጋር መሥራት አልፈልግም፡፡
 • ሹመት አትፈልግም?
 • የመጣሁት እኮ ላስገባ ነው፡፡
 • ምን?
 • መልቀቂያዬን!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከደላላ ወዳጃቸው ጋር እያወሩ ነው]

 • ሰሙ አይደል ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑን?
 • አዲሱን መመርያ ነዋ፡፡
 • የትኛውን?
 • ቤት የሚቀመጥ ገንዘብ ላይ ገደብ የሚጥለው ነዋ፡፡
 • ምን ችግር አለው ብለህ ነው?
 • ባንክ ነው እንዴ የሚያስቀምጡት እርስዎ?
 • ኧረ ቤት ነው፡፡
 • ያው አሁን ወንጀል ሆኗል ብዬ ነው፡፡
 • በዶላር ነዋ የማስቀምጠው፡፡
 • ቢያስወጡት አይሻልም?
 • እንዴት አድርጌ?
 • መላ መቼ ይጠፋል ብለው ነው፡፡
 • ባለፈው እኮ በልተውኝ ነው፡፡
 • እንዴት?
 • ወደ ውጭ እናሻግርልሃለን ብለው ቀልጠው ቀሩ፡፡
 • ምን?
 • አዎን፡፡
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ላድርግ?
 • እ…
 • አልከሳቸው፡፡
 • እንዴት ደፈርዎት ብዬ ነዋ?
 • ያው ሕገወጥ እንደሆንኩ ስለገባቸው ነዋ፡፡
 • ብዙ ነው?
 • በጣም እንጂ፡፡
 • ተጎድተው ነበራ?
 • ለነገሩ ያው እኔም ሰርቄ ስለማመጣው ጉዳቱ ብዙ አልተሰማኝም፡፡
 • ቢሆንም ያናድዳል ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ፖለቲካ ቁማር አይደል?
 • እና ቁማር ተበልቼ አውቃለሁ እያሉኝ ነው?
 • በሚገባ እንጂ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ሰሞኑን ግን እያሳሰበኝ ነው፡፡
 • ምን?
 • የእርስዎ ጉዳይ ነዋ፡፡
 • እንዴት?
 • ያው እዚህም በስምዎት በርካታ ቤቶች አሉ፡፡
 • ምን ችግር አለው?
 • ስምዎት እየተነሳ ነው ብዬ ነው፡፡
 • በምን?
 • በሙስና ነዋ፡፡
 • ሙሰኛ ያልሆነ ማን አለ ብለህ ነው?
 • የእርስዎ ግን ያፈጠጠ ነው፡፡
 • ምኑ?
 • ማስረጃው፡፡
 • ምን ማድረግ እችላለሁ?
 • ለምን ከአገር አይወጡም?
 • አልችልማ፡፡
 • እንግዲያው ራስዎትን ያዘጋጁ፡፡
 • ለምኑ?
 • ለመስጠት ነዋ፡፡
 • ምን?
 • እጅዎትን!

[ለክቡር ሚኒስትሩ ሌላ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]

 • ሁሉንም ደርሰንበታል ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ሰላምታ አይቀድምም፡፡
 • ያሳዝናሉ ግን፡፡
 • ምነው?
 • ትንሽ አይሰማዎትም ግን፡፡
 • ምን አደረኩ?
 • በሕዝብ እንደዚህ ሲቀልዱ ነዋ፡፡
 • እኔ ሁሌም ሕዝብ ማገልገል ነው ሥራዬ፡፡
 • ለነገሩ ሰምቻለሁ፡፡
 • ምኑን?
 • እንደ እርስዎ ዓይነት ውሸታም እንደሌለ ነዋ፡፡
 • እ…
 • በዛ ላይ ግትር ነዎት፡፡
 • ተው እንጂ፡፡
 • ሲቀጥል ምንም አቅም የልዎትም፡፡
 • እየተሳደብክ እኮ ነው፡፡
 • ከዚህ የሚብስ ገና ይደርስብዎታል፡፡
 • ምን ልታደርጉኝ ነው?
 • የሚያሳዝነው እስከ ዛሬ በሕዝብ ላይ መቀለድዎት ነው፡፡
 • ተው እንጂ፡፡
 • አሁን መውደቂያዎት ደርሷል፡፡
 • እ…
 • ሁሉም ነገር በእጃችን ገብቷል፡፡
 • ምኑ?
 • ማስረጃዎቻችንን ይዘን ጨርሰናል፡፡
 • ምን ልታደርጉኝ?
 • ልንጠፍርዎት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...