Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየፌዴራል መንግሥቱ ‹‹ዋጋ አልባ›› ያለው የትግራይ ምርጫ ተካሄደ

የፌዴራል መንግሥቱ ‹‹ዋጋ አልባ›› ያለው የትግራይ ምርጫ ተካሄደ

ቀን:

በነአምን አሸናፊና ዮሐንስ አንበርብር

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የሚካሄደው ክልላዊ ምርጫ ኢሕገ መንግሥታዊና ዋጋ አልባ ነው ባለ ማግሥት፣ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ክልላዊ ምርጫውን ረቡዕ ጳጉሜን 4 ቀን 2012 ዓ.ም. አካሄደ፡፡

ባለፈው ሳምንት ለተካሄደው የክልል ምርጫ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በዕለቱም በ2,672 የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምፃቸውን ሲሰጡ መዋላቸውን ከክልሉ የወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከተመዘገቡ መራጮች መካከል ከ97 በመቶ በላይ የሚሆኑት በዕለቱ ድምፃቸውን መስጠታቸውን የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነ ማርያም ያስታወቁ ሲሆን፣ አጠቃላይ የምርጫው ውጤትም መስከረም 2 ወይም 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

በምርጫው የክልሉ ገዥ ፓርቲ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ን ጨምሮ፣ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችና አራት የግል ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ በኢትዮጵያ ሊደረግ የነበረው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የወረርሽኙ ጫና እስኪቀንስ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን፣ ይህን ውሳኔ ተከትሎም የትግራይ ክልል ምርጫውን በተያዘለት ጊዜ አካሂዳለሁ በሚለው አቋሙ በመፅናቱ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ሻክሯል፡፡

ከዚህ ጋር የክልሉ ምርጫ ‹‹ሕገ መንግሥቱን ይጥሳል›› የሚለው ሙግት፣ እንዲሁም ‹‹ምርጫው አለመካሄዱ ነው የሕገ መንግሥት ጥሰት›› የሚለው ክርክር ለበርካታ ወራት ሲንከባለል የሰነበተ ጉዳይ ነው፡፡

ከዚህ አንፃር የሕገ መንግሥት ምሁሩና ሕገ መንግሥትን የመተርጎም ሒደት ተሳታፊ የነበሩት አደም ካሴ (ዶ/ር)፣ ክርክሩ መቋጫ ያገኘ እንደሆነ ያመላክታሉ፡፡

‹‹በፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ ባንስማማም ብንስማማም ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔውን ሰጥቷል፡፡ ውሳኔውም ምርጫው ኢሕገ መንግሥታዊ ነው የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በኋላ ምርጫውን የተመለከተ መከራከሪያ የሚሆነው ከሕገ መንግሥቱ ውጪ ባሉ መርሆዎች (Extra Constitutional Principles ነው)፤›› በማለት፣ ቀጣዩ ሒደት በሕገ መንግሥት መርሆዎች ብቻ ሊፈታ የሚችል እንዳልሆነ አመላክተዋል፡፡

ምንም እንኳን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫውን ኢሕገ መንግሥታዊ ነው ቢለውም፣ የትግራይ ክልል ምርጫ ከማካሄድ አልገደበውም፡፡ ከዚህ አንፃር ምን ዓይነት ዕርምጃ ሊወሰድ ይችላል የሚለውን በተመለከተ ደግሞ፣ ‹‹የፌዴራል መንግሥቱ አደገኛ የሆነ አካሄድ ይከተላል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስትራቴጂው ቆይተን እንመልከተው የሚል ይመስላል፡፡ ይህም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተነሳበት ከዘጠኝ እስከ 12 ወራት ምርጫ ሊካሄድ ስለሚችል፣ ያኔ ያለው ውጥረት ሊረግብ ይችላል፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

አሁን የሚስተዋለውን ፍጥጫ እንዴት ነው መፍታት የሚቻለው ለሚለው የብዙዎች ጥያቄ ‹‹መፍትሔው ይኼ ነው›› ለማለት እንደሚከብድ የገለጹት አደም (ዶ/ር)፣ ‹‹አንደኛው መንገድ ግን የሕገ መንግሥቱን ማዕቀፍ ማክበር ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይም መግባባት አልታየም፡፡ የተጀመሩት ንግግሮች አካታችና እውነተኛ ከሆኑ ምን አልባት ራሱ ዕድል ሊፈጠር ይችላል፤›› በማለት አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን ኃይል የመጠቀም ሁኔታ ሊኖር ይችላል በሚል በብዙዎች የሚገለጸውን አስተያየት በማጣጣል፣ የትግራይ ክልል ልገንጠል ካላለ ይህ የማይመስል መሆኑን በመግለጽ፣ ‹‹እርግጠኛ ነኝ በሚያስብል ደረጃ ኃይል የመጠቀም ዕርምጃ የማይመስል ነው፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...