Sunday, June 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ በውክልና ሒሳብ ማንቀሳቀስ የሚከለክለውን መመርያ አሻሻለ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለብር ኖቶች ለውጥ ባወጣው መመርያ በውክልና ሒሳብ ማንቀሳቀስ የማይቻል መሆኑን የሚደነግገውን በማሻሻል፣ ከመስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም. በፊት ሕጋዊ ውክልና ያላቸው ሰዎች ሒሳብ ማንቀሳቀስ (ገቢ ማድረግ) እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

 ብሔራዊ ባንክ ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው ማሻሻያ፣ ከዚህ ቀደም ከአምስት ሺሕ ብር በላይ በውክልና ማንቀሳቀስ አይቻልም የሚለውን ሽሮታል፡፡  በዚህ መሠረት ከመስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም. በፊት በተገኘ ሕጋዊ ውክልና ሒሳብ ማንቀሳቀስ ይቻላል፡፡  

ብሔራዊ ባንክ የብር ለውጡ ይፋ ከተደረገ በኋላ በየዕለቱ የሚያጋጥሙ ክስተቶችን በተመለከተ፣ ከሁሉም የባንክ ፕሬዚዳንቶች ጋር እየተመካከረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ችግሮች ሲያጋጥሙም በጋራ መፍትሔ ለመፈለግ በትብብር እየተሠራ መሆኑን፣ ይህም መመርያ የተሻሻለው ከባንኮች በቀረበ ሐሳብ መሠረት እንደሆነ ታውቋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ በየሦስት ቀናት ከባንኮች ፕሬዚዳንቶች ጋር በሚያደርገው የጋራ ምክክር በገንዘብ ለውጥ ሒደቱ እንደ ችግር የታዩ ጉዳዮች ላይ ከመነጋገር በተጨማሪ፣ ባንኮች የፀጥታ ኃይሎችን ዕርዳታ ሲፈልጉ ብቻ የፀጥታ ኃይሎች እንዲሰማሩ ስምምነት ላይ የተደረሰበትም ጉዳይ ተጠቃሽ ነው፡፡

በዚህ መሠረት ከ1.5 ሚሊዮን ብር በታች ሕጋዊ ገንዘብ ሳይረጋገጥ ተይዞ መውረስ እንደማይቻል ውሳኔ ላይ መድረሱን መረዳት ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች