የጂኦግራፊ ሊቅ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ደራሲ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም (1922-2013) ሥርዓተ ቀብር መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡ ለበርካታ ዓመታት በፕሮፌሰርነት ባስተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመታሰቢያና የሽንት ሥነ ሥርዓት የተከናወነላቸው ‹‹ላበረከቱት አስተዋጽኦ እጅግ በጣም እናመሠግናለን›› በሚል መሪ ቃል ነው፡፡ ከስድስት ኪሎ ግቢ የተነሳው አስከሬናቸው አራት ኪሎ እስከሚገኘውና ዘለዓለማዊ ማረፊያቸው ወደ ሆነው ካቴድራል ያመራው በታላቅ አጀብ ነው፡፡ በሥርዓተ ቀብራቸው ላይ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በአሸኛኘቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ፎቶዎቹ የሽኝት መርሐ ግብሩንና የሥርዓተ ቀብሩን ገጽታ በከፊል ያሳያሉ፡፡