Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉየጎጠኞች ትርክት አመጣጡና መዘዙ

የጎጠኞች ትርክት አመጣጡና መዘዙ

ቀን:

በመስፍን ሀብቱ

አሁን የአገራችንን የፖለቲካ ሁኔታ ምስቅልቅሉን አውጥቶ፣ የዝቦቿንም ደንነት አደጋ ላይ ጥሎ ገሪቱም ላይ የመከፋፈል አደጋ ያመጣው ‹‹የጎጠኞች›› አክራሪነት ለመሆኑ ማመሳከሪያ የሚያስፈልገው አይደለም። እነ ጃዋር በሚያስገርም ድንፋታ ‹‹ከፈለግሁ ኦሮሚያን በሁለት ወር እገነጥላለሁ፤›› እንዲሉ ያበቃቸው ጽንፈኝነት ከየት እንደመጣ መረዳቱ በአንድ በኩል ወደፊት እንደዚህ ያሉ ጽንፈኞች እንዳይነሱ ሲረዳ በሌላ በኩልም መንግትና ብረሰቡ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም ሊያስገነዝብ ይችላል።

በአገራችን የፖለቲካ ውይይቶችን አስቸጋሪ የሚያደርገው የአንዳንድ ጽንፈኛ ‹‹የብ›› ፖለቲከኞች ያልታወጀው ዓላማቸው እየተደባበሰ ስለሚቀርብነዚህ ፖለቲካኞች ርግጠኛ ዓላማ ምን እንደሆነ ቆመንልሃል ላሉት ዝብ እንኳ በግልጽ አለመናገራቸው ነው። ጎጠኛ ጽንፈኞች በአብላጫው ውር አጀንዳ አላቸው። ይ ውር አጀንዳቸው ግልጽ የሚሆነው ኃይላቸውን አጠናክረው ልጣን ለመያዝ እንችላለን ብለው በሚገምቱበት ጊዜ ወይም በመጨረሻ ልጣን ሲይዙ ነው። ይኼ ክስተት ብዙ ጊዜ በብር ጽንፈኞች ላይ ይከሰታል። በአገራችንም የሆነው እንደዚሁ ነው። በአገራችን የተነሱት ጎጠኛ ጽንፈኞች የተለያየ መልክ ይዘው መጥተዋል። ይህ ጽንፈኝነት እንዴት መጣ? የዘንድሮዎቹ ጽንፈኞችስ እንዴት ወደዚህ አመለካከት አቀኑ? እንዴትስ በወጣቱ ዘንድ ተደማጭ ሊሆኑ ቻሉ? የሚ ጥያቄዎችን ማንሳት ተገቢ ይሆናል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የብሔር ጥያቄ አነሳ

አሁን ጽንፈኛ ጎጠኞች በአገሪቱ ላይ በደቀኑት አደጋ፣ ባስከተሉት ከፍተኛ ጉዳትና በተለይም ደግሞ ሳዩት አንፍጋፊ ጭካኔና ግድያ የተነሳ ብዙ ዝብ የብሔር ጥያቄን ‹‹አታንሱብኝ›› ወደሚል ሄዷል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር አገር እስከሆነች ድረስ የብሔር ጥያቄ መኖሩ የማቀር ነው። ጽንፈኞች ጉዳዩን ስላበላሹት ጉዳዩ እንዳይነሳ አይባልም። በታሪክም ቢሆን በርካታ ጸፊዎችና አንዳንድ ጋዜጠኞች እንደሚሰብኩት የብሔር ጥያቄ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ዘመን አልተነሳም። የብሔር ችግር ከተጻፉት መጻፍት እንኳ ብንነሳ (የብሔር ጥያቄ ወይም ችግር ባይሉትም) ገና ከአ ቴዎድሮስ ጊዜ ጀምሮ ያለ ነው። አገሪቱ በጣያኖች በተወረረችበት ወቅት ቤልጂያኖች ሩዋንዳ ውስጥ እንዳደረጉት ለከፋፍለህ ግዛ እንዲመቻቸው ጣያኖች ዝባችንን በብሔር ከፋፍለውት ነበር። በግልጽ እንነጋገር ከተባለ ባንዳው ሁላ በጣያን ፋሺስቶች እንደለጠነ (ምናልባት ስፓጌቲ በሹካ መብካት ስለተማረ!! ይኼም ልጣኔ ሆኖ!) በድ ያን ኢትዮጵያም አያሌ የብሔር አመች ነበሩ (ኤርትራ፣ ኦሮሞ፣ ጌዴዎ፣ ማሌ ሲዳማ… ወዘተ)። ወደ 1960ዎቹ ገደማ ደግሞ የኤርትራኢትዮጵያ ፌዴሬሽን በመፍረሱ ምክንያት በኤርትራ የተነሳው አመ ከፖለቲካም አልፎ የብረት ትግል ይዞ መጣና ወደፊት ለሚነሱት ‹‹የብሔር እንቅስቃሴዎች›› አዲስ ይትብሃል ፈጠረ።

የተማሪው እንቅስቃሴ በጋመበት ወቅት የመንግቱ መከላከያ ኃይሎች በኤርትራና በባሌ የተነሱትን አመች ለማጥፋት በገፍ ተመድበው ጦርነት ላይ ነበሩ። በመንግት ደረጃም የኢትዮጵያና ሊያ መንግታት በኦጋዴን ጥያቄ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት አድርገዋል። እነዚህ የፖለቲካ ችግሮች ዞሮ ዞሮ የአገሪቱን አንድነት የሚመለከቱ በመሆናቸው (ቢያንስ የኤርትራና የኦጋዴን የመገንጠል አደጋ ገሃድ ስለነበር) የተማሪው እንቅስቃሴ ስለችግሮቹ መወያየት ከጀመረ በኋላ ያንን የፖለቲካ ችግር ‹‹የብሔር ጥያቄ›› በማለት አነሳው። ኢትዮጵያ የብዙ ብሮች አገር መሆኗን፣ እነዚህ ብሔሮች በእኩልነት መኖር እንዳለባቸው ስለዚህም የራሳቸውን ድል በሳቸው የመወሰን መብት ሊኖራቸው ይገባል አለ። በተረፈ ተራማጆችና በሁሉም ብሔር እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ሞክራቶች በኩልነት ላይ ለተመረተች ኢትዮጵያ መታገል እንዳለባቸው አሳሰበ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይኼን እንዳሉ በመንግሥት ትንኮሳ የተማሪው ማበር ፕሬዚዳንት ጥላሁን ግዛው በመንግሥት ተገድሎ ሌሎች ተማሪዎችም ተረሽነዋል። ታስረው የተደበደቡም በርካቶች ናቸው። በዚህ ጭፍጨፋ የተነሳ ዩኒቨርሲቲውም በመዘጋቱ የብሔር ጥያቄ ገና ካነሳሱ በርካታው ተማሪ የተሳተፈበት ውይይት ሳይደረግ ቀረ። ከዚያ በኋላ በአውሮፓ ያሉ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በ1963 ዓ.ም. በርሊን ላይ ተሰብስበው ከአንድ ሳምንት በላይ ከተከራከሩ በኋላ በአብላጫ ድም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወሰዱትን ዓይነት ውሳኔ አሳለፉ። በዚያኑ ጊዜም ሰሜን አሜሪካ ያሉትም እንዲሁ ተመሳሳይ ውሳኔ አሳለፉ።

በወቅቱ የአገሪቱ የፖለቲካ አጀንዳ የነበረው በኤርትራ የተጀመረው የትጥቅ ትግልና በኦጋዴን ብልጭ ድርግም የሚለው ጦርነት ስለነበር በተለይም በኤርትራው እንቅስቃሴ ላይ ውሳኔ ማሳለፍ አስፈላጊ ስለነበር የተማሪዎቹ ማበራት (በአውሮፓና አሜሪካ) የኤርትራን ሕዝብ ትግል ቢደግፉም (ጭቆናን በመቃወም የተደረገ ትግል በመሆኑ) መገንጠሉን ግን አልደገፉም። በተማሪዎቹ ምልከታ በጊዜው ጉዳዩ ራስን በራስ የማስተዳደር ኮንቴክስት ሊታይ የቻለው የኤርትራው ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄውን ከተወያየበት በኋላ በጊዜው መገንጠሉን አልደገፉም። እዚህ ላይ አንድ ጉዳይ ግልጽ እናድርግ። በተራማጆች አመለካከት መረት የብሔር ንቅናቄ ጭቆናን ተቃውሞ እስከተነሳ ድረስ ይደገፋል። ይሁን እንጂ ያ እንቅስቃሴ የዚያን ብሔር ችግር ሁሉ ይፈታል ማለት ስላልሆነ (በታሪክ የታዩ የብሔር እንቅስቃሴዎች የዝቦቻቸውን ዋና ዋና ችግሮች ሲፈቱ አልታዩምና) እንቅስቃሴው ቢደገፍም መገንጠሉ አይደገፍም። ተራማጆች እንዲህ ዳር ቁጭ ብለው ይ ይደገፍ ያ አይደገፍ የሚሉ ሳይሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ቆርጠው ይነሳሉ። ከዚህም አንደኛው የተነሱት የብሔር እንቅስቃሴዎች የነነት ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ ብቻ ሳይሆን በተቻለ መጠን የዝቡን ዋና ዋና ችግሮች ለመፍታትም እንዲሩ ለማድረግ ይጥራሉ። ከነዚህ ራዎች አንደኛው አብዮታዊ እንቅስቃሴ በመጀመር የብሔር እንቅስቃሴዎችም የዚህ ተራማጅ አካል እንዲሆኑ ማድረግ ነው (በጊዜው ከተጻፉት የተማሪ እንቅስቃሴዎች ጽፎች የምናነበው ይኼንኑ ነው። የዋለልኝ መኮንንና የብርሃነ መስቀል ረዳን ጽፎች ለዋቢነት እንጠቅሳለን)። ይሁን እንጂ የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ተራማጆቹ እንዳሰቡት ሳይሄድ ቀረና ‹‹የብሔር ድርጅቶች ነን›› የሚሉት የፖለቲካ መድረኩን ሲወስዱ ትርክቶቹም እየተቀያየሩ መጡ።

የጎች ትርክት አጀማመር

አውሮፓ ያሉ ተማሪዎች ያንን ውሳኔ ባሳለፉበት ወቅት ከተማሪው ንቅናቄ ወጥተው ሬቮሉሽናዊ ድርጅት ለማቋቋም ይጥሩ የነበሩ ቡድኖች (በአውሮፓ እነ ኃይሌ ፊዳ፣ በአልጄሪያ እነ ብርሃነ መስቀል ረዳ) እንዳሉ ይታወቅ ስለነበር እነዚህ ቡድኖች የብሔሮችን መት ከማወቅ በላይ ሄደው በተለይ የኤርትራን ነነት ወይም መገንጠል እንዲደግፉ በጊዜ ተፅዕኖ ለማሳደር የኤርትራ ግንባሮች በተለይም ሻቢያ ‹‹የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው›› ማለት ጀመረ። ከሻቢያ ጋር የጦፈ የርስ በርስ ጦርነት ላይ የነበረው ጀብሃ (ELF) ለልማዱ የሻቢያን ትርክት ተቀብሎ እሱም ‹‹የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው›› አለ። በውጭ አገር ያሉት የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበራት አዲሱን ‹‹የቅኝ ግዛት ትርክት››ግሩ የማይቆም ብለው አጣጣሉት። በዚህም በኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበራትና በኤርትራ ተማሪዎች ማኅበራት ጋር ክርክር ተደረገ። መግባባት አልተደረሰም። ከዚ ተከትሎ እነዚሁ የሻቢያ ወጣቶች ‹‹ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ሆና አታውቅም›› የሚል ሌላ አፈ ታሪክ ይዘው መጡ (በነገራችን ላይ በኋላ የተቋቋመው ወያኔ እነዚህን ሁለት የሻዕቢያ ትርክቶች ተቀብሏል። ለዚህም ‹‹የኤርትራ ታሪክ ከየት ወዴት? … ወዘተ…›› ብሎ በራሱ በመለስ ዜናዊ የተጻፈውን ጽፍ ማየት ይቻላል)፡፡

ነዚህ ሁለት ትርክቶች ዓላማ ግልጽ ነው። ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ከሆነች ማንም ተራማጅ የማንንም ቅኝ ግዛት ነነት እንደሚደግፈው ሁሉ የኢትዮጵያ ተራማጆችም የኤርትራን ነፃነት ያለ ማንገራገር እንዲደግፉ ነበር። ሁለተኛውም ትርክት ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ሆና የማታውቅ ከነበረ ነነቷ ወዲያው መደገፍ አለበት ለማኘት ነው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ተራማጆች ያኔ በኤርትራ ውስጥ መረታዊ የፖለቲካ ችግሮች እንደ ነበሩ ተገንዝበዋል። ከሁሉም በላይ ሁለቱ የኤርትራ ድርጅቶች የርስ በርስ ጦርነት ላይ ነበሩ። ርስ በርሳቸው እየተዋጉ በምን ተዓምር ነው ነነታቸው የሚደገፈው? ከተራማጅ አስተሳሰብ ነፃነት የሚደገፈው ሌላ አማራጭ ጠፍቶ ነነቱ ብቸኛ አማራጭ ሲሆን ነው። ሁለተኛው ችግር ደግሞ ኤርትራ ራሷ ዘጠኝ ብሔሮች ያሉባት አገር ናት። እንግዲህ የኤርትራ ግንባሮች የኢትዮጵያ ተራማጆች ነነታቸውን እንዲደግፉ የፈለጉትን ያህል እነሱስ በኤርትራ ውስጥ ያሉት ብሔሮች የራሳቸውን መብት በራሳቸው ለመወሰን ያላቸውን መብት ያውቃሉ ወይ? ይደግፋሉ ወይ? የኤርትራ ግንባሮች በዚህ ላይ በግልጽ ያሉት ነገር ባይኖርም ከድርጊታቸው ስንነሳ ግን የራሳቸውን ብሔሮች መብት የሚያከብሩ አልነበሩም። እንደ ተገመተውም ኤርትራ ነ ከወጣች በኋላ በነዚህ ብሔሮች ላይ በተለይም ተደራጅቶ በነበረው የአፋር ንቅናቄ ላይ ዘመቱበት።

በ1967 ዓ.ም. ወያኔ ይቋቋምና ዋናው ደጋፊው ሻዕቢያ ሆነ። ወያኔ የፖለቲካ ፕግራሙ የሆነውን አሳፋሪውን ማኒፌስቶ አወጣና ሌላ አዲስ ትርክት ጀመረ። የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ ዋናው የአገሪቱ የፖለቲካ ጥያቄ ነው፣ በዚህም በአገሪቱ ውስጥ ያለው ዓይ ቅራኔ የብሔር ቅራኔው ነው አለ። የኢትዮጵያ ተማሪዎችና ኢአፓ በ1966 ዓ.ም. የተጀመረው አብዮት በማያወላዳ መንገድ የመደብ ይዘቱ ዋነኛው ገጹ እንደሆነ፣ በየካቲት አብዮት በየትም አካባቢ የብሔር መብት ጥያቄ አለመነሳቱ ለዚህ ማስረጃ ከመሆኑም በላይ በየካቲቱ አብዮት የተነሱት ጥያቄዎች በሙሉ መደባዊ እንጂ ብሔርተኛ አይደሉም አሉ። የሚያውቀው ከራሱ ጋር ብቻ ማውራት የሚመስለው ወያኔ ግን ይኼም አልበቃው ‹‹የትግራይ ሕዝብ በአገሪቱ በጣም የተጠላ ብሔር ሆነ›› አለንና አረፈው። ከዚህ አልፎም የብሔር ጥያቄን ወደ አዘቅት የወሰደ ትርክትና አንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ፖለቲካ ጀመረ፣ ‹‹አማራ ጠላት ነው›› ብሎ አወጀ። የኢትዮጵያ ተማሪዎችና ኢአፓም በጠላትነት ተፈረጁ። ‹‹የታላቋ ኢትዮጵያ›› (‹‹ዓባይ ኢትዮጵያ›› ይሉታል ወያኔዎቹ) አቀንቃኞች፣ ማናህሎኝነት የተጠናወታቸው አሉ።

ሌላው አደገኛው የወያኔ የጎጠኝነት ትርክት ደግሞ በኢትዮጵያ ያሉ ብሔሮች መጀመያ በየብራቸው ‹‹አዲሱን ሞክራሲያዊ አብዮት ካካሄዱ በኋላ ከፈለጉ ተመልሰው ሊዋሃዱ ይችላሉ›› ማለታቸው ነው። ይ ወዲያ ወዲህ የማይል በግልጽ ቋንቋ ‹‹ኢትዮጵያ መጀመያ መገነጣጠል›› አለባት ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ነው ብሔሮች ከፈቀዱ ተመልሰው እንደገና ሊዋዱ ይችላሉ የሚሉን። ከዚያ በኋላማ ኢትዮጵያን ‹‹ቅኝ ገዥ›› ብሎ የሰየመው ጎጠኛ ሁሉ ዓላማው የሆነውን መገንጠልና ልጣን ላይ መፈናጠጥን ከረጋገጠ በኋላ የራሱን መንግሥት አቋቁሞ መገንጠልን እንጂ ተመልሶ መዋድንም መቼ ይሞክረውና። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ናቸው በደርግ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስህተት በመዳከሙ ተጠቅመው ሥልጣን ከያዙ በኋላ ደግሞ ሌላ አዲስ ትርክት (‹‹ብሔር ፌዴራሊዝም››፣ ብሔሮችን በክልል ማካለል፣ ‹‹እስከ መገንጠል ድረስ›› የሚለውን መንግቱ ውስጥ ማስገባት፣ ወዘተ…) ይዘውልን መጡ።

እንግዲህ የ ሻዕቢያ የማይዋጥ ትርክት ከፖለቲካ አንር አንድ ርምጃ ወደ ኋላ መወዱ ሳያንስ ወያኔ ደግሞ ከዘረኝነት የማይተናነስ ፍረተ ፖለቲካ ይዞ መጣ። በኢትዮጵያ ላይና በኢትዮጵያዊነት ላይም ዘመቻ ከፈተ። ሥልጣን ላይ ወጥቶም ቢሆን ይህንን አሳፋሪ እምነቱን ባለመልቀቁ አገራችንን እንኳ ‹‹ኢትዮጵያ›› ብሎ ላለመጥራት ዳዳው። ይህ የሚያሳየው ከሁሉ አስቀድሞ እነዚህ አሳፋሪ ትርክቶች ከኢትዮጵያ ተማሪዎችና አፓ አቋም ጋር ተራሪ እንደነበሩ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሻዕቢያ የተጀመረው የተበላሸ የብሔር ትርክት ወደ ሌላ የተበላሸ ትርክት እንዳዘቀጠ ነው። እንዲህ ያለው ብልሹ ትርክት ነው በየጊዜው አዳዲስ የታሪክ ልብ ወለዶችን እየወለደ ዛሬ የደረስንበት የደረሰው።

በዚያው በ1967 ዓ.ም. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ተቋቋመና የፖለቲካ ፕሮግራሙም ተበተነ። ኦነግ ከዚያ ቀደም ሲል ከነበሩት የሜጫና ቱለማ እንዲሁም ከባሌው ዝባዊ አመ ጋር ምን ያህል የተያያዘ እንደነበር የሚታወቅ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ኦነግም ልክ ንደ ሻዕቢያ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው አለ። ከነሱ ቀደም ሲል አብርሃም ገብረ እግዚአብሔር (አዲስ ይወት) የጀመረውን አገላለጽ ገልብጠው ‹‹ሱ ነው ያገኘነው›› እንኳ ሳይሉ የራሳቸው ግኝት አስመስለው ‹‹የኦሮሞ ጥያቄ ወታደራዊ ፊውዳል ቅኝ ግዛት (Military Feudal Colonialism) ነው›› አሉ። ይህን ቲሲስ የማይቀበሉትን የኦሮሞ ተወላጆች እንዲሁም በተራማጁ የተማሪና ኢአፓ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚካፈሉትን የኦሮሞ ተወላጆች ‹‹አዲሶቹ ጎበናዎች›› (Neo Gobenaists) አሏቸው።

እዚህ ላይ መነሳት ካለበት ጉዳይ አንደኛው እነዚህ ‹‹የብሔር›› ንቅናቄዎች የኢትዮጵያ ተማሪዎች የብሔሮችን መብት ማክበራቸውን በደስታ እንደ መቀበል በተገላቢሽኑ መጀመያ በተማሪው እንቅስቃሴ ላይ በኋላ ደግሞ በኢአፓ ላይ  ዘመቻ መክፈታቸው ነው። በስሱ የ‹‹ብሔርተኝነት›› ባይ የነበረው ትርክት ተቀያይሮ በጎጠኝነት ር መስደድ የጀመረው ያኔ ነበር ማለት እንችላለን። ጎጠኞች ብረ ሔርተኝነት ወደፊት ለሚያልሙት የፖለቲካ ሥልጣን መጨበጥ ዋነኛው አደጋ ሆኖ ታያቸው። በብሔር እንቅስቃሴ ስም በኢትዮጵያ የተነሱት ኃይሎች ዋናው ህልማቸው ሥልጣን መጨበጥ (ከዚያም ብት ማካበት፣ ወዘተ…) ስለነበረ ለዚህ ዓላማቸው መሳካት ዋነኛው እንቅፋት ደግሞ ዓላማው ድህነትን ማጥፋት፣ ሞክራሲን መገንባት፣ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቀረት ወዘተ …  የሆነው ብረ ራዊው የተራማጁ እንቅስቃሴ ነበር። ለዚህ ነው እነዚህ እንቅስቃሴዎች በርግጥም የብሔር እንቅስቃሴዎች ነበሩ ወይ? እንድንል የሚያስገድደን።

በሌሎች ክፍለ ዓለማት በተለይም ብሔርተኝነት እንደ ፖለቲካ ክስተት የተጀመረበትን የአውሮፓ የብሔር ተክሮ ብንወስድ እንዲህ ያለ ጠላትነት በተራማጆች ላይ አልነበረም ማለት ይቻላል። እንዲያውም በአብላጫው የብሔር እንቅስቃሴዎቹ ለሞክራሲ የተደረገው ትግል አካል ነበሩ።  ኛዎቹ የተቆራኙት ግን ብሔርተኝነትን ሳይሆን ወደ ዘረኝነት የሚጠጋ ጎጠኝነትና አንድን ብሔር ለይቶ መጥላት ነው። ለዚህ ነው የብሔር እንቅስቃሴች ናቸው ማለት አይገባም የምንለው (በእንግሊዝኛው በብሔርተኝነትና በኤትኒሲቲ መል ትልቅ ልዩነት አለ። በኛ አገር በተለምዶ ‹‹የብሔር እንቅስቃሴዎች›› የሚባሉት በመረቱ የኤትኒሲቲ ቡድኖች ናቸው ማለት ይቻላል)፡፡ ምክንያቱም ብሔርተኝነት በተለይም በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ አዎንታዊ ሚና ነበረው፡፡ ለዚህም ነው ተራማጁ ክፍል ስለብሔር እንቅስቃሴዎች አዎንታዊ የነበረው። ከዚያም ተነስቶ ብሔርተኝነት የተራማጅ ይዘትና ሪካዊ ተገቢነት አለው ይል የነበረው። በኛ አገር የታየው ግን ይለያል። የብሔር ንቅናቄዎቹ የተመረቱት አንድን ብሔር አማራውን ጠላት አርገው በመነሳት ነው። እስቲ እነ ጃዋር ‹‹በሜንጫ አንገቱን›› ሊቀሉት የዛቱበት የጎጃም ገበሬ የኦሮሞ ገበሬ የሚደርስበት ግፍ በሱም ላይ እየወረደበት እያለ እንዴት ነው የኦሮሞ ጠላት የሚሆነው? የት ተዋውቀው? የት ተገናኝተው? ለመሆኑ የወያኔና የኦሮሞ ንፈኞች እንደዚህ ዓይነት መደምደሚያ ላይ ሲደርሱ ጥናት አርገው ነውን? በአማራ ክልል ተዘዋውረው ዝቡን አናግረው ነውን? እንደዚህ እንዳልሆነ ግን የታወቀ ነው።

ለመሆኑ እንዲህ ያለው አመለካከት ክቡር የሆነውን የኦሮሞ ሕዝብ፣ በሩነትና የዋህነት የታወቀውን እሴቶቹን ያንባርቃልን? በትግራይስ ቢሆን የወያኔ መሪዎችን የሚገልጸው አማራነት፣ ፍም ጨካኝነትና ለከት የሌለው አላስተዋይነት የትግራይን ሕዝብ እሴቶች ያንባርቃልን? የትግራይ ሕዝብ ትግራይ የኢትዮጵያ ታሪክ ምብርት መሆኗን የሚያውቅ፣ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም። ስለሆነም የወያኔ የታሪክም ሆነ የፖለቲካ ትርክት ምንም አይጥመውም። የትግራይ ሕዝብ የሚያምንበትን በግላጭ እንዳይገልጽ ወያኔ ነነቱን ነፍጎታል። ጀግንነት የሳብ ጥራትና በሳብ ጥራት ላይ ያለው እምነት በሆነበት በአሁኑ ዘመን ወያኔ እጅግ አድርጎ የሚፈራው ጉዳይ ቢኖር ከሱ የተለየ ሳብ መገለጹን ነው። የወያኔም ሆነ የሌሎች ጎጠኞች ‹‹ጀግንነት›› ጠመንጃ፣ ገጀራና ሜንጫ ላይ ነው፡፡ ሰማዊውን ሕዝብ መረሸን ወይም አንገቱን መቁረጥ ላይ ነው። ይህ በአንድ በኩል ምን ያህል ኋላቀር እንደሆኑ ሲያሳይ በሌላ በኩል ደግሞ ካኔያቸው የሰውን አንገት እንደ ዘበት ከሚቀሉት አይሲስ ከተባሉት ሽብርተኞች ጋር ተመሳሳይ ባርባሪዝም መሆኑን ነው።

እዚህ ላይ መገለጽ ካለበት ነገር አንደኛው ንፈኞች በሴቶች ላይ ያላቸው ንቀት፣ በሴቶች ላይ የሚያደርሱት በደል እንዲሁም ሴቶች የወንዶች እኩል መሆናቸውን በወሬ እንጂ በተግባር የማይቀበሉ ለመሆናቸው ነው። ወያኔ በተለይ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ በሴቶች ላይ ያለውን ንቀትና ሴቶች ከወንዶች እኩል አይደሉም (ከፕሮጋንዳው ሳይሆን ከተጨባጭ ድርጊቱ ተነስተን) ብሎ እንሚያምን ነው። ታስሮ እንደተለቀቀ ወይፈን መሪዎቹም ጭምር ሴት እንደ ሸሚዥ መቀያየሩን ተያያዙት። ሌሎቹም ንፈኞች ከዚህ የተለየ አመለካከት በሴቶች ላይ የላቸውም። ኦነግ ኔ የተባለው ቡድን ሴት (አማራ) ተማሪዎችን ነጥ አፍኖ ወስዶ ማሰር ምን የሚሉት ነው? አመለካከታቸው እንደ ወያኔ ካልሆነ በተቀር?

መረራና የ‹‹ነፍጠኛ›› አንደርቢ

ከሰሞኑ የሆነው ደግሞ በሚያስገርም ሁኔታ የመረራ ጉዲና መቀልበስ ነው። መረራ በመኢሶንነታቸው ምንም እንኳን የኦሮሞ ኮንግሬስ ብለው ቢነሱምዕምሯቸው ውስጥ ከቀረው ተራማጅ አስተሳሰብ የተነሳ ከጽንፈኞቹ ትርክት ርቀው ቆይተው ነበር። በቀደም ግን እሳቸውም በጽንፈኞች ትርክት እንዳመኑ አወጁልን። ‹‹የነፍጠኛውን ት/አመለካከት›› ሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰፍን ዋና እንቅፋት አርገው አቀረቡና አረፉት። ከአፋቸው ያላወለቁት ማስክ በመጥፎ እየተረጎመባቸው ይመስላል እንዲህ ያለ ጊዜው ካለፈበት ትርክት ይገባሉ ብሎ የገመተም አልነበረም።

ለመሆኑ ነፍጠኛ ምንድነው? የሆነ ሰይጣን ወይም ጭራቅ ካልሆነ የነፍጠኛው ት ነፍስ ዘርቶ ከመቃብሩ ተነስቶ ይህችን አገር እያመሰ ነው ካልተባለ በተቀር ነፍጠኝነት ካበቃለት ይኼው 45 ዓመቱ። የደርግ የመሬት አዋጅ እኮ መሬት ለገበሬው ማከፋፈል ብቻ ሳይሆን የባለመሬቱን መደብ ጠራርጎታል። ነፍጠኛ እኮ ባለመሬቱ ነበር። ባለመሬቱ ሲያበቃለት ነፍጠኝነትም አብቅቶለታል። እንዲያው በቅ እንነጋገር ከተባለ ከተቀበረ ከ45 ዓመት በኋላ በየት ቦታ ነው ባለመሬት መልሶ መሬቱን ይዞ እንደገና ገባሩን እያስገበረ ያለው? ከ45 ዓመት በኋላ ያለቀለት ነፍጠኛ በምን ተምር ነው እንደገና የዚችን አገር የሞክራሲ ደት እያጨናገፈ ያለው? እነ መረራ አሁን ምኑን/ማንን ነው ነፍጠኛ የሚሉን? ነፍጠኛ እስከዚህ የሚወራለት ከሆነ በሆነ የማጉያ መነጽር ነፍጠኛ መፈለግ ሊኖርብን ነው። ‹‹ነፍጠኛ! ነፍጠኛ!›› የሚል ድቤ እየደበደቡ አንደርቢ ማስነሳት ካልሆነ። ‹‹የለም! የለም! የነፍጠኛ አመለካከቱ ማለታችን ነው ኮ!›› ቢሉም የትኛውን አመለካከት? ችግሩ ከላይ ነው ማለታቸው ስለሆነ የትኛው የመንግሥት ፖሊሲ ነው ነፍጠኛ የተባለው? በፖሊሲ ደረጃስ ‹‹ነፍጠኛ›› ብሎ ነገር ምንድነው? ዛር ወይም አንደርቢ ነው ካላሉን።

መረራና መሰሎቹ ምንድነው የሚፈልጉት? በዘመነ ግሎባይዜሽን ዓለም አንድ ወደ መሆን እየተጓዘች ባለችበት ሁኔታ፣ በዓለም ሰፍኖ ያለው ዋና ዋና ችግር የያንዳንዱ አገርም ችግር በሆነበት ስለዚህም አገሮች አንድ ላይ ሆነው ችግሩን ለመታት መሞከር አለባቸው በሚባልበት ጊዜ እኛ በድህነት ወስጥ የምንማቅቅ ዝቦች ድህነትን እንዴት እንደምናጠፋ፣ የሴቶቻችንን በደል ንዴት እንደምናስቀር ማሰብ እንጂ ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን ተመልሶ ከጠፋ 45 ዓመት የሆነን ጉዳይ ልክ አሁንም እንዳለ አስመስለው አንደርቢ ማስነሳት ምን የሚሉት ‹‹ፖለቲካ›› ነው? እንዲህ ያለ ፖለቲካ እኮ የለም። ይህንንም የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰሩ ጠንቅቀው ማወቅ ነበረባቸው እንላለን።

ይኼ ሁሉ ድቤ መደብደብ በሌሎቹ የአፍሪካ አገሮች እንደሚደረገው ለሥልጣን መቋመጥ ያመጣው አባዜ ነው። ‹‹እነ እገሌ ሚኒስትር ከሆኑ እኔ ከዚያ በላይ የማልሆንበት ምክንያት የለም›› የሚል የግብዝነት አባዜም አለበት። እንደዚህ ያሉ ራሳቸውን ‹‹ፖለቲከኛ›› የሚሉ ሰዎች ዋነኛው ችግራቸው አንድም ቀኝነት ማጣት ሁለትም ስለራሳቸው ያላቸው ግምት ከፍተኛ በመሆኑ ከሥልጣን ጥመኝነት ጋር ተደምሮ እንታገልለታለን የሚሉትን ሕዝብ መረታዊ የለት ተለት ብሎም የሩቅ ችግሮቹን ያዩለት አይመስሉም። ስለዚህም ለምሳሌ የኦሮሞ ገበሬና አርብቶ አደር ከድህነት የሚላቀቀው በምን ስትራቴጂ እንደሆነ፣ ምንም የነፃነት ፍንጣ ያጣው የሴቶች አበሳ በምን ዓይነት ስትራቴጂ እንደሚያበቃላቸው፣ በአጠቃላይም በማክሮ ኮኖሚ ያሉት ችግሮች በማይክሮ ደረጃ ካሉት ችግሮች ጋር በምን ዓይነት ሌት ይታያሉ፣ የሚደጋገፉትስ እንዴት ነው? በአጭሩ ልማት ሲባል እንዴት ነው የሚመጣው፣ የኦሮሞስ ሰፊ ሕዝብ በጠቅላላው ከድህነት ወጥቶ ወደ ልማት የሚገባው በምን ዓይነት ስትራቴጂ እንደሆነ እነ መረራ ምንም ዓይነት የተቀመረና የተሰለቀ ሳብ ያላቸው አይመስሉም። ስለነዚህ መረታዊ የመብትና የሞክራሲ ጉዳዮች ሲያወሩ ሰምተን ስለማናውቅ። ስለነዚህ ቁልፍ ጥያቄዎች ማውራት የተከለከሉ ይመስል ምንም ሲያነሱ አይሰሙም። ለምን? ጥላቻን ብቻ መንዛት የኦሮሞውን ገበሬ ከድህነት ያወጣዋል? ለመሆኑ የምኒውልት ፈረሰና የኦሮሞ ሕዝብ ድህነቱ ይቀረፍለታል?

እነ መረራ በሻሸመኔና በሌሎችም አካባቢዎች ቄሮዎች በክርስትና ተከታዮችና በአማሮች ላይ የፈጸሙትን የጅምላ ግድያ (ጄኖሳይድ) ምነው ሳያወግዙ ቀሩ? ይኼ እኮ መረታዊ ጉዳይ ነው። አመላካችም ነው። ይዘግዩ እንጂ የጥታ ኃይሎች ርምጃ ባይወስዱ ኖሮ እጅግ ብዙ ክርስቲያኖችና አማሮች ይታረዱ ነበር። አቶ መረራ ይ እኮ ፖለቲካ አይደለም። ናዚዎች በአይሁዶች ላይ የሩዋንዳ ሁቱዎችም በቱትሲና ሊበራል ሁዎች ላይ የፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋ ዓይነት ነው። ጎጠኞች እንዲህ ያለውን ጄኖሳይድ ሲያወግዙ አልተሰሙም። ካላወገዙት ደግፈውታል ማለት ነው። ሌላ ትርጉም የለውም። ወደፊትም ቢሆን ማንም የኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ከየትኛውም አቅጣጫ ይምጣ በማንም ይደረግ በማንም እንዲህ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ ወዲያው ማውገዝ አለባቸው።

በመጨረሻም ለማንሳት የምንፈልገው የምሁሩን ሚና በሚመለከት ነው። በስድሳዎቹ (ንደ ዛሬው በዘር ላይ የተመረተ ትርክት ናላችንን ሳያዞረው) የምሁሩ ሚና በፖለቲካ ውስጥ የጎላ ነበረ። በዚህ ጊዜ የምሁሩ ክፍል ይባል የነበረው ከብዙዎቹ ብሔሮች የተጣጣ ስለነበር ዘረኝነት ቦታ አልነበረውም። የመኢሶኑ መሪ ኃይሌ ፊዳ በትውልዱ ኦሮሞ ቢሆንም ኢትዮጵያዊ እንደሆነና ለኢትዮጵያ እንዳሰበ አልፏል። መኢሶንም ብዙ ብሔር ያቀፈ እንጂ የአንድ ብሔር ድርጅት አልነበረም። ኢአፓም ከመሪዎቹ አንዱ አበራ ዋቅጅራ ኦሮሞ ቢሆንም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለኢትዮጵያ የታገለ ነው። ሌሎቹም ከትግራይ (ተስፋዬ ደበሳይ፣ ዘሩ ክህሸንና ብርሃነ መስቀል)፣ ከአማራ (ክፍሉ ታደሰ፣ ክፍሉ ተፈራ፣ ኢያሱ ለማየሁ፣ ዮንስ ብርሃኔ፣ ሳሙኤል ዓለማየሁ)፣ ጉራጌ (ፍቅሬ ዘርጋው) የተወጣጡ ነበሩ። ይህ በፖለቲካ ድርጅቶች ደረጃ ይንባርቅ እንጂ በብዙን ድርጅቶች፣ ማኅበራት፣ (ራተኛ ማበር፣ መምህራን ማበር፣ የሴቶች ማበር፣ ወዘተ…) ሁሉ እንደዚሁ ብሔር አቀፍ አደረጃጀት ነበር በአገሪቱ የሰፈነው። ከኤርትራ በተቀር በኢትዮጵያ ውስጥ በብሔር መደራጀት የተጀመረው ከ1967 ዓ.ም. በኋላ ነው። ከ1967 ዓ.ም. እስከ 1970 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ስጥ ከደርግ ጋር በነበረው ፍልሚያ በርካታ የብረ ብሔር ድርጅቶች አባላት ወደቁና በብሔር የተደራጁት ቀሩ።

በርካታ ምሁራን በደርግ ሲገደሉ ገሚሱም ስደት ሄደና የተቃውሞው የፖለቲካ መድረክ በብሔር ድርጅቶች ተያዘ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ምሁራን ተገቢ ቦታቸውን ሳይዙ ቀሩ። በዚህ ጊዜ ነው የተለያዩ ብሔር ድርጅቶች የታሪክ ትርክቶች እየተወለዱ የመጡት። ለዚህ ዓይነቱ በሬ ወለደ ትርክት ቦታ ማግኘት ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያ ምሁራን ማፈግፈግ (Retreat of Intellectuals) ነው። ምሁራን እስከ ዛሬ ካፈገፈጉበት ተመልሰው ተገቢ ቦታቸውን አልያዙም። የአገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ አደገኛ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንደኛው ይው የምሁራን ማፈግፈግ ነው። ስለአገሪቱ የመከፋፈል አደጋ ጋቱ ያለው ሁሉ፣ የአገሪቱም የፖለቲካ አካሄድ ወደ ሞክራሲ እንዲያመራ የሚፈልግ ሁሉ ምሁራን በአገሪቱ በሚዋቸው ውይይቶች ዋናውን ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ አለበት። የተለያዩ የበሬ ወለድ ትርክቶች ሊፈርሱ የሚችሉትና የወደፊቱም ጥርጊያ መንገድ ሊታይ የሚችለው በምሁራን ትንተና ነውና። ‹‹ምሁራን በውይይት መሳተፍ አለባቸው›› ማለት ብቻውን ምንም ማለት አይሆንም። የሚሳተፉበትን መድረክ ማዘጋጀት ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ አያሌ የሚዲያ ተቋማትን በቁጥጥሩ ር ያደረገው የዓይ መንግሥት ምሁራንን የማሳተፍ ላፊነት አለበት። የፓርቲ ካድሬ ይላፊነት ሊወጣ አይችልም።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

 

spot_img
Previous article
Next article
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...