Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከ60 ሺሕ በላይ ሰዎችን የገደለው የዓምናው የቤት ውስጥ አየር ብክለት

ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎችን የገደለው የዓምናው የቤት ውስጥ አየር ብክለት

ቀን:

ከኢትዮጵያ ሕዝብ 55 በመቶ ያህሉ በኤሌክትሪክ ዕጦት የሚቸገር ነው፡፡ ይህም ህብረተሰቡ በተለይ ለቤት ውስጥ ፍጆታ የእንጨት ማገዶን እንዲጠቀም አስገድዶታል፡፡

የቤት ውስጥ አየር ብክለትን ከሚያስከትሉ ተርታ የተሠለፈው የማገዶ እንጨት ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ነው፡፡ በማገዶ እንጨት ምክንያት በገጠር የሚኖሩ አብዛኞቹ ሰዎች ለዓይን ሕመም ተዳርገዋል፡፡ ለመተንፈሻ አካል ችግር ተጋልጠዋል፡፡ እንጨት ፍለጋ ማስነዋል፡፡ ይህ ዛሬም የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሕይወት ክፍል ነው፡፡

የእንጨት ማገዶ በስፋት ጥቅም ላይ በሚውልባት ኢትዮጵያ በቤት ውስጥ በሚፈጠር አየር ብክለት በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ይሞታሉ፡፡ በቤት ውስጥ አየር ብክለት ሳቢያም ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለሕልፈት ሕይወት መዳረጋቸውን በጥናት ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ካፌና ሬስቶራንት በጠቅላላ ሠራተኛ ስም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማከናወኛ የሦስት ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዥ የፈጸመበትን ቼክ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሰሞኑን ሲያስረክቡ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኤባ አባተ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ከሶስት ሚሊዮኑ መካከል  67,000 ያህሉ የሞቱት ዓምና ሲሆን፣ የተቀሩት ደግሞ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ነው፡፡

ከ55 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ የኤሌክትሪክ ሀይል የማይጠቀም በመሆኑ በቤት ውስጥ በሚከሰት የአየር ብክለት ለሳንባ ምች፣ ለሳንባ ካንሰር፣ ለልዩ ልዩ ከመተንፈሻ አካላት ጋር ለተያያዙ በሽታዎች፣ ለልብ ህመምና ለሌሎችም በርካታ ህመሞች ተጋላጭ እንደሚሆኑና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ ልዩ ልዩ በሽታዎች ለህልፈተ ህይወት እንደሚዳረጉም ተናግረዋል፡፡

የግድቡ መጠናቀቅ ከኤሌክትሪክ ተደራሽነት ባሻገር ከጤና አንፃር ብዙ ትሩፋቶችና ጥቅሞች እንዳሉት ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተው፣ በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ሳቢያ ወሳኝ በሆኑ ጤና ተቋማት ውስጥ የሚገኙ የቀዶ ሕክምናና የላቦራቶሪ ክፍሎች ቀጣይና ዘላቂ አገልግሎት ለመስጠት እንደተሳናቸውም አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ ኃይሉ አብርሃም የታላቁ ህዳሴ ግድብ እስከሚጠናቀቅ ድረስ 160 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ፣ እስካሁን 121 ቢሊዮን ብር እንደወጣና ሥራውን ለማጠናቀቅ ወደ 40 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...