Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ አስተዳደር ጳጉሜን አንድን በይቅርባይነት የሚያከብር መርሐ ግብር ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ጳጉሜን አንድን በይቅርባይነት የሚያከብር መርሐ ግብር ይፋ አደረገ

ቀን:

በአምስቱ የጳጉሜን ቀናት መሰናዶዎች ይኖራሉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ.ም. ለመቀበል በሚቀሩት  አምስቱ የጳጉሜን ቀናት ‹‹አዲስ አበባን በአዲስ የተስፋ ብርሃን›› በሚል መሪ ቃል ከኅብረተሰቡ ጋር ለማክበር እንደተዘጋጀና ጳጉሜን አንድ ቀንን ‹‹ይቅርታ እላለሁ ይቅር እላለሁ›› በሚል መርሐ ግብር እንደሚያከብር አስታወቀ፡፡

የአስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ወ/ሮ አልፍያ ዩሱፍ ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ይቅርታ እላለሁ ይቅር እላለሁ በሚል የሚጀምረው የጳጉሜን አንድ መርሐ ግብር፣ ይቅርታ የኢትዮጵያውያን ባህልና እሴት መሆኑን በማጉላት ኅብረተሰቡ፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ አገልጋዮችና ተገልጋዮች ይቅርታ የሚባባሉበት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በሚታደሙበት መርሐ ግብር፣ ‹‹ልባችንን በይቅርታ አካባቢያችንን በፀረ ተዋህሲያን እናፀዳለን፤›› ብለዋል፡፡

እኔ ለወገኔ፣ እኔ ለሕዝቤ፣ እኔ ለአገሬ በሚል ጳጉሜን ሁለት ቀን የሚከበረው የአብሮነት ቀን፣ ደሃውን በመርዳት፣ የታመመውን በመጠየቅ፣ የበረደውን በማልበስና ያዘነውን በማፅናናት የሚከበር ይሆናል፡፡

በአብሮነት ቀን ሸገር ዳቦ የዕለት አቅርቦቱን በነፃ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስም ይሆናል፡፡ የአምባሳደርነት ቀን በሚከበርነት ጳጉሜን ሦስት አገራቸውንና ከተማቸውን በመልካም የሚያስጠሩ ዜጎች ‹‹አምባሳደሮች›› ዕውቅና የሚሰጥበት ነው፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ከፅዳት ሠራተኞች ጋር በመሆን የፅዳት ዘመቻ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ሕዝብ በሚበዛባቸውና በዋና ዋና መንገዶች ላይ የኬሚካል ርጭት ይደረጋል፡፡ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አስመልክተው የመልካም ምኞት መግለጫ ያስተላልፋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ጳጉሜን አራት የምስጋና ቀን ሆኖ ኅብረተሰቡ የሚመሰጋገንበት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ሁሉም በያለበት ሆኖ እጁን በማጨብጨብ ምስጋናውን የሚገልጽበት  ሲሆን፣ የ2013 ዓ.ም. ዋዜማ ጳጉሜን አምስት ደግሞ ሁሉም ሕዝብ በይቅርታ በጀመረው ጳጉሜን አንድ ልቡን አንፅቶ ወደ 2013 የሚሸጋገርበት ‹‹የብሩህ ተስፋ ብሥራት ቀን›› ሆኖ ይከበራል፡፡ በዕለቱ በተለያዩ ሆስፒታሎች የሚገኙ ታካሚዎች ጉብኝት፣ የፖሊስ ማርሽ ባንድ ዜማዎች፣ የሞተረኞች ትርዒት የሚካሄድ ሲሆን፣ የታክሲ ማኅበራት ታክሲያቸውን በማሸብረቅ በከተማዋ እየተዘዋወሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ወ/ሮ አልፍያ ገልጸዋል፡፡

በ2009 ዓ.ም. ከነሐሴ 25 ቀን እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን በተካሄዱ የተለያዩ የአዲስ ዓመት መቀበያ መርሐ ግብሮች የተጀመረው ፕሮግራም ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ይከናወናል፡፡

በ2010 ዓ.ም. ‹‹በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር›› በሚል መርህ ጳጉሜን 1 የሰላም ቀን፣ ጳጉሜን 2 የፍቅር ቀን፣ ጳጉሜን 3 የይቅርታ ቀን፣ ጳጉሜን 4 የመደመር ቀን፣ እንዲሁም ጳጉሜን 5 የአንድነት ቀን እየተባሉ በተለያዩ መሰናዶዎች የተከበሩ ሲሆን፣ ከጳጉሜን 1 እስከ 6 በነበሩት 2011 ዓ.ም.  ጳጉሜን 1 ብልጽግና፣ ጳጉሜን 2 ሰላም፣ ጳጉሜን 3 አገራዊ ኩራት፣ ጳጉሜን 4 ዴሞክራሲ፣ ጳጉሜን 5 ፍትሕና ጳጉሜን 6 የብሔራዊ አንድነት ቀን በሚል ስያሜ መከበራቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...