Friday, December 1, 2023

የኮቪድ ወረርሽኝ እያለ ሀገራዊ ምርጫውን ማኬሄድ እንደሚቻል ጤና ሚንስቴር ገለጸ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የጤና ጥበቃ ሚንስቴር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እያለ ሀገር አቀፍ ምርጫውን ማኬሄድ እንጀሚቻል ገለጸ ።

የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዛሬ መስከረም 8 ቀን 2012 ዓም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ ሪፖርትና ምክረሀሳብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው ይህንን ያለው።

የትግራይ ተወካይ የሆኑት ገብረእግዚአብሔር አርአያ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳር በሌለበት ምርጫው መካሄድ የለበትም ብለዋል።

የጤና ሚንስቴር ባቀረበው ሪፖርት እና ምክረሀሳብ ላይ የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክረ ሀሳቦቹን በዝርዝር መርምረው በቀጣይ የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርቡለት ምክር ቤቱ ወስኗል።

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -