Tuesday, July 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

ይህን ስጽፍ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሰዎች ያለፈው ሳያንስ ከዚህ በኋላም ቅር ሊሰኙም፣ ሊቀየሙኝም ይችላሉ። እኔ ግን የምመዝነው ሰውን ከማትረፍ ጋር ነውና እችለዋለሁ።

አንዳንድ አዘገጃጀቶቹ የሚታረሙ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ከሬዲዮ ፋና ምርጥ ፕሮግራሞች አንዱ፣ ‹‹እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?›› የሚለው የቅዳሜ ጠዋት ፕሮግራም ነው። ይህ፣ አንድ ሰው ራሱን በፕሮግራሙ በቀረበው ባለጉዳይ ቦታ ቢሆን ስለሚወስደው ዕርምጃ በስልክ ሐሳቡን የሚገልጽበት ነው።

በምኖርበት የካ አባዶ ኮንዶሚኒየምማራኪየተሰኘ የነዋሪዎች ማኅበር ሲኖር የማኅበሩ ጸሐፊ ነኝ።አብዛኛውበሚያሰኝ አገላለጽ ነዋሪው እንደ ሌላው አካባቢ ለጋራና ራሱ ለሚጠቀምበት ልማት ተባባሪ ካለመሆን አልፎ በፈጠራ ጥርጣሬ የተለየ ስም ለጣፊ ነው። ትምክህት አይሁንብኝና፣ አይደለም ታማኝ አለመሆን በምሳተፍበት ኮሚቴም ይሁን ስብስብ ውስጥ ሌባ ካለ አብሬው አልሠራም።

የእኛ ኮሚቴ ግን ከአንዳንዶች ዳተኝነትና እንደ ብዙዎቹ የአገራችን ፓርላማ አባላት አንገት ለመነቅነቅና እጅ ለማውጣት ከመፈጠር በስተቀር ከዚህ የፀዳ በመሆኑ አብሬ ስሠራ ደስ እያለኝ ነው። በዚህ ሒደት በተለይ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን ስንሠራ ቆይተናል። በቆይታችን ብዙ ችግሮችን ያሳለፍን ቢሆንም ካለፈው መጋቢት ወዲህ ግን በተከሰተው የኮሮና ወረርሺኝ ራሳችንን ለአደጋ አጋልጠን ብዙ ነገሮችን አከናውነናል።

እነዚህን ለማከናወን ውሳኔዎች ያስፈልጋሉና በስብሰባ ተወያይተን በቃለ ጉባዔ ለማስረገጥ አምስትም፣ ስድስትም ሆነን መክረናል። በዚህ ሁኔታ ታዲያ ነሐሴ 11 ምሽት ስብሰባ አድርገን ነሐሴ 13 አንድ መረጃ ይደርሰኛል። መረጃውም፣ በስብሰባ ካመሸነው ውስጥ ማስኩን አንገቱ ስር ወሽቆ ሲናገረ የነበረው አንደኛው በኮሮና ቫይረስ ተይዞ የካ ኮተቤ ሆስፒታል መግባቱ ነበር። ይህን የነገረኝ ሰው ግን ጉዳዩን በምስጢር መያዝ እንዳለብኝ ቢያስጠነቅቀኝም እንደ ሌሎች ጉዳዮች በምስጢር ስለመያዜና ስላለመያዜ ከራሴ ጋር ሳልሟገት ቢያንስ ለኮሚቴ አባላቱና ለጎረቤቶቹ ማሳወቅ እንዳለብኝ በውስጤ የወሰንኩት እዚያው ምስጢር ነጋሪዬ ፊት ነው።

ከዚያ በፊት ግን ከራሱ ለማረጋገጥ ስልክ ደውዬ፣ምነው ጠፋህ?” ስለው ‹‹ክፍለ አገር ጉዳይ ገጥሞኝ ነው›› ነበር ያለኝ። እንደ ኤች አይ በምስጢር በመያዙ ውስጤ እያዘነ ለኮሚቴ አባላቱና ለአንዳንድ ጎረቤቶቹ ካሳወቅሁ በኋላ ያልሰማሁ የመሰለው አንድ ሌላ ራሱ ታማሚው የነገረው ሰው፣ ‹‹ለማንም የማይነገር ምስጢር›› ብሎ ነገረኝ። ‹‹እናንተ ምን ነካችሁ? ምስጢር የማይሆንና የሚሆንን ለዩ እንጂ! ይሄ ነፍስ የማዳን ነገር ነው። ሲሆን ንክኪ ያለው ሰው ራሱን እንዲጠብቅ በፌስቡክም፣ በግድግዳ ማስታወቂያም ማሳወቅ እንጂ ጭራሽምስጢር ነውይባላል?›› ብዬ በመቆጣትና፣ ‹‹ግለሰቡ ግን ወዳጆቹ እናንተ ብቻ ናችሁ?›› በማለት ማዘኔን ገልጬ ተለያየን።

ያን ዕለት ምሽት ታማሚው ደውሎ ሊያናግረኝ ሲሞክር፣ ‹‹ለምን ትደውላለህ? ያንተ ወዳጆች ብቻ እንዲተርፉ ካደረግህ በኋላ ማዘኔን ሰው ሲነግርህ ነው የምትደውለው?›› ብዬ ስልኩን ዘጋሁ። በነጋታው ግን ደውሎልኝ የማያሳምኑ ምክንያቶችን ሲደረድርልኝ እሱን ትቶ ማድረግ ያለብንን ተማከርንና የአካባቢው ነዋሪ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስደረግሁ።

ከዚህ በፊት ግን ወደ 8,335 ደውዬ በተለያዩ ደቂቃዎች ልዩነት ያናገሩኝ የጤና ሚኒስቴር ኦፕሬተሮች ማድረግ ስላለብን ጥንቃቄ በትህትና መልስ በመስጠታቸው ምሥጋናዬ ከአድናቆት ጋር ነው። ምክንያቱም፣ እንደ ቴሌና መብራት ኃይል ኦፕሬተሮች ስልክ ያለማንሳት ነገር እንደሌለባቸውና እንደውም ፈጣኖች በመሆናቸው።

ከኦፕሬተሮቹ ባገኘሁት መረጃ ያመራሁበት የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ቢሮ ባለሙያ ግን ከኦፕሬተሮቹን ትህትና ተቃራኒ ነበር። ‹‹እዚያ ራቅ በል!›› ከሚል ማመናጨቅ ተጀምሮ፣ ‹‹ታማሚው ስማችሁን እንዲያስመዘግብ ንገሩት›› በሚል የተኮሳተረ ፊት መለሰኝ።

ለማንኛውም ከታማሚው በተሰጠኝ የሞባይል ስልክ መሠረት ደውዬ የአምስቱንም የኮሚቴ አባላት ሙሉ መረጃ በቃልም፣ በጽሑፍ መልዕክትም አሳውቄ የኮሚቴ አባላቱ የምንኖርባቸው ስድስት ሕንፃዎች ነዋሪዎችም ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው አስገንዝቤ ነበር። ይህ ከሆነ ዛሬ ስድስተኛ ቀን ቢሆንም ለእኛም፣ ለነዋሪውም የተደረገ ምርመራም ሆነ ሌላ ነገር የለም። እውነትም መንግሥት አቅም እንዳጣ ወይም የሕዝቡ ቸልተኝነት እንደተጋባበት ያመንሁት አሁን ነው። ምክንያቱም፣ በፊት አብነትና 24 አካባቢዎች ሥጋት የታየባቸው ስለነበሩ ከእንቅስቃሴ ዘግቶ ስለነበር።

በበኩሌ፣ በየቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ ሕፃናትና ታዳጊዎች የተለመደ ጨዋታቸውን ቀጥለው ስለነበር በማስቆሜ፣ በመልካም አሳሳቢዎች አነሳሽነት የማስጠንቀቂያ መልዕክት በመለጠፌና ጉዳዩን የሚመለከተው ቦታ በማድረሴ የህሊና እርካታ አግኝቻለሁ።

ከዚህ ባሻገር ግን ጉዳዩን እንደሰማሁ የነበረው በጭንቀት የታመመ መምሰል ቢለቀኝም ቢያንስ 14 ቀን ቤት ውስጥ ከጤና ኦፕሬተሮች የተመከርሁትን የጥንቃቄ ዕርምጃዎች እየወሰድሁ ሲሆን በአስቸኳይ ሥራ ምክንያት ግማሽ ግማሽ ቀን እየሠራሁበት ያለው ሥሪያ ቤቴ ላይ ባልደረቦቼን አሳውቄ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተንቀሳቀስሁ ነው። እኔስ ይህን አደረግሁ፣ እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ? በዚህ አጋጣሚ ማገዝ የምትችሉ ሰዎች ብታስመረምሩን መልካም ነው።

  • እስክንድር መርሐጽድቅ በማኅበራዊ ገጹ ‹‹እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?›› በሚል ርዕስ የጻፈው
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...