Saturday, December 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ግሎባል ኢንሹራንስ ‹‹ታካፉል›› የተሰኘውን የመድን አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ግሎባል ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ታካፉል የተባለውን አዲስ የኢንሹራንስ አገልግሎት ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡

ኩባንያው የታካፉል የተሰኘውን ይህንን አገልግሎት መነሻ በማድረግ በሰጠው መግለጫ፣ ለአገልግሎቱ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘቱ በሁሉም የግሎባል ኢንሹራንስ ቅርንጫፎች በመስኮት ደረጃ አገልግሎቱን ማቅረብ እንደጀመረ አስታውቋል፡፡

በርካታ የታካፉል ኢንሹራንስ ዓይነቶች ቢኖሩም፣ ግሎባል ኢንሹራንስ የመረጠው ግን የተገልጋዮችን ፈንድ በማሰባሰብ ላይ የተመሠረተውን ታካፉል እንደሆነ የኩባንያው ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሸሪፍ ገልጸዋል፡፡

የቦርድ ሰብሳቢው ስለአገልግሎቱ እንደገለጹት፣ እንዲህ ያለው አማራጭ የኢንሹራንስ አገልግሎት በኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ታሪክ ቢኖረውም የብዙኃኑን ፍላጎት ሳያካትትና ተደራሽ ሳይሆን መቆየቱ ቁጭት አሳድሮ ነበር፡፡

የአገሪቱ የኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲሁም እየተካሄደ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ ተከትሎ ታኅሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ተግባር ላይ የዋለው አዋጅ ቁጥር 1163/2019 ተካፉልን በማካተቱ ለዘመናት ቁጭት ምላሽ የሚሰጥ ሆኖ እንደተገኘና ኩባንያውም ይህንን አገልግሎት ለመጀመር መብቃቱን አስታውቀዋል፡፡ የኢንሹራንስ ዘርፉን ደኅንነት፣ አስተማማኝነትና ፍትሐዊነት ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ማውጣቱን ተከትሎ የየምጣኔ ሀብት ዕድገት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ የሚገለጸው ይህ የኢንሹራንስ አገልግሎት፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙበት እንደሆነ ተብራርቷል፡፡

የታካፉል አገልግሎት የሸሪዓውን መርሆዎችና ሕግጋት የሚከተል የመድን ሥራ ነው፡፡ ይህ አገልግሎት የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ፍላጎት ከሃይማኖቱ የተስማማ አገልግሎት የሚቀርብበት ከወለድ ነፃ በመሆን መንገድ የሚቀርብ አማራጭ የመድን ዘርፍ ሆኖ እንደሚያገልግል ተብራርቷል፡፡

ለዘመናት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ሲቀርብለት የቆየው መደበኛው ኮንቬንሽናል የኢንሹራንስ ሥርዓት፣ ሥጋት አስተላላፊ ወለድን ስለማካተቱ በግልጽ ያልተረጋገጠ የውል ስምምነት የሚታይበትና ከቁማር ጋር የሚመሳሰል አሠራር ያለው በመሆኑ አስገዳጅ በሆኑ ምክንያቶች ሳቢያ ሕዝበ ሙስሊሙ ሲጠቀምበት መቆየቱን የቦርድ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም አዳዲስ አማራጮች ለማቅረብ የሚያመች ጊዜ በመምጣቱ የታካፉል መድን አገልግሎት መቅረብ እንደጀመረ አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ሙስሊሙ ለንብረቱና ለንግድ ግብይቱ የሸሪዓውን ሕግ የተከተለ ኢንቨስትመንት ሲያካሄድና ሌሎች ንብረቶቹም ከጉዳት እንዲጠበቁ በተካፉል ሽፋን እንደሚያገኙ ተብራርቷል፡፡

አገልግሎቱ በኢትዮጵያ አዲስ ከመሆኑ አኳያ፣ ለሥርዓቱ የሚያስፈልጉ ዕርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ከወለድ ነፃ የባንክ ሥራና የሸሪዓ መርህን የተከተለ መድን የፋይናንስ ዘርፍ በተገቢው ሕግ ሽፋን እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡ ወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎቶች እየተስፋፉ እንዲመጡ ብቁና የሠለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦት መረጋገጡ ወሳኝ ሥራ ነው፡፡ በመሆኑም የእስልምና መርህን የሚከተል የፋይናንስ ትምህርት በከፍተኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተካቶ እንዲቀርብ ለማስቻል የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች