Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምከሩሲያ ድጋፍ ከአገር ውስጥ ተቃውሞ ያስተናገዱት የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

ከሩሲያ ድጋፍ ከአገር ውስጥ ተቃውሞ ያስተናገዱት የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

ቀን:

የቤላሩስ ዋና ከተማ ሚኒስክ በየሳምንቱ እሑድ በመቶ ሺሕ የሚጠጉ ተቃውሞ ሠልፈኞችን ማስተናገድ ከጀመረች አምስተኛ እሑዷን መስከረም 3 ቀን 2013 ዓ.ም. አስቆጥራለች፡፡ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ደግሞ በሌሎች ከተሞች በመውጣት በምሥራቅ አውሮፓ የምትገኘውን ቤላሩስን ለ26 ዓመታት የመሩት ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከሥልጣን እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፖሊስ ዋና አካባቢዎችን በመዝጋትና ከ400 በላይ ተቃዋሚዎችን በማሰር ዕርምጃ ቢወስድም፣ ቤላሩሳውያኑን ከተቃውሞ መግታት አልቻለም፡፡

ከወር በፊት በቤላሩስ የተካሄደውን አወዛጋቢ ምርጫ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ፣ ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ ከሥልጣን ይልቀቁ የሚል አጀንዳን አንግቧል፡፡ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን ተቃውሞ ያልተቀበሉት የ66 ዓመቱ ሉካሺንኮ፣ ቤላሩስን እንደሚከላከሉ የገለጹ ሲሆን ፖሊስም በተቃዋሚዎች ላይ ዕርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መታሰራቸውንና መሰደዳቸውንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ፖሊስ በሚኒስክና በተለያዩ የቤላሩስ ከተሞች የሚገኙ የተቃውሞ መሪዎችን ያሰረ ሲሆን፣ የአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ‹‹የታሰሩት ስድብ አዘል መፈክርና ያልተገባ ሰንደቅ ዓላማ የያዙ ናቸው›› ብሏል፡፡

ከሩሲያ ድጋፍ ከአገር ውስጥ ተቃውሞ ያስተናገዱት የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

በሕዝባቸው የገማቸውን ተቃውሞ ለማርገብ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሩሲያ ሶቺ የመከሩት ሉካሼንኮ፣ ከፑቲን ጋር ከነበራቸው ውይይት በኋላ ግን የአገራቸውን ሕገ መንግሥት እንደሚያሻሽሉ ከዓመታት በፊት ተናግረው የነበረ ቢሆንም ይህንን ባለማድረጋቸውም ሲተቹ ነበር፡፡ ሕገ መንግሥቱን ለመቀየር ማቀዳቸውን አስታውቀዋል፡፡ የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የቤላሩስ ፕሬዚዳንት ቀጣዩን የፕሬዚዳንት ምርጫ ቀደም ብለው ለማድረግ መወሰናቸውንም ተናግረዋል፡፡

አልጀዚራ በሶቺ የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ እንዳለው፣ ፕሬዚዳንቱ ከፑቲን ጋር የተወያዩት በአገር ቤት በገጠማቸው ተቃውሞና በቤላሩስ ድንበር በሚገኙት የሩሲያ ወታደሮች ዙሪያ ነው፡፡

ፔስኮቭ እንዳሉት፣ በቤላሩስ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ከሕገ መንግሥት ውጪ እንዲሆን ሩሲያ አትፈልግም፡፡ በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ መከናወን አለበት ብላም ታምናለች፡፡

ቤላሩስ በኢክኖሚውና በፖለቲካው የተደቀነባትን ቀውስ ለመወጣት ሪፎርም እንደሚያስፈልጋት ተቃዋሚዎች ሲገልጹ መክረማቸውን ተከትሎም ፕሬዚዳንቱ በሶቺ በነበራቸው ውይይት ማሻሻያዎች እንደሚያደርጉ በደፈናው ተናግረዋል፡፡

ሉካሼንኮ አሁን እቀይረዋለሁ ብለው የተናገሩት ሕገ መንግሥት፣ ተቃዋሚዎች ሕገ መንግሥቱ ወደነበረበት እንዲመለስ ሲጠይቁ ነው የከረሙት፡፡ ሕገ መንግሥቱ የተሻሻለው የፕሬዚዳንትነትን ሥልጣን ለማራዘምና ኃላፊነትን ለማብዛት ነበር፡፡

በምርጫ ማሸነፋቸውን የቤላሩስ ምርጫ አስፈጻሚ ከገለፁ በኋላ ሩሲያ ሕጋዊ ያለቻቸው ቢሆንም፣ በቤላሩስ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላት የፕሬዚዳንቱ ተቀናቃኝ  ስቪትላና ቲካኖቪስኪያ በምርጫው ማሸነፏን ገልጻለች፡፡

የቤላሩስ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሚስተር ሉካሼንኮ 80 በመቶ ምርጫ እንዳገኙ ሲገልጹ፣ ሚስ ቲካኖሺሽካ ከ60 በመቶ እስከ 70 በመቶ ያለውን ማሸነፏን አሳውቃለች፡፡ ተቃውሞ ሠልፍ አድራጊዎችም እሷን በመደገፍ ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን ይልቀቁ ብለዋል፡፡

የቤላሩስ መንግሥት አብዛኞቹ የቤላሩስ ዜግነት ያላቸውን ጋዜጠኞች ፈቃደ ሰርዟል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የቢቢሲ ሩሲያ አገልግሎት ሁለት ጋዜጠኞች እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በቤላሩስ የነገሠውን ተቃውሞ ለማርገብ ሩሲያ ደርሰው የመከሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ሞስኮ ቤላሩስ ድንበር የሚገኘውን ተጠባባቂ ወታደር እንድታስወጣም ከስምምነት ደርሰዋል ተብሏል፡፡

ሩሲያ የቤላሩስ ምርጫ እንዲረበሽ እየሠራች ነው ሲሉ ከዚህ ቀደም የወነጀሉት የቤላሩሱ ፕሬዚዳንት፣ አሁን ላይ ከተቃውሞው ኋላ ምዕራባውያን አሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ምዕራባውያን መንግሥታቸውን በማፍረስ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ሩሲያ ድንበር ድረስ እንዲዘልቅ እየሠሩ ነው ቢሉም፣ ኔቶ ውንጀላውን አጣጥሎታል፡፡

ከሩሲያ ድጋፍ ከአገር ውስጥ ተቃውሞ ያስተናገዱት የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...

ወዘተ

ገና! ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤ ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ። በዳዴ ዘመኔም፣ በ'ወፌ ቆመችም!'፤ አውዴ ክፉ ነበር...