Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓለም አቀፍ የተራድኦ ተቋማት በትግራይ ክልል የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ከፌዴራል መንግሥት ማብራሪያ...

ዓለም አቀፍ የተራድኦ ተቋማት በትግራይ ክልል የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ከፌዴራል መንግሥት ማብራሪያ ጠየቁ

ቀን:

የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር ግንኙነት ማቋረጡን ተከትሎ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ተቋማት በትግራይ ክልል የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ በተመለከተ፣ፌዴራል መንግሥት ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። 

የተራድኦ ተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች ማብራራያ እንዲሰጣቸው የጠየቁት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ፣ ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የውጭ ዲፕሎማቶች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ማብራሪያ ለመስጠት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ የተገኙ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማቋረጥ በመወሰኑ፣ እነሱ በክልሉ በሚኖራቸው እንቅስቃሴ ላይ ምን ዓይነት አንድምታ ሊኖረው እንደሚችል ግልጽ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በጠቅላይ ሚኒስትር ሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁንዴሳ (/) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር) እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተወካዮች መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ በማብራራት፣ ከዲፕሎማቶቹናዓለም አቀፍ የተራድኦ ተቋማት ተወካዮች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል። 

በዚህም መሠረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ሕገወጥ ሥራዎችን በሕጋዊ መንገድ ለማረም እንጂ ሕዝብን ለመጉዳት እንዳልሆነየፌደራሉ መንግሥት የክልሉን ሕዝብ መሠረታዊ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ከታችኛው የክልሉ መዋቅር ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ፣ ኃላፊዎቹ ማብራራታቸውን ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። 

እንዲሁም መንግሥት የሕግ የበላይነትንና የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር ቁርጠኛ አቋም እንዳለውም ነው ቃል አቀባዩ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ያብራሩት። ከዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ በትግራይ ክልል የተራድኦ ሥራዎች እንዴት ይቀጥላሉ ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ አምባሳደር ዲና በሰጡት ምላሽ፣ የተራድኦ ድርጅቶች የትግራይ ሕዝብን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎቻቸውን ከክልሉ ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር አጠናክረው መቀጠል እንደሚችሉ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በሁሉም ክልሎች እኩል መከበር የሚገባው እንደሆነ፣ በዚህ ረገድ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የሚያሳልፏቸው ውሳኔዎችም በሁሉም ክልሎች ገዥ እንደሆኑ ለዲፕሎማቶቹ ገለጻ መደረጉን አስረድተዋል። 

ይህንን ሕጋዊ ሥርዓት የትግራይ ክልል መንግሥት እየተገነዘበ ያካሄደው ምርጫ ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ የሚቃረን በመሆኑ ምርጫው ተቀባይነት እንደማይኖረው፣ የማይፀናና ሕገመንግሥታዊ መሆኑን የሚገልጽ ውሳኔ መተላለፉን ለመድረኩ ተሳታፊዎች ማስገንዘባቸውን ገልጸዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤትን የቀደመ ውሳኔ በመተላለፍ ክልሉ የተናጠል ምርጫ አካሂዶ መንግሥት በመመሥረቱ፣ የተመሠረተው መንግሥት ማለትም የክልሉ ምክር ቤትና አስፈጻሚ አካል ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖረው መወሰኑን አስረድተዋል።

የውሳኔው ዝርዝር አፈጻጸም በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚወጣም ተገልጾላቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የገንዘብ ሚኒስቴር ማክሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ፣ ከጥቅምት ወር ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ ተቋቁሟል ለተባለው የትግራይ ክልል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማይተላለፍ አስታውቋል። 

የበጀት ዓመቱ ከተጀመረ አንስቶ በነበሩት ሦስት ወራት ውስጥ፣ ለፌዴራል መንግሥትና ለሁሉም ክልሎች 97.7 ቢሊዮን ብር በጀት ማስተላለፉን ገልጿል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...