ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመንን መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ሲከፍቱ የተናገሩት፡፡
በኢትዮጵያ ዓምና የተከሠቱት የሕግ ጥሰትና የሕዝብን ሕይወትና ንብረት የቀጠፉ አስነዋሪ ተግባራት ዴሞክራሲን የተረዳንበት መንገድ ምን ያህል በስህተቶች የተሞላ እንደሆነ በቂ ማሳያ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ ዘንድሮ ፖለቲከኞችም ይሁኑ ዜጎች ዴሞክራሲን በባዶ ከመሻት ባለፈ ዴሞክራሲ የሚጠይቀውን ሥርዓትና ዲሲፕሊን እንዲላበሱ ለማድረግ ከፍተኛ ሥራዎች የሚሠሩ ይሆናል ብለዋል፡፡