Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ዝግጁነታቸውን የሚያረጋግጠው ኮሚቴ ውሳኔ ሲያሳልፍ ብቻ መሆኑ ተገለጸ

ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ዝግጁነታቸውን የሚያረጋግጠው ኮሚቴ ውሳኔ ሲያሳልፍ ብቻ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ለጊዜው ታግደዋል

ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ ለመክፈት ባለፈው ሳምንት ውሳኔ ያሳለፈው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጣው ኮሚቴ ዝግጁነታቸውን ሲያረጋግጥ ብቻ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ለትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ይሁንታ የሚሰጠው ኮሚቴ በአብላጫው ወላጆች የሚሳተፉበት ሆኖ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከአስተዳደር ዘርፍና ከወላጆች የተውጣጣ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ትምህርትን ለማስጀመር ከቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አንዱ ይህንን ኮሚቴ ማዋቀር ሲሆን፣ የተዋቀረው ኮሚቴ በመጪዎቹ ሦስት ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ወረርሽኝን ተከላክሎ ለማስተማር የሚያስችል ደረጃ ላይ መሆናቸውን፣ ከሚኒስቴሩ የሚላኩ ቁሳቁሶች መድረሳቸውን፣ በየትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ግብዓት መሟላቱን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች ትምህርቱን ማስኬድ ይችላሉ ወይ የሚለውን ይገመግማል ተብሏል፡፡

ኮሚቴው ትምህርት ቤቶችን ገምግሞ ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በግል ትምህርት ቤቶች የወላጅ ኮሚቴዎች የየትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት ካላረጋገጡና ወረርሽኙን ተከላክሎ ለማስተማር የሚያስችል ሁኔታ አለ ብለው ካላመኑ፣ ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመር እንደማይችሉ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ፣ የግል ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ክፍያ ላይ ምንም ጭማሪ እንዳያደርጉ ያስቀመጠውን ውሳኔ የተላለፉ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን ለጊዜው ማገዱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በአንድነት ኢንተርናሽናልና በግሪክ ኮሙዩኒቲ ትምህርት ቤቶች ላይ የተላለፈው ጊዜያዊ ዕገዳ፣  የወላጅ ኮሚቴዎች በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመርያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ሪፖርት እስኪያቀርቡ ድረስ፣ ምንም ዓይነት የትምህርት ሥራ እንዳያከናውኑ መታገዳቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...