Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊለጤና ባለሙያዎች የገቢ ግብር ወጪ እንዲሸፈን ተወሰነ

  ለጤና ባለሙያዎች የገቢ ግብር ወጪ እንዲሸፈን ተወሰነ

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዓርብ መስከረም 15 ቀን 2013 . ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ፣ በከተማዋ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የገቢ ግብር ወጪ መሸፈንን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡  

  የከንቲባ ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሪታሪያት እንዳስታወቀው፣ ዓለም አቀፍጋት የሆነው የኮሮና ወረርሽኝ፣ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ከመጋቢት 2012 . ጀምሮ፣ በአዲስ አበባ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት፣ በማስተባበርና በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ጤና ተቋማት ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ወረርሽኙ በኢትዮጵያ ሥጋት መሆኑ እስከሚያበቃ ድረስ የከተማ አስተዳደሩ ወጪያቸውን ለመሸፈን ውሳኔ አሳልፏል።

  የከተሞች ዕድገትና ልማት ከአካባቢያቸው ጋር ሲተሳሰር፣ የሕዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት፣ የአብሮነት አስተሳሰብና ሰላማዊ ግንኙነት እንደሚያዳብር፣ አዲስ አበባም በዙሪያዋ ካሉ አካባቢዎች ለዕድገትናልማቷ የሚሆኑ ብዙ ግብዓቶችን እያገኘች፣ የውኃ፣ የመሬት፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች በማቅረብ፣ እንዲሁም በርካታ የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት፣ የግል ሠራተኞችና የከተማዋ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች መኖሪያ ሆነው ሳሉ፣ ለማኅበራዊ ችግርና የመሠረተ ልማት እጥረት ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡

  በመሆኑም ካቢኔው በከተማዋ የተጀመሩትን የትምህርት ተሞክሮና አገልግሎቶች በአካታች ልማት መርህ መሠረት በፊንፊኔ ልዩ ዞን በሚገኙ 346 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ 152 ሺሕ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ ጫማና የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል የ669,210,780 ብር በጀት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ በልዩ ሁኔታ ውሳኔ ማሳለፉንም ሴክሪታሪያቱ አስታውቋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img