አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በ2013 ዓ.ም. እንዲካሄድ የተወሰነው አገር አቀፍ ምርጫ በመላ አገሪቱ እንደሚካሄድ ገለጹ፡፡
በአሁኑ ወቅት በመንግሥትና በሕዝቦች መካከል ያለው ማኅበራዊ ውል ሕገ መንግሥቱ እንደሆነ የጠቀሱት አፈ ጉባዔው፣ በዚህም ምክንያት ሁሉም አካል ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥቱ ያቋቋማቸው ተቋማትን ማክበርና በሕግ መሠረት የሚወሰኑትን መቀበል ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ ፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን የጠቀሱት አፈ ጉባዔው ምክር ቤቱ በትግራይ የተካሄደው ምርጫ ተቀባይነት እንደሌለው መግለጹን በመጥቀስ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በትግራይም እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡