Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓቃቤ ሕግና አቶ ልደቱ አያሌው በዋስትና መብት ላይ ክርክር አደረጉ

ዓቃቤ ሕግና አቶ ልደቱ አያሌው በዋስትና መብት ላይ ክርክር አደረጉ

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ዓቃቤ ሕግ፣ አቶ ልደቱ አያሌው የተመሠረተባቸው የፀና ፈቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ 20 ዓመታት ፅኑ እስራት ስለሚያስቀጣቸው ዋስትና ሊፈቀድላቸው እንደማይገባ ባቀረበው መከራከሪያ ሐሳብ ላይ፣ አቶ ልደቱም ዋስትና ስለማይከለክል ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ሰፋ ያለ ክርክር አደረጉ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ ከተመለከተ በኋላ፣ በዋስትና መብት ላይ ዓቃቤ ሕግና አቶ ልደቱን አከራክሮ የዓቃቤ ሕግን መቃወሚያ በማለፍ አቶ ልደቱ በ100,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር የተሰኘው የምሥራቅ ሸዋ ዞን ዓቃቤ ሕግ መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በተጻፈ የይግባኝ አቤቱታ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት አቅርቦ ዋስትናቸውን አሳግዷል፡፡ ይግባኙን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 185፣187 እና 189 ድንጋጌ መሠረት ያቀረበ ሲሆን፣ አቶ ልደቱ እስከ 20 ዓመታት ድረስ የሚያስቀጣቸው ክስ መከሰሳቸውን አስታውሷል፡፡ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 60025 የሰጠው ብይን፣ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 195(2ሀ) ድንጋጌ መሠረት እንዲሻርለትም ጠይቋል፡፡ በአንቀጽ 185 (5) ድንጋጌ መሠረትም የዋስትናው መብት እንዲታገድ ጠይቆ ታግዶለታል፡፡

ተዘዋዋሪ ችሎቱ ለመስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ሁለቱን ተከራካሪ ወገኖች ያከራከረ ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ በመቃወሚያ መከራከሪያው አቶ ልደቱ ለሕክምና ወደ አሜሪካ እሄዳለሁ ብለው በችሎት መናገራቸውን ጠቁሞ በዋስ ቢወጡም ከሄዱ እንደማይመለሱ፣ ይኼንን ራሳቸው አረጋግጠው እያለ ዋስትና ሊጠበቅላቸው እንደማይገባ ተናግሯል፡፡

በሌላ በኩል አቶ ልደቱ የፖለቲካ ሰው በመሆናቸውና ብዙ ደጋፊ ስላላቸው በዋስ ቢለቀቁ በደጋፊዎቻቸው አማካይነት በምስክሮቹ ላይ ግፊትና ተፅዕኖ ሊፈጥሩ እንደሚችሉም አስረድቷል፡፡ ለማስረጃ ያህልም መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ሦስት ምስክሮች የቀረቡ ቢሆንም፣ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ግን በደረሰበት ግፊት አንድ ምስክር አለመቅረቡን ተናግሯል፡፡ ይኼ ሁሉ ማስረጃ በግልጽ በታየበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤት ሁሉንም በማለፍ ተከሳሹ በእስር ቢቆዩ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ ሊጋለጡ ይችላሉ በማለት በአብላጫ ድምፅ ዋስትና መፍቀዱ፣ የሕግን አካሄድ ያልጠበቀና መዝገቡ ፍትሐዊ ውሳኔ እንዳያገኝ ያደረገ መሆኑን በማስረዳት ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡ በሌላ በኩልም ሕገወጥ መሣሪያ ይዞ በመገኘቱም ዋስትና ሊፈቅድለት እንደማይገባ በመግለጽ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

አቶ ልደቱ በሰጡት ምላሽ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ፍርድ ቤት ከአሥር ጊዜ በላይ ቀርበዋል፡፡ ከ70 ቀናት በላይ ታስረዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግን የታዘቡት ነገር ቢኖር ዓላማው እሳቸውን በወንጀል ማስቀጣት ሳይሆን፣ በእስር በማቆየት በጤናቸው ላይ እክል ደርሶ ሕይወታቸውን እንዳያጡ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሕክምናቸው በውጭ አገር መሆኑን ያሳወቁት ያንን ታሳቢ ያደረገ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ሕክምናቸውን አጠናቀው ሲመለሱ የክስ ሒደታቸውን እንዲከታተሉ እንጂ፣ ባይሆንና ዓቃቤ ሕግ እንዳለው ቢያስቡ ኖሮ አለመናገር ይችሉ እንደነበር ለችሎቱ ማስረዳታቸውን የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ምስክሮቹን ማስፈራራት የሚባለው ከእሳቸው ጋር የማይሄድና የእሳቸውን ተጨባጭ ሁኔታ አለመረዳት መሆኑን ጠቁመው፣ ምስክሮች የተባሉት ቤታቸው ሲፈተሽ ታዛቢ የነበሩ ስለሆኑ፣ እነሱ እሳቸውን ይጠቅሟቸዋል እንጂ ስለማይጎዷቸው ያስፈራራሉ መባሉ ተቀባይነት የሌለው መከራከሪያ ሐሳብ መሆኑን አቶ ልደቱ መናገራቸውንም አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡

መሣሪያን በሚመለከትም ያስታጠቃቸው መንግሥት መሆኑን ገልጸው፣ ሕገወጥ ነው ከተባለ ያስታጠቃቸው የመንግሥት አካል ከሚጠየቅ በስተቀር በእሳቸው ላይ የሚቀርብ መከራከሪያ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡ ብዙ ደጋፊ ስላላቸው በምስክሮች ላይ ግፊት ለመፍጠር ያስተባብራል ስለተባሉትም፣ ‹‹ይኼንን የሚለው የፓርቲዬን የትግል ሒደት የማያውቅ ነው፤›› ብለዋል፡፡ አምስት ጊዜ ተከሰው አምስቱንም በነፃ መውጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡

እየሆነ ያለው ነገር የመደራጀት፣ የመሰባሰብና ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብቶቻቸውን መጣስ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ዋስትናቸውን በመከልከል እስር ቤት እንዲቆዩና በሕይወት እንዳይወጡ ለማድረግ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ይኼንን ተመልክቶ የዋስትና መብታቸውን በማክበር፣ ሕክምናቸውን እንዲከታተሉ እንዲያደርግላቸው መጠየቃቸውንም አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ተዘዋዋሪ ችሎት በክርክሩ ላይ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...