Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናባልደራስ የአዲስ አበባ ነዋሪ በመረጠው መሪ የመተዳደር መብቱ እንዲከበር ጠየቀ

ባልደራስ የአዲስ አበባ ነዋሪ በመረጠው መሪ የመተዳደር መብቱ እንዲከበር ጠየቀ

ቀን:

አዲስ አበባ እንደ ፌዴራል መንግሥት ርዕሰ ከተማነቷ የግዛተ መሬት ባለቤትነቷ ለፌዴራል መንግሥት ሳይሆን፣ በሽግግር ወቅት እንደነበረው በክልልነት ደረጃ ዳግም እንድትዋቀር ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ጥሪ አቀረበ፡፡

‹‹ይህንንም ለማድረግ የሚያስችል ሕጋዊና ሰላማዊ ትግል በማድረግ የፌዴራል መንግሥት ጥያቄውን እንዲቀበልና በአገሪቱ አሁን ባለው ሥርዓት መሠረት ሕዝበ ውሳኔ ተካሂዶ የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡ ይህንንም ጥያቄ ዕውን ለማድረግና በሕጉ አግባብ እንዲስተናገድ ለማድረግ የከተማው ነዋሪ የስምምነት ፊርማ የማሰባሰብ ሒደት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን፤›› በማለት፣ የከተማው ነዋሪዎች አዲስ አበባ ክልል እንድትሆን የሚጠይቀውን የድጋፍ ፊርማ በመፈረም ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ፓርቲው ይህን ጥሪ ያቀረበው ማክሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በዋና ጽሕፈት ቤቱ፣ ‹‹አዲስ አበባ በራሷ ግዛተ መሬት ላይ የፌዴራል አድያምነት (ክልልነት) መብት ሊረጋገጥላት ይገባል›› በሚል ርዕስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

እዚያው ተወልዶ ያደገውንና ከአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የመጣውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ አንድ ብሔረሰብንና አንድ ቋንቋ ተናጋሪነትን መሠረት አድርጎ በተዋቀረ ክልል ውስጥ አስገብቶ እንዲተዳደር ማድረግ ፍትሐዊነት የለውም የሚለው ባልደራስ፣ ‹‹የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥያቄ ከራሴ ውጪ በእኔ ዕጣ ሌላ ሊወስንብኝ አይገባም የሚል ነው፤›› በማለት፣ የከተማው ነዋሪ በመረጠው መሪ የመተዳደር መብቱ ሊከበር እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

የአዲስ አበባ ራሷን የማስተዳደር መብት በሕገ መንግሥቱ የታወቀ ቢሆንም፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጭምር ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ውክልና እንደሌላት የሚገልጸው ፓርቲው፣ ‹‹ገዥ ፓርቲዎች  ፍላጎታቸውን የሚጭኑባት ከተማ ናት›› በማለት፣ ‹‹ይህ ሁኔታ የከተማዋ ነዋሪዎች በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸውን ራሳቸውን የማስተዳደር መብት ፍፁም የሚጥስ ነው፤›› ሲልም ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች የራሳቸውን መሪ የመምረጥ መብትን ለማረጋገጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን መገንዘቡን የገለጸው ባልደራስ፣ ይህን ለማሳካትና መንግሥት ላይ ጫና ለማድረግ ከጳጉሜን 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች መንግሥትን የሚጠይቁበት የድጋፍ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ይፋ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት ሦስት ዘርፎችን የያዘ ግብረ ኃይል ማዋቀሩን የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ሰለሞን ጌታነህ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡ እነዚህ ሦስት ግብረ ኃይሎች ደግሞ ሕጋዊ መንገድን ተከትሎ ትግሉን ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያደርስ፣ ሕዝቡን ተሳታፊ ለማድረግ የድጋፍ ፊርማ የሚያሰባስብና ሕዝባዊ ውይይት፣ ኮንፈረንስና ዓውደ ጥናት የሚያዘጋጅ ኮሚቴ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ፓርቲው ሕዝቡን አንቀሳቅሶ ለማቅረብ ከተዘጋጀው የሕዝበ ውሳኔ ሐሳብ በተጨማሪ፣ ስለከተማዋ ያገባናል የሚሉ ሁሉ እንቅስቃሴውን እንዲደግፉም ጥሪ አስተላልፏል፡፡

‹‹ባልደራስ የከተማችንን ነዋሪ የሚመጥን አስተዳደር እንዲዘረጋ የሚያደርገው ጥረት ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥያቄ በላይ እንደሆነ ያምናል፡፡ በመሆኑም በአገራችን የምትገኙ የፖለቲካ ኃይሎች የከተማዋ ነዋሪ የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲመሠርት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ትብብር እንድታደርጉለት፡፡ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችም የሚመሠረተው አስተዳደር የሚያስፈልገውን ድጋፍና አወቃቀር በአግባቡ መልክ ለማስያዝ የሚረዳ ልምዳችሁን፣ ዕውቀታችሁን፣ እንዲሁም ተፅዕኖ የመፍጠር አቅማችሁን አበርክቱ፤›› በማለት ጥሪ አስተላልፏል፡፡

‹‹መንግሥት በማናለብኝነት ያለ ኃጥያታቸው አስሯቸው የሚገኙ ንፁኃን መሪዎቻችንንና አባላቶቻችንን በአስቸኳይ ይፍታ፤›› ሲልም ባልደራስ ጠይቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...