Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርይድረስ ለሪፖርተር

ይድረስ ለሪፖርተር

ቀን:

ይድረስ ለሪፖርተር ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እንደምን አላችሁ እኔ ደህና ነኝ ጋዜጣችሁን ታትሞ በወጣ ቁጥር አያመልጠኝም አነባለሁ፡፡ በትኩስ ኢንፎርሜሽን ፈጣን ነው፡፡ ስለ ጋዜጣው ይህንን ካልኩኝ ወደ ዋና አጀንዳዬ ልውሰዳችሁ፡፡

እኔ የምሠራው በአንድ የግል ኤጀንሲ የባንክ ጥበቃ ነው፡፡ በአጋር ኤጀንሲ ውስጥ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በጥበቃው ዙሪያ ያለውን ብልሹ አሠራር ልጠቁማችሁና የሚመለከተውን ብታነጋግሩ ብዬ ነው፡፡ ኤጀንሲው ከቀጠረ በኋላ የት ወደቃችሁ ምን ችግር አለ ወይ ብሎ የሚጠይቅ አካል የለም፡፡ ደመወዝ የሚሰጠው በባንክ ሲሆን፣ ለምን እንደተቆረጠ እንኳን ማንንም መጠየቅ አይቻልም፡፡

ቋሚ ሠራተኛ ነህ ተብሎ ብዙ ዓመት የሠሩ የደመወዝ ጭማሪ የለም፡፡ ለምሳሌ 1,800 ብር የሚባል ከአራትና ከአምስት ዓመት በኋላ ያችው 1,800 ብር የሚባል ነች፡፡ ጥቅማ ጥቅም የሚባል የለም፡፡ ሁለተኛ ባንክ የሚጠብቅ ጥበቃ ለምሳሌ ቡና ከሆነ የሚጠብቀው ደመወዙ 1,800 ብር ነው፡፡ ግን ለጥበቃው የሚከፈለው 1,600 ብር ነው፡፡ ለምንድነው ብሎ ሲጠየቅ ሁለተኛ ጥበቃህ ስለሆነ ነው ይሉታል፡፡ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የሠራተኛና ማኅበራዊ ሚኒስቴር የሰው ሀብት አመራሩን አነጋግረው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል ምንም መፍትሔ የለም፡፡ ሕግ ባለበት አገር የሠለጠነ ጉልበት ብዝበዛ ነው ያለው፡፡ እሰኪ እናንተ በመርካቶ በየባንኩ ዘወር ዘወር ብላችሁ ብትጠይቁ ሀቁን ታገኙታላችሁ፡፡ ማስረጃ ግብዓትም ታገኛላችሁ፡፡ ሚሊተሪ ተራ፣ ጎጃም በረንዳ፣ መርካቶ በወንበር ተራ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጋገን ባንክ፣ ኅብረት ባንክ፣ ዓባይ ባንክ፣ ቡና ባንክ፣ እናት ባንክና አዲስ ባንክ ከብዙ በጥቂቱ አነጋግሩ፡፡ በመጨረሻ ይመለከታል ለምትሉት በማነጋገር አንድ ነገር ይዛችሁ እንደምትመጡ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ለእናንተ የጻፍኩት አቤት የሚባልበት በመጥፋቱ ነው፡፡ በቸር ሰንብቱ መልካም ሥራ ይሁንላችሁ፡፡

ጮራ፣  ከአዲስ አበባ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...