Saturday, March 2, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኦሊምፒክ ኮሚቴ ለቶኪዮ 2020 ዝግጅት ጀመረ

ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለቶኪዮ 2020 ዝግጅት ጀመረ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ‹‹ተደረገም አልተደረገም›› በሚል ከስድስት ወራት በፊት ተዋቅሮ የነበረው ብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴ ቀደም ሲል ባቀደው መሠረት ሥራ እንዲጀምር ማድረጉን አስታወቀ፡፡ በወቅቱ ከተቋቋመው ብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴው መካከል ከተለያዩ የጤና ተቋማት ተዋቅሮ የነበረው የሕክምና ኮሚቴ ባለፈው ዓርብ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ዓርብ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ፣ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ ሕክምና ኮሚቴው ጸሐፊ ሕይወት ዘላለም (ዶ/ር) በጋዜጣዊ መግለጫው እንደተናገሩት ከሆነ፣ አትሌቲክሱን ጨምሮ ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተመረጡ ብሔራዊ አትሌቶች ዝግጅት እንዲጀምሩ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንደየ ባህሪያቸው ወደ ውድድር እንዲገቡ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ዶ/ር ሕይወት ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የጤና ችግር በተመለከተ ጸሐፊዋ እንደገለጹት፣ በአጠቃላይ ሕክምናውን የሚመራው ቡድን ሰባት ዶክተሮች የተካተቱበት ብሔራዊ የሕክምናና የሥነ ምግብ እንዲሁም የሥነ ልቦናና መሰል ባለሙያዎች ያቀፈ ነው፣ አትሌቶች በካምፕ አልያም በሆቴል ተሰባስበው ዝግጅት እንዲጀምሩ ቢደረግ፣ ለጤናቸው ሲባል አቅሙም ብቃቱም ያላቸው ወጌሻዎች፣ የሥነ አዕምሮ፣ የሥነ ምግብና ጠቅላላ ሐኪሞች ክትትል የሚያደርጉላቸው ባለሙያዎች ናቸው ያሉት ዶ/ር ሕይወት የጤና ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ግብረ ኃይል መቋቋሙንም አስረድተዋል፡፡

ከሕክምናው በተጨማሪ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥር ‹‹የኢትዮጵያ ስፖርት ሕክምና ኅብረት›› በሚል ማኅበር እንዲቋቋም መደረጉን ያስረዱት ደ/ር ሕይወት፣ የኅብረቱ ዓላማም የስፖርት ባለሙያውን በአካል ብቃትና በሥልጠና የተሻለ የመጀመርያ ደረጃ ሕክምና መስጠት እንዲችል ማድረግ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ሳይንሳዊ ሥልጠናዎችንና የምርምር ሥራዎችን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ተሞክሮ በመውሰድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲለመዱና እንዲሠራባቸው መደላድሎች እየተመቻቸ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹ይህ መግለጫ በዋናነት የ2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት እንዲጀመር የሚያስችሉ ቀደም ሲል የተቀመጡ አቅጣጫዎች መነሻ ያደረገ ከመሆኑ ባሻገር፣ ችግሮች እንዳይፈጠሩ መፍትሔዎችም እንዲቀመጡ ተደርጓል፤›› ያሉት ሌላዋ የሕክምና ቡድኑ አባል ቃልኪዳን ዘገየ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

እንደ ዶ/ር ቃልኪዳን ከሆነ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ካልሆነ ሌሎች አገሮች አትሌቶቻቸው ሥራቸውን እየሠሩ ለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለዚህም ቀደም ሲል በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተይዘው የነበሩ በርካታ የዓለም ክብረ ወሰኖች በሌሎች መወሰዳቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ ሌላው የሕክምና ቡድኑ አባል ኃይሉ ሰይፉ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የቫይረሱ ባህሪ በየጊዜው ተለዋዋጭ እንደ መሆኑ መጠን የሕክምና ባለሙያዎች በጊዜ ሒደት ወረርሽኙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍበትን መንገድ በበቂ ሁኔታ መቆጣጠር በሚያስችል አቅም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ወረርሽኙ ባለበትም ቢሆን ከዕለት ዕለት ሥራው ጎን ለጎን ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የሚያስፈልገውን ዝግጅት ሲያከናውን መቆየቱን የገለጹት፣ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ዋና ጸሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው ብሔራዊ የሕክምና ቡድን የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑንም አውስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቀደም ሲል ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ከተቋቋመው ብሔራዊ የዝግጅትና የቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ያወጣው የዝግጅት መርሐ ግብር እንዲቋረጥ የተደረገው፣ ‹‹የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሔ ሳያገኝ ብሔራዊ አትሌቶችን በሆቴል አሰባስቦ ዝግጅት ለማድረግ መሞከር የአትሌቶቹን ሕይወት ለአደጋ እንደማጋለጥ ነው›› በሚል የቀረበበትን ትችት በመፍራት እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በወቅቱ ይቀርብ የነበረውን ሥጋት ከግምት በማስገባት ለብሔራዊ ዝግጅት የተጠሩትን ጨምሮ በርካታ አትሌቶች ከወትሮ እንቅስቃሴያቸው ተቆጥበው፣ አንዳንዶቹ በግላቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ የወትሮ ልምምዳቸውን ከነአካቴው አቋርጠው ወደየ ቤተሰቦቻቸው የሄዱበት አጋጣሚ እንዳለ የሚናገሩም ነበሩ፡፡

በዚህም የተነሳ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተይዘው ከነበሩ የዓለም ክብረ ወሰኖች መካከል አራቱ ክብረ ወሰኖች በሌሎች አገሮች አትሌቶች እንዲነጠቁ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከነዚህ ክብረ ወሰኖች መካከል በቀነኒሳ በቀለ አማካይነት ለ16 ዓመታት ያህል ተይዞ የቆየው የ5,000 ሜትር ክብረ ወሰን፣ በኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተይዞ የነበረው የአንድ ሰዓት ክብረ ወሰን፣ በተመሳሳይ ርቀት በድሬ ቱኔ ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰንና በነፃነት ጉደታ ተይዞ የነበረው ግማሽ ማራቶን (21 ኪሎ ሜትር) ክብረ ወሰን ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...