Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለአገር ውስጥ ኤጀንሲዎች ጥብቅ ትዕዛዝ ይስጡልን!

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለአገር ውስጥ ኤጀንሲዎች ጥብቅ ትዕዛዝ ይስጡልን!

ቀን:

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ምንም እንኳ ሠራተኛን ለሦስተኛ ወገን ቀጥሮ የማሠራት (Out Sourcing) የኤጀንሲነት ሥራ ባደጉ አገሮች የሠራተኛ እጥረትን ለመቅረፍ የተጀመረ ቢሆንም፣ በእኛ አገር ሥራ አጥነት እጅግ በጣም በተንሰራፋበት ድርጅቶች ሠራተኛ ፈልገው በማያጡበት ሁኔታ፣ ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ የማይቋረጥ ቋሚ ከፍተኛ ኮሚሽን የሚቆረጥበት ከአገልግሎት ተጠቃሚው ድርጅት በአንድ ሠራተኛ ከሚቀበሉት ላይ አንደ አራተኛውን ለሠራተኛው በመወርወር ሦስት አራተኛውን እየነጠቁ ኤጀንሲዎች በሕግ ፍቃድ የተሰጣቸው የጉልበት መበዝበዣ ተቋማት ሆነው የደሀ እንባ የሚረግፍባቸው እሮሮና ብሶት የሚዘንብባቸው፣ የመከራ ማዕከላት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በአገሪቱ ዘርፉን ለመምራት የወጡ ሕጎችም ሆነ ተብሎ የሕግ ክፍተት የተበጀላቸውና ለብዝበዛና ለዘረፋ የተመቻቹ መሆናቸው ደግሞ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዳይቻል ጭምር ያደረገ ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነበር፡፡

የኢትዮጵያን ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ባደረጉት አመራሮችና አባላት ትግል የአገራችን ሚዲያዎችም የሠራተኛውን ብሶትና እሮሮ በከፍተኛ ሁኔታ በማስተጋባታቸው፣ በአገራችን የመጣው የአመራር ለውጥም ተጨምሮበት፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓመታት ዝምታ በኋላ፣ በዘርፉ የተሰማሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሠራተኞችን መብት የሚያስከብር፣ የአገር ውስጥ ኤጀንሲዎች የሥራ ስምሪት መመሪያ በማዘጋጀት በዋናነትም ክፍያን በተመለከተ ኤጀንሲዎች ከአገልግሎት ተቀባይ ተቋማት በአንድ ሠራተኛ ከሚበሉት ላይ 80 በመቶ ለሠራተኛው መክፈል እንዳለባቸው በመወሰን ከታኅሳስ 22 ጀምሮ ሥራ ላይ ያዋለ ቢሆንም፣ ኤጀንሲዎች በማንአለብኝነት መመርያውን በመጣስ ከሕግ በላይ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሆነ የክክልልና የከተማ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች በመመርያው መሠረት ዕርምጃ ከመውሰድ በማፈግፈጋቸው በሠራተኞች ላይ የሚደርሰው ብዝበዛ ከመቀጠሉም በላይ ከታኅሳስ 22 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣውን መመርያ መሠረት አድርገው መብታቸውን የጠየቁ ሠራተኞች ከሥራ ለመታገድና ለወከባ ለቅጣት እየተዳረጉ ነው፡፡ ኤጀንሲዎች በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የገቡ ደላሎች እንጂ እነሱ ቀጥታ በራሳቸው የሚፈጥሩት የሥራ ዕድል እንደሌለ እየታወቀ ሠራተኛ ይበተናል እያሉ የሚያሠራጩትን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ባለመቀበል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሕግ እንዲያስከብር ጥብቅ ዕርምጃ እንዲወስድ እየጠየቅን ከ1000,000 በላይ ሠራተኛ አገሪቱ ያለችበትን ዘርፈ ብዙ ችግር ተገንዝቦ ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከመግባት ተቆጥቦ እየተበደለ ብሶቱ ዛሬም በመንግሥትም በግልም ሚዲያዎች ተደጋግሞ ዘወትር እየተሰማ፣ መንግሥት ባለበት አገር ሕግ ተጥሶ ተመልካች አጥቶ እየተዘረፈ የመንግሥትን ውሳኔ በትዕግስት እየጠበቀ መሆኑን ተረድተው ይኼ ገደቡን ያለፈ ብሶትና የሚሊዮኖች አቤቱታ ምላሽ ማጣት የተለያየ አጀንዳ ያላቸው የጥፋት ኃይሎች መጠቀሚያ ሆኖ ችግር እንዳይፈጠር፣ አፋጣኝ ቁርጥ ያለ ሕግ የማስከበር ሥራ እንዲሠራ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጡልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

  • የችግሩ ገፈት ቀማሾች
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...