Monday, September 25, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አዲስ ሥራ አስፈጻሚ ሰየመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር ቦርድ፣ በኢንሹራንስ ዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸውን አቶ ፍቅሩ ፀጋዬን በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሰየመ፡፡

አቶ ፍቅሩ ብቸኛውን የጠለፋ መድን ሰጪ ኩባንያ በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ በቦርዱ የተሰየሙት ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው፡፡ አቶ ፍቅሩ የጠለፋ ሰጪውን ኩባንያ የኃላፊነት ድርሻ የተረከቡት፣ ባለፈው ዓመት ከቦታው የተነሱትን አቶ ወንድወሰን ኢተፋን በመተካት በተጠባባቂነት ሲሠሩ የቆዩትን ወ/ሮ መሠረት ጥላሁን ተክተው እንዲሠሩ ነበር፡፡

የቀድሞውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድወሰንን ተክተው በተጠባባቂነት  እንዲሠሩ በጠለፋ መድን ድርጅቱ ቦርድ ተሾመው የነበሩት ወ/ሮ መሠረት፣ ከጥቂት ወራት ቆይታ በኋላ በአቶ ፍቅሩ እንዲተኩ የተደረጉበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ በወ/ሮ መሠረት ምትክ አቶ ፍቅሩ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሠሩ መወሰኑ ታውቋል፡፡ የቦርዱ ውሳኔም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተልኮ ሹመታቸውን እንዲያፀድቀው ይደረጋል ተብሏል፡፡

አቶ ፍቅሩ ለኢትዮጵያን ጠለፋ መድን ኩባንያ ከመታጨታቸው በፊት በዚሁ ኩባንያ ውስጥ የሥራ አመራር አባል ነበሩ፡፡ የስትራቴጂና የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮም የቦርድ ጸሐፊ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር፡፡

በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ከ16 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው አቶ ፍቅሩ፣ የኢትዮጵያ የጠለፋ መድን ኩባንያን ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት የማይክሮ ኢንሹራንስ ዘርፍ ዳይሬክተር፣ በኦፕሬሽንስ ዘርፍ የውልና ካሳ ሱፐርቫይዘርና የኦፕሬሽንስ ዘርፍ ኦፊሰር ሆነው ሠርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መድን ሥራ ባለሙያዎች ማኅበር የቦርድ አባልም ናቸው፡፡ አቶ ፍቅሩ የማስተርስ ዲግሪ በሰው ሀብት አስተዳደርና ተቋም ግንባታ ከማግኘታቸውም በተጨማሪ ሌላ የማስተርስ ዲግሪ በጋዜጠኝነትና ሕዝብ ግንኙነት መስክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ የመጀመርያ ዲግሪ ቢኤስሲ ባችለር ኦፍ አርትስ ዲግሪ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ዲፕሎማ አላቸው፡፡ አሜሪካ ከሚገኘው ላይፍ ኦፊስ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት፣ በጠለፋ መድን አገልግሎት በጠቅላላ መድን ዘርፍ ዕውቅና አግኝተዋል፡፡ በዚሁ ዘርፍ በአሁኑ ወቅት የአመራር ሚና ላይ ያተኮረ የፒኤችዲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ አቶ ፍቅሩ በአፍሪካ ደረጃ በእስልምና ኢንሹራንስ (ታካፉል) ኢንሹራንስና ሪኢንሹራንስ ዘርፍ እ.ኤ.አ. የ2020 ተሸላሚ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ የጠለፋ መድን ኩባንያ በኢትዮጵያ የጠለፋ መድን የሚሰጥ ብቸኛው ተቋም ሲሆን፣ ከአራት ዓመታት በፊት በተለያዩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና በጥቂት ባንኮች ባለቤትነት የተቋቋመ ነው፡፡ የኩባንያው የተቋቋመበት ዋነኛ ዓላማ በጠለፋ መድን ከኢትዮጵያ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረትና የጠለፋ መድን ሥራ በአገር ውስጥ እንዲሠራ ታሳቢ ተደርጎ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች