Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የካቢኔ ሽግሽግ በማድረግ ሹመቶችን ሰጡ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የካቢኔ ሽግሽግ በማድረግ ሹመቶችን ሰጡ

ቀን:

በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ እንዲያስተዳድሩና እንዲመሩ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙት / አዳነች አቤቤ፣ በካቢኔያቸው ላይ ሽግሽግ በማድረግ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጡ። 

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙትን የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማን (ኢንጂነር) ተክተው ከተማዋን በምክትል ከንቲባነት እንዲመሩ የተሾሙት፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የነበሩት / አዳነች፣ የካቢኔ ሽግሽግ በማድረግ ሹመቶችን የሰጡት ማክሰኞ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም. መሆኑን ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። 

ምክትል ከንቲባዋ ለስምንት አመራሮች ሹመትና የተለየ የኃላፊነት ምደባ አድርገዋል። የሹመቶቹና አዳዲስ ምደባዎቹ ዋና ዓላማ፣ ምክትል ከንቲባዋ የጀመሩትን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ እንደሆነ የከተማ አስተዳደሩ የገለጸ ሲሆን፣ ‹‹በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱ የሕዝብ ቅሬታዎችን ለመመለስ የአመራር ሽግሽግና አዳዲስ የሥራ ሥምሪት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፤›› ብሏል። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የነዋሪዎች ቅሬታ የሚሰማባቸው እንደሆኑ ከሚጠቀሱት የከተማዋ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ሁለቱየገቢዎች ቢሮና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አዳዲስ አመራሮች አግኝተዋል። 

በዚህም መሠረት የከተማ አስተዳደሩ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ ተነስተው፣ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ መሾማቸው ታውቋል። አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ከዚህ ቀደም የከተማ አስተዳደሩ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። 

አቶ ሙሉጌታ ይመሩት የነበረውን የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲመሩ ደግሞ አቶ ተፈራ ሞላ ተሹመዋል። አቶ ተፈራ ሞላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። 

ከአስተዳደሩ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊነት የተነሱት አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ በቢሮ ኃላፊነት ማዕረግ የምክትል ከንቲባዋ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ ሆነው ተመድበዋል።  ከእነዚህ በተጨማሪም የቦሌ ክፎለ ከተማና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈጻሚዎች ተነስተው፣ በአዲስ አመራሮች የተተኩ መሆኑን የአስተዳደሩ መረጃ ያመለክታል። 

በዚህም መሠረት የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ አቶ መኰንን አምባዬ ሲሾሙአቶ ጀማል ረዲ ደግሞ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል። 

ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚነት የተነሱት አቶ የትናየት ሙሉጌታ፣ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል። 

ከዚህ በተጨማሪ አቶ ተተካ በቀለ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የምክትል ከንቲባዋ አደረጃጀት አማካሪ ሆነው የተመደቡ ሲሆንአቶ ጥላሁን ፍቃዱ በተመሳሳይ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የምክትል ከንቲባዋማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ተመድበዋል። 

ተሿሚዎቹ የተሰጣቸው ኃላፊነት የሕዝብ አገልጋይነት መሆኑን በመረዳት፣ ሕዝቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ ምክትል ከንቲባ አዳነች ማሳሰባቸው ታውቋል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...