Thursday, October 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ፍሬከናፍር‹‹የፖለቲካ ልሂቃን ያለ ምንም ልዩነት በአንድ አዳራሽ ተገናኝታችሁ ለዚህ አገርና ሕዝብ የሚበጅ...

  ‹‹የፖለቲካ ልሂቃን ያለ ምንም ልዩነት በአንድ አዳራሽ ተገናኝታችሁ ለዚህ አገርና ሕዝብ የሚበጅ ነገር ፍጠሩ››

  ቀን:

  ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ በመስቀል ክብረ በዓል ላይ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የክብረ በዓሉ መገለጫ በሆነው የደመራ ሥርዓት ላይ በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ለፖለቲካ ልሂቃን ባስተላለፉት የተማፅኖ ጥሪ፣ ለኢትዮጵያ ሰላም፣ እኩልነት፣ አንድነት፣ የሕይወትና የንብረት ዋስትና ይከበሩ የሚሉትን ነገሮች መሠረታዊ የጋራ አድርጋችሁ ያዙልን ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሌላውን ለሕዝቡ ስጡትና እርሱ ራሱ የፈለገውን ርዕዮተ ዓለም፣ የፈለገውን መንግሥት ራሱ መርጦ ያስቀምጥ፡፡ ነገሩ ሁሉ በዚህ አልቆ ወደ ልማትና ዕድገት እንግባ ሲሉም አክለዋል፡፡ ለወጣቶችም ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ልጆቻችን እባካችሁ ሰከን በሉ ጥያቄ አትጠይቁ አንልም፣ ግን የሰውን ሕይወትና ንብረት አታጥፉ፣ የሚጠፋው ንብረት የእናንተ ነውና›› ሲሉም አጽንኦት ሰጥተውበታል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img